ምርጫችን

የመምረጥ ነጻነታችን እና የውሳኔዎቻችን ተጽዕኖ

 

ኤፍ.ዋይኒ ማክ ሌዎድ

 

ላይት ቶ ማይ ፓዝ የመጽሐፍ ስርጭት
Sydney Mines, Nova Scotia, CANADA B1V 1Y5

 


 

ምርጫችን

የቅጂ መብት © 2020 በኤፍ. ዋይ ማክ ሌዎድ

መብት ሁሉ የተጠበቀ ነው። ከፀሐፊው የጽሑፍ ፈቃድ ውጪ የትኛውም የዚህ መጽሐፍ አካል በማንኛውም መልክ ወይም መንገድ ሊሰራጭ ወይም ሊተላለፍ አይችልም።

ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉም በዚሀ መጸሐፍ ውስጥ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተወሰዱት ከEnglish Standard Version, copyright 2001 by Crossway Bibles, a division of Good News Publishers. ነው። የተፈቀደ። መብት ሁሉ የተጠበቀ ነው።


 

ማውጫ

መቅድም... 4

ምዕራፍ 1 ምርጫ እንደ ነፍስ ተግባር. 7

ምዕራፍ 2 የሰው ምርጫ እና የኃጢአት ውድቀት.. 13

ምዕራፍ 3 የመምረጥ ነጻነት.. 19

ምዕራፍ 4 የውሳኔ እና ቁርጠኝነት ተጽዕኖ.. 27

ምዕራፍ 5 የምርጫ ጥሪ. 35

ምዕራፍ 6 በምንመርጠው ምርጫ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሪት.. 44

ምዕራፍ 7 የመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና ውሳኔዎቻችን. 51

ምዕራፍ 8 እግዚአብሔርን የሚፈሩ አማኞች ምክር. 59

ምዕራፍ 9 ውሳኔዎቻችንን የሚከታተል አምላክ.. 67

ምዕራፍ 10 በውሳኔዎቻችን ጌታን መፈተን. 75

ምዕራፍ 11  ኃጢአት: አመጸኛ ፈቃድ.. 85

ምዕራፍ 12 ደህንነት: የፈቃድ መታደስ.. 93

ምዕራፍ 13 መቀደስ: የፈቃዳችን መማረክ.. 101

ምዕራፍ 14 እምነት: ከፍጻሜ የመድረስ ጥንካሬ.. 107

ምዕራፍ 15 ጸጋ: የመውደቅ ነጻነት.. 115

ምዕራፍ 16 የተስፋ ቃል ኪዳኖች አምላክ.. 124

ምዕራፍ 17 የቅዱሳን ውሳኔዎች.. 133

ላይት ቱ ማይ ፓዝ የመጽሐፍ ስርጭት.. 142

 


 

መቅድም

 

እግዚአብሔር ከሰጠን መሠረታዊ ነፃነቶች አንዱ የመምረጥ ነፃነት ነው። እንግዲህ እሱ የምርጫ እና የውሳኔ አምላክ ስለሆነ ይህ የእርሱን ባህሪ የሚያንፀባርቅ ነው። እኛ ግን መቼም ቢሆን ይህንን ነፃነት አቅልለን ማየት የለብንም በአዳምና ሔዋን ምርጫ ምክንያት ኃጢአት ወደዚህ ዓለም ገባ፣ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በኃጢአት ምክንያት የመጡ ውጤቶችን  እየተቀበልን እንገኛለን።

የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን ቅርፅ እና ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። በዚህ ምክንያት የምንወስደው መንገድ ልምዶቻችንን እና ዕጣ ፈንታችንን በጥልቀት ሊለውጠው ይችላል።

የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው፣ጌታ በምርጫዎቻችን ውስጥ እኛን ለመርዳት ጣልቃ አይገባም። መመሪያችን ይሆን ዘንድ ቃሉን እና መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል። እንግዲህ እሱ ውሳኔዎቻችንን ይመለከታል፤ከዓላማው ስንጎድል ደግሞ በቸርነቱ ይቅር ይለናል።

ስለሆነም ይህንን ነፃነት የሰጠን አምላክ አሁን መብታችንን እንድንጠቀም ይጠራናል። አስቀድሞ የመረጠን አምላክ አሁን ደግሞ እንድንመርጠው ይጠይቃል። ውሳኔ ላይ አለመድረስ አማራጭ አይደለም። ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ያልሆነ እንደሚቃወመው ተናግሯል (ሉቃስ 1123) ። በሎዶቅያ ለነበረው ቤተክርስቲያን በራድም ወይም ትኩስ ባለመሆኑ ምክንያት ከአፉ እንደሚተፋው ተናግሯሮ ነበር (ራዕይ 315) ።  

እንግዲህ ቁጭ ብለን ስናስብ የክርስትናን ሕይወት መኖር ለእኛ በጣም ቀላል መስሎ ይታየን ይሆናል። የጉዳዩ እውነታ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ማደግ ከፈለግን እኛ ልንወስናቸው የሚገቡን ውሳኔዎች ይኖራሉ። ከጌታ ከኢየሱስ ጋር በምንጓዘው የሕይወት ጉዞ ብስለት ከመንፈሱ ሥራ ውጭ ሊሆን ባይችልም፣የምንወስናቸው ውሳኔዎች እና ቁርጠኝነቶች እንዲሁ ከእርሱ ጋር ባለን ህብረት እና ቅርበት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።

እንደማንኛውም ወቅታዊ ጥናት፣ይህ አጠቃላይ ስዕል አይደለም። በእርግጥ እኛ ከምናደርጋቸው ውሳኔዎች የበለጠ በክርስትና ሕይወት ጉዞ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ። በምሰራቸው ነገሮች ውስጥ እንዲመራኝ እና አቅጣጫ እንዲያሳየኝ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደሚያስፈልገኝ በጥብቅ አምናለሁ። ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ማናቸውም ውሳኔዎቻችን በመጨረሻ ምንም ለውጥ አያመጡም። እኔ ደግሞ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ስለወደደኝ እንጂ እሱን ለመውደድ በጭራሽ እንዳልመረጥኩ አምናለሁ። እሱ ቅድሚያውን ይወስዳል፣ዳሩ ግን እኔም ለእሱ መላሽ መስጠት ይኖርብኛል። በማንኛውም የሕይወት ግንኙነት ውስጥ እንደዚህ አይደለምን? እኔ ባለቤቴን መውደድን ልመርጥ እችላለሁ ይሁን እንጂ እርሷም ደግሞ በምላሹ እኔን ለመውደድ ትመርጣለች።

ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ለመውደድ እና ራሱን ለእኛ ለመግለጥ ስለመረጠ፣አሁን ለእርሱ በቅንነት ምላሽ የመስጠት መብት አለን። እግዚአብሔር ለሕይወታችን አስደናቂ የሆነ ዓላማን በፊታችን አስቀምጧል። አሁን ልባችንን ከፍተን ያንን ዓላማ እንድንቀበል ይጠብቀናል። ለብዙ ዓመታት መጋቢ ከመሆን ሃሳብ ጋር እታገል ነበር። እግዚአብሔር ያለማቋረጥ መጋቢ በምሆንበት ሁኔታዎች ውስጥ አሳልፎኝ ነበር። በመጨረሻም ጌታን “እሺ ጌታ ሆይ፣ይህንን አደራ እቀበላለሁ” ያልኩበትን ጊዜ አስታውሳለሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነገሮች በልቤ ውስጥ ተቀየሩ። እግዚአብሔር ለህዝቡ ጥልቅ ልብ ሰጠኝ፣በሄድኩበት ሁሉ የመጋቢ ክትትልና መንፈሳዊ እንክብካቤ የሚሹ ሰዎችን እንዳማገኝ ተረዳሁ። እግዚአብሔር አንድን ሥራ መርጦልኝ ነበር፣ዳሩ ግን በእሱ ላይ ያለውን የበረከቱን ሙላት ከመለማመዴ በፊት ያንን ሚና በፈቃደኝነት መቀበል ያስፈልገኝ ነበር። እርሱ ለእኔ የመረጠልኝን መምረጥ ያስፈልገኝ ነበር።

በመሠረቱ፣የክርስትና ሕይወት ለክርስቶስ ፈቃድ እና ዓላማ መማረክ ነው። መማረክ ምንድ ነው? መማረክ ማለት የእግዚአብሔርን ዓላማ ለሕይወቴ የመቀበል ፈቃድ እና ነፃ ምርጫ ነው። ይህንን እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እየጠራን ነው። እርሱ አስቀድሞ ስለመረጠን እርሱን እንመርጥ ዘንድ እየጠየቀን ነው።

 

በዚህ ጥናት ውስጥ የመምረጥ ነፃነታችንን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመረምራለን እንዲሁም ስለምናደርጋቸው ምርጫዎች እና ውሳኔዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ምን እንደሚሉ እንገልፃለን። እግዚአብሔር ለክብሩ እንድንሆን ያሰበውን ሁሉ እንድንሆን አስፈላጊ ውሳኔዎችን ለማድረግ እንችል ዘንድ ይህንን ጥናት በማጥናታችን ጌታ ክብሩን ይወሰድ።

 

ኤፍ.ዋይኒ ማክ ሌዎድ


 

ምዕራፍ 1 - ምርጫ እንደ ነፍስ ተግባር

 

የሰው ፈቃድ ጥያቄ ከዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ውይይት የተደረገበት ነው። ጥንታውያን የግሪክ ፈላስፎች ስለ ሰው ፈቃድ ትርጓሜ እና ገደቦች ክርክር አድርገውበት ነበር። የጥንቷ ቤተክርስቲያን የሥነ-መለኮት ምሁራንም እንዲሁ ይህን ጥያቄ ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር መርምረዋል። በእርግጥ እነዚህን ታሪካዊ ክርክሮች መመርመር የእኔ ዓላማ አይደለም። እንደ መንፈሳዊ መጽሐፍት ጸሐፊ ዓላማዬ የሰው ፈቃድ ምንነት እና ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን የህይወት ጉዞ እና ግንኙነት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በቀላሉ ማጤን ነው።

እስቲ በአንዳንድ ትርጓሜዎች እንጀምር። መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጆች ነፍስ እንዳላቸው ያስተምራል። ነፍስ ከሥጋዊ አካል የተለየች ብትሆንም ዳሩ ግን እኛ እንደ ግለሰብ ማን እንደሆንን ታሳያለች። ነፍስ የስሜት፣የአመክንዮት እና የውሳኔ ችሎታ ያላት ክፍላችን ናት። እስቲ ስለዚህ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት።

 

የነፍስ ስሜቶችን እና ጥልቅ መሻቶች

በዘፍጥረት 34 ሴኬም ለያዕቆብ ልጅ ዲና ስላለው ጥልቅ የፍቅር ስሜት ምሳሌ ተቀምጧል፡  

8 ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት። (ዘፈጥረት 34:8)

 

የሴኬም ነፍስ ዲናን አንደናፈቀች አስተውሉ። በሌላ አገላለጽ፤እርሱ በነፍሱ ለእሷ ጥልቅ መስህብ እና ፍቅር ተሰምቶት ነበር።

 

ኢየሱስ ወደ ሞቱ ሲቃረብ በነፍሱ ውስጥ ጥልቅ ስሜት ተሰምቶት ነበር። የወንጌሉ ጸሐፊ ማርቆስ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ያሳለፈውን ጊዜ ሲናገር

33 ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና።

34 ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ ትጉም አላቸው። (ማርቆስ 14)

 

ኢየሱስ በነፍሱ ውስጥ ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማው በዚያ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ነገሯቸው ነበር። ስሜቶች የሰው ልጅ ነፍስ ተግባር ናቸው።

 

የነፍስ አመክንዮት እና የማስታወስ ችሎታ

የሰው ልጅ ነፍስ የአመክንዮት እና የመረዳት ችሎታ አለው። በመዝሙር 139 ላይ ዘማሪው የተናገራቸውን ቃላት ልብ በሉ፡

 

14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። (መዝሙር 139)

የዘማሪው ነፍስ የሰው አካል ተፈጥሮን ስታሰላስል በአስደናቂ ሁኔታ የተሠራመሆኑን ተረድታ ነበር። ነፍሱ በእግዚአብሔር ሥራ ውስብስብነት ተደነቀች።

እንደ ሰቆቃው ኤርሚያስ 3 ገለጻ፤ይህ አመክንዮት ያላት ነፍስ በዝርዝር የማስታወስ ችሎታ አላት

19 ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።

20 ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች። (ሰቆቃው ኤርምያስ  3)

 

ነፍስ ትዝታዎች የሚከማቹባት እንዲሁም ሃሳቦች የሚብላሉባት ስፍራ ናት

 

የነፍስ ውሳኔ እና ቆርጠኝነት

እንዲሁም ሌላ የሰው ነፍስ ተግባር አለ። ቁርጠኝነቶች እና ውሳኔዎች የሚደረጉት በነፍስ ውስጥ ነው። በዚህ ጥናት ውስጥ ይህንን በበለጠ በዝርዝር እንመረምራለን፤ እስቲ የዚህን ጥቂት ምሳሌዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ልስጥ።

ከዘፍጥረት 27 እናነባለን፡

1 ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው፤ እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው።

2 እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ አረጀሁ፥ የምሞትበትን ቀን አላውቅም።

አሁንም ማደኛህን የፍላጻህን አፎትና ቀስትህን ውሰድ፥ ወደ ምድረ በዳም ውጣ፥ አደንም አድንልኝ፤

4 ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ። (ዘፍጥረት 27)

እነዚህ ቁጥሮች ይስሐቅ ልጁን ኤሳውን ለመባረክ ያለውን ፍላጎት ይናገራሉ። በተለይም ይህ የመባረክ ውሳኔ የነፍሱ ተግባር እንደነበረ አስተውሉ ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህይላል። ይስሐቅ በነፍሱ ለልጁ ርህራሄ ስለተሰማው እሱን ለመባረክ እንደሚፈልግ አምኖ ነበር። ከዚህ ዓላማ ጋር ወደፊት የመሄድ ውሳኔው የነፍሱ ተግባር ነበር።

በዘዳግም 26 እግዚአብሔር ሕዝቡ በፍጹም ልባቸው እና ነፍሳቸው ትዕዛዛቱን በመታዘዝ እንዲመላለሱ አዘዛቸው፡

16 አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው፥ አድርገውም።

17 አንተ በመንገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ፥ ቃሉንም ትሰማ ዘንድ እግዚአብሔር እርሱ አምላክህ መሆኑን ዛሬ አስታውቀሃል።

 

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ጌታ ህዝቡን በፍጹም ነፍሳቸው ይታዘዙ ዘንድ ማዘዙ ነው። በሌላ አገላለጽ በነፍሳቸው ውስጥ ለማድረግ የሚያስፈልጋቸው ቁርጠኝነት ነበር። ያ ቁርጠኝነት ለጌታ እና ለህይወታቸው ስላለው ዓላማ በፍፁም ታዛዥነት መመላለስ ነው።

ዘማሪው ይህን ሲናገር ለእግዚአብሔር የሚደረግን የነፍስ መሰጠት ተረድቶ ነበር፡

167 ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች፥ እጅግም ወደደችው። (መዝሙር 119)

 

የእግዚአብሔርን ምስክርነት ለመጠበቅ ውሳኔው በዘማሪው ነፍስ ውስጥ ነበር። በነፍሱ ውስጥ ለጌታ ምስክርነት ጥልቅ መሻት እና ፍቅር ስለተሰማው በእነዚህ መንገዶች ለመራመድ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

በነፍስ ውስጥ የተደረጉ ሁሉም ውሳኔዎች ለመልካም አይደሉም። በሉቃስ 12 ላይ የሰፈረውን የጌታን ትምህርት አስተውሉ። በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ እቅድ እያወጣ ስለ ነበር አንድ ሀብታም ሰው ተናግሯል።

19 ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።

20 እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው። (ሉቃስ 12)

እንግዲህ እዚህ ጋር በነፍስ እና በመዝናናት፣በመብላት፣በመጠጣት እንዲሁም በደስታ ውሳኔ መካከል ያለውን ግንኙነት አስተውሉ። ይህ ውሳኔ ለእግዚአብሔር ወይም ለዓላማው ምንም ባለማሰብ በነፍሱ የተወሰነ ነው። በመጨረሻም፣ያ ውሳኔ ሰውየውን የሕይወት ዋጋ ያስከፍለዋል። ነፍስ ስሜት እና አመክንዮትን የያዘች ናት፤በዚህም በነፍስ ውስጥ ውሳኔዎች እና ቁርጠኝነቶች ይደረጋሉ።

 

በዚህ ጥናት ውስጥ ውሳኔዎችን እና ቁርጠኝነቶችን የሚያደርገውን ይህን የነፍስ አቅም እንመለከታለን። ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጊት መካከል አንዱን የመምረጥ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ችሎታ አለን። እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ ያሉንን ውሳኔዎች እና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች የመወሰን አቅም አለን።

ይህንን የመምረጥ ነፃነት በየዕለቱ እንጠቀማለን። ጠዋት ከእንቅልፋችን ነቅተን ከአልጋ ለመነሳት እንወስናለን። ከዚያ በኋላ በነፍሳችን ውስጥ ስለ ህይወታችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች ነገሮች በተመለከተ ባወጣነው እቅድ መሠረት ውሳኔዎችን በማድረጉ ረገድ ቀኑን ሙሉ እንቅስቃሴ እንደርጋለን። እኔ እንደ ፈቃዴ ተግባር ይህንን ምዕራፍ ከኮምፒውተሬ ፊት ለፊት ተቀምጬ እጽፋለሁ። እግዚአብሔር ወደዚህ አገልግሎት እንደጠራኝ አምናለሁ ስለዚህ ለማጥናት እና ለመጻፍ ጊዜ እወስዳለሁ። እንዲሁም ሌሎች የማደርጋቸው ነገሮች ይኖራሉ። በእውነቱ፣ስለዘገዩ ሌሎች ነገሮች አስባለሁ ነገር ግን በነፍሴ፣ይህንን እንደ ቅድሚያ እመለከተዋለሁ፣ስለዚህ ለእሱ ጊዜ ለመስጠት እወስናለሁ።

ነፍስ ስሜት አላት ሲሆን እውነታዎችን ማቆየት እና ማቀናበር ትችላለች ዳሩ ግን እነዚህ ነገሮች በራሳቸው በቂ አይደሉም። ነፍስ እነዚያን ስሜቶች እና ሀሳቦች  በማጣራት ወደ ውሳኔዎች እና ቁርጠኝነት ይለውጣቸዋል። በሚሰማው እና በሚረዳው ላይ በመመርኮዝ የሚወስደውን እርምጃ የሚወስን ነው።

እንዳየነው ሁሉም የነፍስ ውሳኔዎች እና ተግባሮች ጽድቅ እና ቅዱስ አይደሉም። ኃጢአት በሰው ፈቃድ ውሳኔዎች እና ፍላጎቶች የተነሳ ይኖራል። በዚህ ምድር ላይ እርግማን ያመጣው የአዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን አለመታዘዝ ውሳኔ ነበር። ውሳኔዎቻችን የህይወታችንን ቅርፅ እና ገጽታ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ይለውጣሉ።

 

ለግንዛቤ፡

ነፍስ ምንድ ነው? የሰው ልጅ ነፍስ ተግባር ምንድ ነው?

 

የነፍሳችን ውሳኔ በሕይወታችን እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ጉዞ ላይ አስከምን ድርስ ተጽዕኖ ያሳድራል?

 

ነፍሳችን ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች ምንድ ናቸው ?

 

ለጸሎት:

ጌታ የማሰብ፤የአመክንዮት እና የመወሰን ችሎታን ስለሰጠን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። በሕይወታችሁ ትክክለኛውን ውሳኔ መወሰን ትችሉ ዘንድ ጸጋን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።

 

በሕይወታቸው መጥፎ ውሳኔ የወሰኑ ሰዎችን ታውቃለህን? ጌታን እነርሱን ታገለግል ዘንድ እና እርሱ ብቻ ቅድሚያ ወደሚሰጠው ስፍራ እንድታመጣቸው ጸልይ


ምዕራፍ 2 - የሰው ምርጫ እና የኃጢአት ውደቀት

 

እግዚአብሔር የሰው ልጅን ስሜት እና አመክንዮት ካለው ነፍስ ጋር ፈጠረው። ያ ነፍስ ሃሳቦችን ማዘጋጀት፣ውሳኔዎችን መወሰን እንዲሁም በአንዱ እና በሌላ ድርጊት መካከል መምረጥ ይችላል። ነፍሳችን በተረዳችው እና በሚሰማት ላይ በመመርኮዝ ውሳኔ መወሰን እና ቅድሚያን ማድረግ ትችላለች። ይህ በከፍተኛ ኃላፊነት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል። ከመካከላችን ትክክለኛውን ውሳኔ አድርገናል ማለት የሚችል ማን ነው? ብዙውን ጊዜ የነፍሳችን ፍላጎቶች በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ሊያጠፉን ይችላሉ። የነፍስ አመክንዮት በእውነታው ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።

የነፍሳችን ውሳኔዎች ሕይወትን የሚቀይር ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በአንጻሩ አጥፊም ሊሆኑ ይችላሉ። በዘፍጥረት 2 ላይ በኤደን ገነት ውስጥ የዚህን ምሳሌ እናገኛለን።

15አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።

16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤

17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። (ዘፍጥረት 2)

በዘፍጥረት 2:15-17 ጌታ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውን ዛፍ በገነት ውስጥ እንዳስቀመጠው እና አዳምን እንዳይበላ እንደከለከለው አስተውሉ። እኛ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ይህ ነው፤እግዚአብሔር አዳም መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ እንዲበላ ካልፈለገ ለምን በገነት ውስጥ አኖረው?

የተከለከለውን ዛፍ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ በማስቀመጥ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ምርጫ ሰጥቷቸው። እግዚአብሔር በአዳም ውስጥ የፈጠረውን የነፍስ ውሳኔዎች አክብሮ ከፍጥረቱ ጋር የሚፈልገውን ዓይነት ግንኙነት አሳይቷል። እግዚአብሔር ለአዳም ስሜትን፣አመክንዮትን እና ጥልቅ የሆነ ቁርጠኝነት ያለውን ነፍስ ሰጠው። ግንኙነቶችን ትርጉም ያለው የምታደርገው ነፍስ ናት። ነፍስ ለሌላው ጥልቅ የሆነ ፍቅር እና ፍላጎት ይሰማታል። የአመክንዮት አቅም ፍላጎቶችን ለማስተናገድ እና ምላሽ ለመስጠት ያስችለናል። ስለ ባልንጀራዎቻችን በእውቀት እና ግንዛቤ እንድናድግ ያስችለናል። እነርሱን እና ለእኛ የሚሰጡን ምላሾች እንድንረዳ ይረዳናል። ለእነሱም አፍቃሪ እና ዘላቂ ውሳኔ እንድናደርግ ያስችለናል። ያለ ነፍስ ግንኙነታችን ሁሉ ሜካኒካል ይሆናል።

የመኪና ሞተርን እና እያንዳንዱ ክፍል ከሌላው ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እና ተሽከርካሪው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ይንቀሳቀስ ዘንድ አብረው እንዴት እንደሚሰሩ ያስቡ። እያንዳንዱ ክፍል ከሌላው ጋር በሚስማማ ሁኔታ ይሠራል ነገር ግን ሞተሩ ነፍስ የለውም። ፍላጎት፣ማስተዋል ወይም በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ውሳኔም አይሰጥም።

እግዚአብሔር የሰው ልጆችን እንደ ሞተር ሊፈጥር ይችል ነበር፣ዳሩ ግን እንደ ነፍሱ ተግባር ነፍስና ፈቃድ መስጠትን መረጠ። ይህን በማድረጉ በጣም የተለየ የግንኙነት ዓይነትን ቀየሰ። ፍላጎት፣መረዳትና ቁርጠኝነት አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች የሆኑበትን ግንኙነት አስተዋውቋል።

እግዚአብሔር ነፍስን በመስጠት እኛ እንዲሆን የሰራነው አይነት ሜካኒካዊ ግንኙነት እንደማይፈልግ አሳይቶናል። ይልቁንም ህዝቡ በፈቃደኝነት እሱን ለመውደድ የመረጡበትን ግንኙነት ይፈልግ ነበር። ፍላጎት፣መግባባት እና ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ቁርጠኝነት ያለው ሕብረት ነው።

እግዚአብሔር ለአዳም ምርጫን ለመስጠት መልካምና ክፉን የሚያስታውቀውን ዛፍ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ አኖረ። ያለመታዘዝን ዕድል ሰጠው። ከእሱ ለመራቅ የምርጫ ዕድል ሰጠው። እውነተኛ ፍቅር እና ቁርጠኝነት ምርጫን ይፈልጋል። ከእርሱ ለመራቅ ነጻ ነኝ ዳሩ ግን ላለመራቅ መርጫለሁ። ለሌላ ነገር ቅድሚያ ለመስጠት ነጻ ነኝ፣ነገር ግን በምትኩ ራሴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ። ታማኝነት የጎደለው ከመሆን ይልቅ መከራን ለመቀበል እመርጣለሁ። ይህን በፈቃደኝነት እና በደስታ ልብ አደርጋለሁ።

እግዚአብሔር ፈቃድ እና የመምረጥ ችሎታ ስለሰጠን ከእሱ ጋር ያለንን ግንኙነት በጣም ግላዊ ያደርገዋል። እንዲሁም ሌላ መንገድ የመምረጥ እድልም ይሰጠናል። በኤደን ገነት ውስጥ የሆነው ይህ ነው። ሔዋን በዲያብሎስ ተፈትና መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ ፍሬውን በመውሰድ በልታ ለባሏ እንዲበላው ሰጠችው። የዛፉ ፍሬ የተከለከለ መሆኑን ጠንቅቃ በማወቅ ይህን አደረገች። ሔዋን በእባቡ በመታለል   ላለመታዘዝ ሆን ብላ ውሳኔ አደረገች። እግዚአብሔር አላገዳትም። ግንኙነታቸውን የሚያበላሽ ቢሆንም ያንን ውሳኔ እንድታደርግ ፈቀደላት።

እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ ውሳኔ የነፍስ ተግባር ነበር። አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር እና ከአላማው መራቅን መረጡ። አለመታዘዝ ብችልም እኔ ለድርጊቶቼ ተጠያቂ እና ለወሰንኩት ውሳኔዎችም ኃላፊነት አለብኝ። በመጥፎ ምርጫዎቼ ምክንያት በመጡ ውጤቶች እሰቃያለሁ። በአዳምና በሔዋን ላይ የሆነው ይህ ነው። የእግዚአብሔር እርግማን በዓለም ላይ ወደቀ። ከእሱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከእንግዲህ ተመሳሳይ አይሆንም። አንዳቸው ከሌላው ጋር የኖሩበት ቅርርብ የተበላሸ ነው። ፍጥረት በኃጢአታቸው እና በአመፃቸው ክብደት እየቃተተ ነው። አዳምና ሔዋን በዚያ ቀን ያደረጉት ውሳኔ የዓለምን አቅጣጫ የቀየረ ሲሆን የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ህብረት ለመመለስ የአዳኝ ጣልቃ ገብነት ይጠይቅ ነበር።

እግዚአብሔር ስሜት፣አመክንዮት እና ጥልቅ የሆነ ቁርጠኝነት ካላት ነፍስ ጋር ፈጠረን፤ ዳሩ ግን ያቺ ነፍስ መጥፎ ውሳኔዎችን የማድረግ ችሎታ አላት። የእነዚህ መጥፎ ውሳኔዎች ውጤት አጥፊ ሊሆን ይችላል። ከእግዚአብሔር ጋር በግል እና በተቀራረበ ግንኙነት ለመደሰት እንድችል ታስባ የተሰራች ነፍስ እንዲሁ ከእቅፉ ውስጥ ልታስወጣኝ ትችላለች። የመምረጥ ችሎታ ያለው የሰው ነፍስ ኃይለኛ ስሜት አለው። ወደ እውነት እና ወደ ጽድቅ ጎዳናዎች ወይም ወደራሱ ወደ ገሃነም ጉድጓድ ሊወስደኝ ይችላል። ይህንን ፈቃድ ለህይወታችን ቅርፅ እና ሁኔታ በትክክል መጠቀማችን በምንወስናቸው ውሳኔዎች ላይ ምን ያህል አስፈላጊ ነው።

 

ለግንዛቤ:

እግዚአብሔር መልካሙን እና ክፉውን የምታስታውቀውን ዛፍ ለምን በገነት ውስጥ ያኖረ ይመስላችኋል?

 

በሜካኒካዊ እና በግላዊ ህብረት ውስጥ ያለው ልዩነት ምንድ ነው? ነፍስ በዚህ ዙሪያ የምትጫውተው ሚና ምንድ ነው?

 

የምንወስናቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

 

ከእግዚአብሔር ጋር ለመጓዝ እና እርሱን ለመታዘዝ እንመርጣለን? ኃጢአት ምንድ ነው?

 

የሕይወታችን ቅርጽ እና ሁኔታ በምንወስነው ውሳኔ እንዴት ይቀየራል ?

 

ለጸሎት:

እግዚአብሔር ስሜት፤አመክንዮት እና በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ የሚያደርግ ነፍስ ያለህ አድርጎ ስለፈጠረህ አመስግን 

 

እግዚአብሔር ለሕይወት ትክክለኛውን ውሳኔ ትወስን ዘንድ እንዲረዳህ ጸልይ። እርሱን እና ዓላማውን እንድትጠብቅ ራስህን አስገዛ።

 


 

ምዕራፍ 3 - የመምረጥ ነጻነት

 

እግዚአብሔር የመምረጥ ችሎታን ፈጥሮልናል። በመጨረሻው ምዕራፍ ይህ ምርጫ ለእርሱ ያለንን ቁርጠኝነት በጣም ግላዊ እንደሚያደርገው ተመልክተናል። የዚህን የመምረጥ ነፃነት ማስረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናያለን።

እንደ ምሳሌ በዘጸአት 17 ላይ ያለውን የሙሴን ውሳኔ እንመለክት:

8 አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።

9 ሙሴም ኢያሱን፦ ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው።

10 ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ።

1 እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።

12የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ።

13 ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ። (ዘጸአት  17)

ሙሴ የእግዚአብሔርን ህዝብ በምድረ በዳ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲመራ የአማሌቃውያንን ጦር ወደ ገጠሙበት ወደ ራፊድ መጡ። እነዚህ አማሌቃውያን እስራኤላውያን በምድራቸው እንዲያልፉ ለመፍቀድ አልፈለጉም ነበር፤እንደ ስጋትም ይመለከቷቸው ነበር። ሙሴ ሁኔታውን ተመልክቶ ውሳኔ አደረገ። ለኢያሱ ሰራዊት እንዲሰበስብ እና ከጠላቶቻቸው ጋር ለመዋጋት እንዲሰለፉ አዘዘው።                  ሙሴም የእግዚአብሔርን በትር በእጁ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ። ያንን በትር ወደ ላይ ከፍ ባደረገ ጊዜ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ድል ይነሱ ነበር። በዚያ ቀን እግዚአብሔር ከአማሌቃውያን ጋር ጦርነት ለማካሄድ ያደረገውን የሙሴን ውሳኔ አክብሮ ለእስራኤል ድል አጎናጸፈ።

በዚያ ቀን ሙሴ ተቃዋሚዎቹን ፊት ለፊት ለመግጠም ወስኖ ነበር። ከእነሱ ፊት ለመሸሽ ሳይሆን እነሱን ለመጋፈጥ መርጠ። እግዚአብሔር ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደጠራቸው ያውቅ ስለነበረ በእግዚአብሔር ኃይል ጠላቱን ለመጋፈጥ ወሰነ።

ሁሉም ውሳኔዎች እግዚአብሔርን የሚያከብሩ አይደሉም። እስራኤላውያን በምድረ በዳ ጉዞቸውን ሲቀጥሉ ስለ ኑሯቸው ማጉረምረም ጀምረው ነበር። ሕዝቡ የደረሰባቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ ከግምት ካስገባ በኋላ ውሳኔ ሰጠ:

2 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ፦ በግብፅ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ!

3 እግዚአብሔርም በሰይፍ እንሞት ዘንድ ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሴቶቻችንና ልጆቻችን ምርኮ ይሆናሉ፤ ወደ ግብፅ መመለስ አይሻለንምን? አሉአቸው።

4 እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ። (ዘኍልቍ 14)

 

በዚያ ቀን ህዝቡ አዲስ መሪን በመምረጥ ወደ ግብፅ ለመመለስ ወሰኑ። በዚህ ውሳኔ ምክንያት ጌታ ሕዝቡን በታላቅ ቸነፈር መታው (ዘኍልቍ 14:11-12) የሙሴ ምርጫ ለህዝቡ መማለድ ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ያጠፋቸው ነበር። ዘኍልቍ 14 በምርጫዎች የተሞላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ሕዝቡ በእግዚአብሔር ዓላማ ላይ ማመጽን መረጠ። እግዚአብሔርም እነሱን ለማጥፋት መረጠ። ሙሴ ደግሞ ስለ እነርሱ መማለድን መረጠ። ከዚያም እግዚአብሔር መጸጸት እና ይቅር ማለትን መርጠ። እነዚህ ውሳኔዎች የእስራኤልን የወደፊት አቅጣጫ የሚነኩ ህይወትን የሚቀይሩ ውሳኔዎች ነበሩ።

ጓደኛው ኤልፋዝ ኢዮብ ስለ መከራው ያቀረበውን ቅሬታ ካዳመጠ በኋላ ምላሽ ሰጠ።

1ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦

2 በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ንፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን?
በሆዱስ የምሥራቅን ነፋስ ይሞላልን?

3 ከማይረባ ነገር፥
ወይስ ከማይጠቅም ንግግር ጋር ይዋቀሳልን?

4አንተም እግዚአብሔርን መፍራት ታፈርሳለህ፤
በእግዚአብሔር ፊት አምልኮን ታስቀራለህ።

5በደልህ አፍህን ያስተምረዋል፥
የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ።

6 የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል። (ኢዮብ 15)

 

በተለይም ኤልፋዝ መጥፎ ውሳኔን በመወሰኑ ምክንያት ኢዮብን እንደከሰሰው አስተውሉ በእግዚአብሔር ፊት አምልኮን ታስቀራለህ።” (ቁጥር 5) ይላል። በሌላ አገላለጽ ኤልፋዝ ኢዮብ ለእግዚአብሔር እና ለዓላማዎቹ ምንም አክብሮት ሳያሳይ ለቅሬታው በነፃነት መናገርን መርጧል ብሎ ያምናል። ኢዮብ ለመናገር የመረጠው ቃል እግዚአብሔርን እንደሚያዋርድ ተሰምቶት ነበር። ኤልፋዝ ኢዮብ ቃላቱን ይበልጥ በጥንቃቄ መምረጥ እንዳለበት ያምን ነበር።

ኢየሱስ በሚከተለው ንግግሩ የተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ አንጸባርቋል፡

36 እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ (ማቴዎስ 12)

በግዴለሽነት የተሞሉ ቃላትን የመናገር ነጻነት አለን፤ዳሩ ግን በፍርድ ቀን ስለተናገርናቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ እንሰጣለን

የምሳሌ መጽሐፍ ጸሐፊ በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች በምርጫቸው ሲገስጻቸው እንመለከታለን፡

29  እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤

30 ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤

31 ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ። (ምሳሌ 1)

 

የዚያን ጊዜ ሰዎች እግዚአብሔርን መፍራት አልመረጡም ነበር። የእግዚአብሔርን ምክርና ተግሣጽ ለመናቅ ወሰኑ። በውጤቱም እግዚአብሔር ለክፉ መንገዳቸው አሳልፎ ሰጣቸው። በአዲስ ኪዳን ሐዋርያው ጳውሎስ ሲጽፍ ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።

 

18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤

19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።

20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።

22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥

23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤

25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።

(ሮሜ 1)

እግዚአብሔር ራሱን ለሮማውያን ገልጧል፣ነገር ግን እሱን ላለማክበር መረጡ። ይልቁንም ሰውነታቸውን ለሥጋዊ ምኞቶች አሳልፈው በመስጠት ለጣዖታት ይሰግዱ ነበር። በውሳኔያቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለሥጋቸውና ለመንገዶቹ አሳልፎ ሰጣቸው። በመጨረሻም፣በራሳቸው ምኞቶች ተውጠው በኃጢአታቸው ጠፉ።

በዚህ ሕይወት ውስጥ የምንወስናቸው ምርጫዎች እንዳሉን ግልጽ ነው። እነዚያ ምርጫዎች በዚህች ምድር እና በሚመጣው የሕይወታችን ቅርፅ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል። የምናደርጋቸውን ውሳኔዎች አስፈላጊነት በመረዳት፣እግዚአብሔር ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንዲያደርግ በዘዳግም 30 ውስጥ ሕዝቡን ይማጸናል:

15 “ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ።

16 በሕይወትም እንድትኖር እንድትባዛም፥ አምላክህም እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እንዲባርክህ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙንና ሥርዓቱን ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ።

17 ልብህ ግን ቢስት አንተም ባትሰማ፥ ብትታለልም፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድ ብታመልካቸውም፥

18 ፈጽማችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን አታስረዝሙም።

19 በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤

20 እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ።

(ዘዳግም 30)

እግዚአብሔር የሕይወትንና የሞትን መንገድ በሕዝቡ ፊት ያስቀመጠ ሲሆንሕይወትን ምረጡሲል ተማጸናቸው። ለሕዝቡ የመምረጥን ክብር ሰጣቸው ሆኖም ግን የተሳሳተ ውሳኔ በማድረጋቸው ስለሚያስከትለው ውጤት አስጠንቅቋቸዋል።

የእስራኤል የጦር አዛዥ ኢያሱ ወደ ሕይወቱ ፍጻሜ ሲቃረብ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በፊቱ እንዲሰበሰቡ ጠርቶ እነዚህን ቃላት ነገራቸው፡

14አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።

15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።  (ኢያሱ 24)

 

ኢያሱ የእስራኤልን ልጆች አምላኮቻቸውን አውጥተው እንዲጥሉ እንዲሁም አንዱን እና እውነተኛውን የእስራኤልን አምላክ ያገለግሉ ዘንድ ዓይኖቻቸውን በእርሱ ላይ እንዲያኖሩ አስጠነቀቃቸው። እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡበማለት ለሕዝቡ ምርጫን እንዴት እንደሰጠ ልብ በሉ (ቁጥር 15)። የአሞራውያንን አማልክት ወይም የሚያመልኳቸውን ማንኛውንም የሐሰት አምላክ የመምረጥ ነፃነት እንዳላቸው አሳውቋቸዋል እርሱ ግን-   “እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። በማለት የግል ውሳኔውን ገልጦላቸዋል (ቁጥር 15)

እነዚህ ቁጥሮች ምን ያስተምሩናል? እንደ ሰው የተፈጠርነው ውሳኔ ከማድረግ ችሎታ ጋር እንደሆነ በጣም ግልፅ ነው በእግዚአብሔር ኃይል ጠላቶቻችንን ለመቃወም ወይም ከእግዚአብሔር ርቀን ለመሄድ ምርጫ አለን በቃላችን እግዚአብሔርን ለማክበር ወይም በዓላማው ላይ ለማማረር መወሰን አለብን በመታዘዝ ለመመላለስ ወይም የእግዚአብሔርን ተግሣጽ እና ምክር ለመናቅ መወሰን አለብን። በሕይወት እና በሞት መካከል የመምረጥ ግዴታ አለብን የእስራኤል አምላክም ሆነ የአሕዛብ አማልክት የምናገለግላቸውን በልባችን ውስጥ መወሰን አለብን በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ ውሳኔዎች በሕዝቡ ፊት አስቀምጧል

እግዚአብሔር ምርጫን በፊታችን አስቀምጦ ውሳኔ እንድናደርግ ይጠይቀናል በጽናት ለመቆም ወይስ ከእርሱ ለመራቅ ትመርጣላችሁ? በቃልም ሆነ በተግባር እርሱን ለማክበር ትመርጣላችሁ ወይስ ለራሳችሁ ምኞት ቃሉን ታግፋፋላችሁ? እግዚአብሔርን ወይንስ ይህን ዓለም ትመርጣላችሁ? እነዚህ በየቀኑ በንቃት ልንወስዳቸው የሚገቡ ውሳኔዎች ናቸው ሁልጊዜ ትክክለኛውን ውሳኔ አንወስንም ብዙጊዜ እግዚአብሔር ለእኛ ካዘጋጀው ደረጃ ስንጎድል እንገኛለን ለወሰናቸው ውሳኔዎች ኃላፊነትን መውሰድ አለብን እግዚአብሔር ውሳኔ የመወሰን እና ቁርጠኝነትን የማሳየት ችሎታ ካለው ነፍስ ጋር ስለፈጠረን ለምናደርጋቸው ውሳኔዎች በእርሱ ተጠያቂ እንደሆንን በመገንዘብ ህይወታችንን መምራት አለብን በሕይወት ውስጥ የምናደርጋቸው ምርጫዎች በሕይወታችን ባለን ፍሬያማነት እና ከእግዚአብሔር ጋር ባገኘነው ቅርበት ይንጸባርቃሉ

 

ለግንዛቤ፡

በሕይወታችሁ ተግዳሮት ገጥሟችሁ ያውቃልን? እነዚህ የሕይወት ተግዳሮቶች በገጠሟችሁ ጊዜ የመረጣችሁት ምርጫ ምንድ ነው? ያ ምርጫ ውጤቱ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አሳደረ?

 

ሐዋሪያው ያዕቆብ አንደበት ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ የሆነ የሰውነታችን ክፍል እንደሆነ ይናገራል። የምንናገራቸውን ቃላት መምረጥ እንችላለን? ምርጫችን እግዚአብሔርን እና በዙሪያችን ያሉትን እንዴት ያከብራል ወይስ ያዋርዳል?

 

በሕይወታችሁ ለፈተና እጅ ሰጥታችሁ ታውቃላችሁን? በዚህ ጉዳይ ላይ የምርጫ ነጻነታችሁ መጫወት ያለበት ሚና ምንድ ነው?

 

እግዚአብሔርን እና ቃሉን በመታዘዝ መመላለስን መምረጥ እንችላለን? ሁልጊዜ ይህንን መንገድ ትመርጣላችሁን?

 

በየዕለቱ የምንወስናቸው ውሳኔዎች ምን ያህል አስፈላጊ ናቸው? የምንወስናቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን ቅርጽ እና ሁኔታ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንድ ነው?

 

ለጸሎት፡

በሕይወታችሁ በሚገጥማችሁ ተግዳሮቶች ጽንታችሁ ትቆሙ ዘንድ ጌታ ጸጋን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ። ትክክለኛውን ነገር መምረጥ ትችሉ ዘንድ ጥበብን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።

 

በየዕለቱ እርሱ እንድትመርጡ የሚጠይቃቸሁን ምርጫ በሚገባ ታውቁ ዘንድ እውቀት እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።

 

በሕይወታቸው የተሳሳተ ውሳኔ የወሰኑ ሰዎችን ታውቃላችሁን? ለእነዚህ ለመረጧቸው የተሳሳቱ ውሳኔዎች እግዚአብሔር አይኖቻቸውን ይከፍት ዘንድ ለጸሎት ትንሽ ጊዜ ውሰዱ። እነዚህን ውሳኔዎች ለእርሱ ይናዘዙ ዘንድ ፈቃደኝነቱን እንዲሰጣቸው ጸልዩ። ጌታ ከእርሱ ይማሩ እና ሕይወትን ይመርጡ ዘንድ ፈቃደኝነቱን እንዲሰጣቸው ጸልዩ። 


 

ምዕራፍ 4 - የውሳኔ እና ቁርጠኝነት ተጽዕኖ

 

የምናደርጋቸው ምርጫዎች በሕይወታችን ላይ ሕይወትን የሚቀይር ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ስለዚህ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ምሳሌዎችን እናገኛለን                በገነት ውስጥ የነበረውን የአዳምና ሔዋን ውሳኔ ውጤት አስቀድመን ተመልክተናል በአንዳንድ ቁልፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ-ባህሪያት በተደረጉ ምርጫዎች አማካኝነት ያሳደሩትን ተጽዕኖ በተመለከተ ተጨማሪ ምሳሌዎችን ትንሽ ጊዜ ወስደን እንመልከት

እስቲ በመጀመሪያ ንጉስ ዳዊት ከጎረቤቱ ሚስት ቤርሳቤህ ጋር በነበረው ግንኙነት የመረጠውን ምርጫ እንመልከት የጎረቤቱ ሚስት ለመታጠብ ስትወጣ ዳዊት በቤቱ ጣሪያ ላይ ሆኖ ሴቲቱን የተመለከተበትን ታሪክ በደንብ እናውቃለን ዳዊት በቤርሳቤህ ውበት የተሳበ እንደሆነ አውቆ አንድ ውሳኔ ወሰነ

4 ዳዊትም መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኵሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤትዋም ተመለሰች።

5 ሴቲቱም አረገዘች፥ ወደ ዳዊትም፦ አርግዤአለሁ ብላ ላከችበት። (2 ሳሙኤል 11)

ቤርሳቤህ የዳዊትን ልጅ ማርገዟን ይፋ ባወጣች ጊዜ ዳዊት ተጨማሪ ውሳኔዎችን ማድረግ ነበረበት ልጁ የእርሱ ነው ብሎ በማሰብ የቤርሳቤህን ባለቤት ማታለልን መረጠ ከጦር ሜዳ ጠርቶ ወደ ቤቱ ሄዶ ከሚስቱ ጋር እንዲሆን አግባባው የቤርሳቤህ ባል ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ዳዊት እንዲገደል በማሰብ በጦርነቱ ፊት ለፊት እንዲቆም አዘዘ ባሏ ከሞተ በኋላ ዳዊት  ቤርሳቤህን ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት

የዳዊት ውሳኔዎች በሕይወቱ ያለውን የእግዚአብሔርን ዓላማ በቀጥታ የሚቃወሙ ነበሩ ዳዊትን ይገሥጽ ዘንድ ጌታ ነቢዩ ንናታንን ላከው የነቢዩን ቃል እንመልከት፡

 

10 ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።

11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።

12 አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት አደርገዋለሁ። (2 ሳሙኤልl 12)

 

በዚያ ቀን ለዳዊት ቅጣቱ ሦስት እጥፍ ነበር በመጀመሪያ፣እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ጋር በቋሚነት እንደሚዋጋ ነገረው። ሁለተኛ፣በቤቱ ክፉ ነገር የሚያሥነሳበት ሲሆን በመጨረሻም፣እግዚአብሔር ሚስቶቹን ወስዶ በጠራራ ፀሐይ አብረዋቸው ለሚተኙ ለጎረቤቶቹ ይሰጣቸዋል

ከእነዚህ ምርጫዎች በኋላ የዳዊትን ሕይወት በምንመረምርበት ጊዜ የናታን ትንቢት ተፈጽሞ እናያለን ዳዊት ከእስራኤል ጠላቶች ጋር በመዋጋቱ ምክንያት በእጆቹ ላይ ብዙ ደም ያለው ንጉሥ ሆነ በእርግጥ፣ዳዊት ቤተመቅደሱን የመገንባት ታላቅ ህልም በእጆቹ ላይ ባለው ደም ምክንያት ሊያጣ ችሏል ዳዊት ወደ ህይወቱ ፍፃሜ ሲመጣ ስለ ቤተመቅደስ ግንባታ ያለውን ራዕይ ለልጁ ሰለሞን አካፍሏል1ኛ ዜና 22 ውስጥ ከልጁ ጋር የተጋራውን ቃል ያዳምጡ፡

7 አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ ይጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበረ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር እግዚአብሔር የአክዓብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሜሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።

8 ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድን ሲፈጽም የይሁዳን መሳፍንትና አካዝያስን ያገለግሉ የነበሩትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው። (1 ዜና 22)

ዳዊት የቤተመቅደሱን ግንባታ በጭራሽ አላየም ዳዊት ከጎረቤቱ ሚስት ጋር ለመተኛት የወሰነው ውሳኔ በሕይወቱ ውስጥ ካሉት ታላላቅ ራዕዮች መካከል አንዱን መሥዋዕት እንዲያደርግ ግድ ሆነበት

ከዚህ ባሻገር ግን ከቤርሳቤህ ጋር ከነበረው ግንኙነት በኋላ የዳዊት ሕይወት ተመሳሳይ አልሆነም ቤተሰቦቹ በችግር የተተበተቡ ነበሩ በዳዊት እና ቤርሳቤህ መካከል በነበረው ያልተገባ ግንኙነት ምክንያት የተወለደው ልጅ ሞተ (2 ሳሙኤል 12:15-18) የዳዊት ልጅ አምኖን በወንድሙ አቤሴሎም እህት ትዕማር በመሳብ አስገድዶ አስነወራት (2 ሳሙኤል 13) የትዕማር ወንድም አቤሴሎም በእህቱ መደፈር ምክንያት ወንድሙን አምኖንን ገደለው በዚህ ግድያ ምክንያት አቤሴሎም ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲሸሽ ተገደደ ከዓመታት በኋላ አቤሴሎም አባቱ ፈጽሞ ይቅር እንዳላለው ስለተሰማው አቤሴሎም አባቱን ዳዊትን ይጠላው ነበር ይህ ጥላቻ በጣም የበረታ ከመሆኑ የተነሳ አቤሴሎም ንጉስን ለመገልበጥ አሴረ እንደበቀል አቤሴሎም በቤተመንግሥቱ ጣሪያ ላይ ድንኳን ተክሎ ከአባቱ ቁባቶች ጋር ተኛ (2 ሳሙኤል 1620-23)

ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ለመተኛት የመረጠው ምርጫ በራሱ እና በቤተሰቡ ላይ አስከፊ መዘዞች አስከትሏል እርሱና ቤተሰቡ ዳግመኛ የቀድሞ ሕይወታቸውን መምራት አልቻሉም

በሐዋርያት ሥራ 4 የእግዚአብሔር መንፈስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ እናነባለን በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር መንፈስ ሥራ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች ያላቸውን ሁሉ ይካፍሉ ነበር የሐዋርያት ሥራ 4 በመካከላቸው ምንም ችግረኛ ሰው እንዳልነበረ ይነግረናል:

34 በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥

35 በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር። (ሐዋ 4)

 

ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ሥራ በዚያን ዘመን ይኖሩ የነበሩ አማኞች መሬታቸውን እና ቤቶቻቸውን እስከመሸጥ እና የተገኘውን ገቢ ወደ ሐዋርያቱ በማምጣት ለችግረኞች ያከፋፍሉ ዘንድ ያነሳሳቸው ነበር የእግዚአብሔር መንፈስ መሬታቸውን ይሸጡ ዘንድ ካነሳሳቸው ከእነዚያ ቀደምት አማኞች መካከል ሐናንያ እና ሰጲራ ይገኙበታል ይህን ታሪክ በሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ እናነባለን

ከሸጡ በኋላ የገቢውን እኩሌታ ክፍል ለራሳቸው ደበቁ ይህ ድርጊት ፍጹም ህጋዊ ነበር እነዚህን አማኞች ሁሉንም እንዲሰጡ ማንም አላስገደዳቸውም ነበር ችግሩ ግን ባልና ሚስቱ በልባቸው የወሰኑት ውሳኔ ነበር የሽያጩን ሙሉ ዋጋ እንደሰጡ አድርገው ቤተክርስቲያንን ለማታለል ወሰኑ የእምነት አጋሮቻቸው ከሽያጩ ዋጋ ግማሹን ብቻ ለቤተክርስቲያን ሰጥተው ሳለ ሁሉንም ነገር የሰጡ አድርገው  እንዲያስቡ ፈለጉ

ይህ ባልና ሚስት አንድ ላይ የወሰዱት ውሳኔ ነበር ገንዘባቸውን ወደ ሐዋርያት ሲያመጡ መንፈስ ቅዱስ ለጴጥሮስ እውነቱን ገለጸለት በቤተክርስቲያን ላይ ለመዋሸት ስለ ወሰደው ውሳኔ ሐናንያን ጠየቀው በዚህ ውሸት ምክንያት ሐናንያ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመቶ ሞተ

ከሦስት ሰዓታት በኋላ ሚስቱ በባሏ ላይ የሆነውን ሳታውቅ ገባች በተሰጠው መጠን ንብረታቸውን እንደ ሸጡት ጴጥሮስ ጠየቃት እርሷም ስለ እሱ መዋሸትን በምትመርጥበት ጊዜ እሷም ተመትታ ከባሏ ጎን ተቀበረች (ሐዋ 5:7-10)

ሐናንያ እና ሰጲራ ቤተክርስቲያንን ለማሳት ውሳኔ ላይ ደረሱ ያ ውሳኔ በነጻነት እና ሆን ተብሎ የተደረገ ነውየውሳኔያቸው ውጤቶች ግን ገዳይ ነበሩ በተሳሳተ ምርጫ ምክንያት ሁለቱም በጣም አሳዛኝ ሞት ሞቱ

የውሳኔዎቻችን መዘዞችን በተመለከተ አንድ ተጨማሪ ምሳሌ እንመልከትየዳንኤል መጽሐፍ እስራኤል በንጉሥ ናቡከደነፆር ዘመነ መንግሥት በስደት የኖረችበትን ዘመን ይገልጻል ናቡከደነፆር እጅግ በጣም ቅን የሆኑ የእስራኤል ወጣቶችን ለማሠልጠን ወስኖ በአገልግሎቱ ውስጥ እንዲመዘገቡ አደረገ ከእነዚህ ሰዎች መካከል ዳንኤል የሚባል አንድ ሰው ይገኝበታል

ለእነዚህ ወጣቶች ከሚሰጠው የሥልጠና መርሃ ግብር አካል የነበረ አንድ የተወሰነ ምግብ አይነት ነበር ይህ ምግብ ግን ከአይሁድ የምግብ ሕግ ጋር የሚቃረን ነበር ስለሆነም ምግቡን የሚበሉትን የአይሁድ ሰዎች የሚያረክስ ነበር ዳንኤል እንደ እውነተኛ የእምነት ሰው ወደዚህ ሥልጠና ሲገባ  አንድ ውሳኔ አደረገ

8 ዳንኤልም በንጉሡ መብልና በሚጠጣው ጠጅ እንዳይረክስ በልቡ አሰበ፤ እንዳይረክስም የጃንደረቦቹን አለቃ ለመነ። (ዳንኤል 1)

 

እግዚአብሔር በጃንደረባው አለቃ ፊት ለዳንኤል ሞገስን ሰጠው፤ዳንኤል አትክልትን ብቻ እንዲበላና ውሃ ብቻ እንዲጠጣ ፈቀደለት በዚህ የአመጋገብ ውስጥ የቆየው ዳንኤል ከአስር ቀናት በኋላ በንጉሱ አመጋገብ ውስጥ ከተካፈሉት ሁሉ የተሻለ ነበር ዳንኤል በዚህ ጉዳይ እግዚአብሔርን ለማክበር ወሰነ፤እግዚአብሔርም ሞገስ እና በረከት ሰጠው

ከጊዜ በኋላ ዳንኤል ዋጋውን በማረጋገጡ በሃገሩ መንግሥት ውስጥ ወደ ከፍተኛ  ክብር ደረጃ ከፍ አለ ይህም የአለቆች እና መሳፍንቱን ቅናት ቀሰቀሰ፤እነርሱም በእርሱ ላይ ጥፋት ለማግኘት እና ለማውረድ የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ወሰኑ እነዚህ ባለሥልጣናት ዳንኤልን ለመጉዳት ያገኙበት ብቸኛው መንገድ በእስራኤል አምላክ ላይ ካለው እምነት ጋር በተያያዘ ነበር ከንጉሱ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰው ቢለምን፥ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የንጉሥ ሕግና ብርቱ ትእዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማከሩ። ዳንኤል ይህንን በሰማ ጊዜ የሚያስከትለው መዘዝ ምንም ይሁን ምን መጸለዩን ለመቀጠል ወሰነ

አለቆቹ እና መሳፍንቱ ዳንኤልን ሕግ ጥሷል በሚል በከሰሱት ጊዜ ንጉሱ ወደ አንበሳ ጉድጓድ ዳንኤልን ሊወረውረው ተገደደ ዳንኤል ቅጣቱን ተቀብሎ ለአንበሶች ተላልፎ ተሰጠ እግዚአብሔር ግን ዳንኤልን ጠብቆ ሌሊቱን ሙሉ ደህና ሆኖ እንዲቆይ የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ ነበር

ንጉሱ በዳንኤል ላይ የሆነውን ለማየት ሄዶ አምላኩ እንደጠበቀው ባወቀ ጊዜ የሚከተለውን አዋጅ አወጣ

25 የዚያን ጊዜም ንጉሥ ዳርዮስ በምድር ሁሉ ላይ ወደሚኖሩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ ወደሚናገሩ ሁሉ ጻፈ፥ እንዲህም አለ፦ ሰላም ይብዛላችሁ።

26 በመንግሥቴ ግዛት ሁሉ ያሉ ሰዎች በዳንኤል አምላክ ፊት እንዲፈሩና እንዲንቀጠቀጡ አዝዣለሁ፤ እርሱ ሕያው አምላክ ለዘላለም የሚኖር ነውና፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፥ ግዛቱም እስከ መጨረሻ ድረስ ይኖራል።

27 ያድናል ይታደግማል፥ በሰማይና በምድርም ተአምራትንና ድንቅን ይሠራል፥ ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታል። (ዳንኤል 6)

 

ንጉሥ ዳርዮስ ሁሉም የምድር ሕዝቦችና ቋንቋዎች የዳንኤልን አምላክ እንዲያከብሩና እንዲፈሩ አዘዘ እርሱ እውነተኛና ሕያው አምላክ መሆኑን አሳወቀ ይህ እግዚአብሔርን ከማያውቅ ንጉስ አንደበት የተሰጠ የማይታመን መግለጫ ነበር በንጉሣዊ መንገዶች አማካኝነት የዳንኤል ምስክርነት እና የአምላኩ ኃይል ለንጉስ ዳርዮስ ግዛት ሁሉ ታወጀ  

ይህ አዋጅ እንዴት ታወጀ? በዳንኤል የተደረጉ የውሳኔዎች ውጤት ነበር በንጉሱ ምግብ ራሱን ላለማረከስ የሚደረግ ውሳኔ ለእስራኤል አምላክ እንጂ ለሌላ አምላክ ፈጽሞ አምልኮ ያለማቅረብ ውሳኔ ለአምላኩ እውነተኛ እና ታማኝ በመሆን ለሞት እንኳን የሚያደርስ አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ። እነዚያ ግላዊ ውሳኔዎች በመላው አገሪቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ቻሉ በእነዚህ ውሳኔዎች ምክንያት የእስራኤል አምላክ በመላው ዓለም እውነተኛ አምላክ ተብሎ ታውጀ

ጌታ እግዚአብሔር ፈጥሮናል እንዲሁም ውሳኔዎችን የማድረግ አቅም ሰጥቶናል የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን አቅጣጫ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ከዲያብሎስ ፈተና ፊት ለፊት እንደመቆማችሁ መጠን፣በሕይወታችሁ ላይ ለዘላለም ተጽዕኖ የሚያሳድር ምርጫ አላችሁ። ለፈተና እጅ ሰጥታችሁ በክፉ ጎዳና ትመላለሳላችሁ ወይንስ በፈተና ውስጥ በጽናት ትቆማላችሁ? ሕይወታችሁ የሚሄድበት አቅጣጫ በውሳኔአችሁ ይወሰናል ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ኃጢአት ከሠራ በኋላ ሕይወቱ ፈጽሞ ተመሳሳይ አልሆነም አንድ ታላቅ ቤተመቅደስ ለመስራት ያየው ራዕይ በዚያ ቀን ጠፋ ሐናንያ እና ሰጲራ በቤተክርስቲያን ላይ ለመዋሸት ከወሰኑ በኋላ ህይወታቸው በድንገት ቆመ ዳንኤል በታማኝነት የወሰናቸው ታማኝ ውሳኔዎቹ  ምንም እንኳን ከፍተኛ ሥቃይ ቢደርስበትም ለታላቅ በረከት መንገድ ነበሩ እግዚአብሔርን ለማክበር ያለው ቁርጠኝነት በተጽዕኖ እና በከፍታ የሥልጣን ቦታዎች ላይ አኖረው በሕይወቱና በምስክሩ ምክንያት የእስራኤል አምላክ ዝና ወደ መላው ዓለም ይናኝ ነበር

በህይወት ውስጥ ውሳኔ የማድረግ ችሎታ መኖሩ ትልቅ ክብር ነው በዚህ ታላቅ የምርጫ በረከት ጋር ትልቅ ኃላፊነት ተያይዞ ይመጣል። ትክክለኛ ውሳኔዎችን እናደርጋለን?

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር ዳዊትን ከቤርሳቤ ጋር ኃጢአት እንዳይሰራ ሊያስቆመው ችሏልን? እግዚአብሔር በኃጢአት እንዳትወድቅ የጠበቀህ ጊዜ አለን? እግዚአብሔር ኃጢአት እንዳትሠራ  ያስገድደናልን?

 

ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር በኃጢአት ከወደቀ በኋላ የኃጢአቱ ውጤቶች ምን ነበሩ?

 

የሐናኒያ እና ሰጲራ ውሳኔ ወደሞት መራቸው። በሕይወታችሁ በወሰናችሁት የተሳሳቱ ውሳኔዎች ምክንያት የደረሰባችሁን ችግሮችን አስተውሉ።

 

ትክክለኛ ውሳኔዎችን ወስነናል ማለት ችግሮች አይገጥሙንም ማለት ነውን? ዳንኤል የወሰናቸውን ውሳኔዎች ተመልከቱ። የእነዚህ ትክክለኛ ውሳኔዎች ውጤት ምን ነበሩ?

 

ለጸሎት፡

ጌታ መጥፎ ውሳኔዎችን እንዳንወስን እንደማያስገድደን እና በመጥፎ ውሳኔዎች ምክንያት ለሚመጡ ውጤቶች ሁሉ እርሱ ተጠያቂ እንዳልሆነ እንረዳ ዘንድ እንዲረዳን ጸልዩ።

 

በሕይወታችሁ ስለወሰናችሁት መጥፎ ውሳኔዎች እግዚአብሔር ይቅር እንዲላችሁ ጸልዩ።

 

እንደ ዳንኤል በሕይወታችሁ በምትወስኑት ውሳኔ ሁሉ እርሱን ታከብሩ ዘንድ ጌታ ምሪት እና ብርታት እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።

 


 

ምዕራፍ 5 - የምርጫ ጥሪ

 

መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ጌታ እግዚአብሔር የመምረጥ መብታችንን እንጠቀም ዘንድ ሲጠራን እንመለከታለን በሕይወት ውስጥ ከምናደርጋቸው በጣም አስፈላጊ ውሳኔዎች መካከል አንዱ ጌታን መከተል ወይም የራሳችንን እቅድ እና ሃሳብ መከተል ነው

በዘመኑ በነበሩ ሰዎች ፊት ቆሞ ኢያሱ የሚያገለግሉትን አምላክ እንዲመርጡ ይሞግታቸው ነበር፡

14 አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ።

15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። (ኢያሱ 24)

 

የእግዚአብሔር ህዝብ ውሳኔ መወሰን ያስፈልገው ነበር በጌታ ዓላማ ይራመዳሉ ወይንስ ሌላ አምላክ ይመርጣሉ? እንደ ኢያሱ ገለጻ እነርሱ የፈለጉትን ውሳኔ ለማድረግ ነጻ ነበሩ፣ዳሩ ግን የተሳሳተ ውሳኔ ማድረጉ የሚያስከትላቸው ውጤቶች አሉ

በዘዳግም 11 ውስጥ ሙሴ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለሕይወታቸው ሁለት አማራጮችን እያዘጋጀ መሆኑን ነገራቸው:

26እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤

27በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ፤

28 መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።

29 አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ። (ዘዳግም 11)

 

እግዚአብሔር በረከትንና መርገምን በእስራኤል ፊት አኖረ ህዝቡ የሚለማመደው  ነገር ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ የተመሠረተ ነው የጌታን ትዕዛዛት ለመታዘዝ ከመረጡ፣ይባረካሉ። አለመታዘዝን ከመረጡ የእርሱ እርግማን ያገኛቸዋል እዚህ ላይ ያለው አንድምታ የእስራኤል ህዝብ የሚመርጠው ምርጫ እንደነበረ ነው

ይህ ምርጫ በዘዳግም 30 ላይ ግልጽ ሆኖ ተቀምጧል፡

15 ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ።

16 በሕይወትም እንድትኖር እንድትባዛም፥ አምላክህም እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እንዲባርክህ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙንና ሥርዓቱን ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ።

17ልብህ ግን ቢስት አንተም ባትሰማ፥ ብትታለልም፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድ ብታመልካቸውም፥

18 ፈጽማችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን አታስረዝሙም።

19 በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤

20 እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ። (ዘዳግም 30)

   

እግዚአብሔር ህይወትን እና ሞትን (በረከት እና እርግማን) በሕዝቡ ፊት አኖሯል የሚሄዱበትን መንገድ ምርጫ ሰጣቸው ከዚያም ጌታ ውሳኔ እንዲያደርግ ሕዝቡን እንዴት እንደጠራ በቁጥር 19 ላይ ልብ ይበሉ ሕይወትን እንዲመርጡይማጸናቸዋል። እግዚአብሔር ለፈቃዱ ድርጊት ጥሪ እያደረገ ነው ህዝቡ እርሱን እንዲከተል እና በእነሱ ላይ ሊያዘንባቸው የፈለገውን በረከቶች ይለማመዱ ዘንድ ከልብ የመነጨ ውሳኔ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል ሆኖም ይህን ውሳኔ እንዲወስኑ አያስገድዳቸውም ከእግዚአብሔር ለመራቅ እና ላለመታዘዝ እንዲሁም የሞት ጎዳናን የመምረጥ ነፃነት ነበራቸው

መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን የሕይወት እና የበረከት መንገድ ባልመረጡ ወንዶችና ሴቶች ምሳሌዎች ተሞልቷል የምሳሌ ጸሐፊ የእግዚአብሔርን የጥበብ ጎዳና መቃወምን ስለመረጡ ሰዎች ሲናገር

28 የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።

29እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤

30 ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤

31 ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ። (ምሳሌ 1)

 

እዚህ ጋር ጸሐፊው  እግዚአብሔርን ለመፍራት እና በመንገዱ ለመሄድ ስላልመረጡ ሰዎች ይናገራል። የዚህ ውሳኔ ውጤት የመንገዳቸውን ፍሬ የሚበሉ ይሆናሉ የሚል ነው።

ይህ ተመሳሳይ ጥሪ ወደ አዲስ ኪዳን ይሄዳል። የወንጌሉ ጸሃፊ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ማብራሪያ ለምን እንደጻፈ ይነግረናል፡ 

30  ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤

31ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። (ዮሐንስ 20)

 

የኢየሱስን ሕይወት ታሪክ የሰሙ ሰዎች እንዲያምኑ እና በስሙ ሕይወት እንዲኖራቸው ዮሐንስ ወንጌሉን ጻፈው ማመን ማለት ምን ማለት ነው? እምነትን ሙሉ ክብደታችንን በአንድ ነገር ላይ እንደ ማስቀመጥ አድርጌ መግለጽ እፈልጋለሁ የሚያምን ሰው በሚያምነው ነገር ላይ ሙሉ እምነት ይጥላል እንጂ ከማመን ወደኋላ አይልም። በእምነት ውስጥ አንድ የምርጫ ክፍል አለ እምነታችንን በምንሰማው ላይ እናደርጋለን ወይንስ እንጠራጠራለን? ለቀረበልን እውነት እጅ እንሰጣለን ወይንስ አንቀበልም ብለን እንሄዳለን? ዮሐንስ ስለ ጌታ ኢየሱስ ሕይወት እና ሞት እውነታውን ለማቅረብ እና እያንዳንዱን አንባቢ ወደ ውሳኔ ስፍራ ለማምጣት ፈለጎ ነበር በእውነታዎች ላይ እምነትን ጥለው ሙሉ መተማመናቸውን በኢየሱስ ላይ ያደርጋሉ ወይንስ ከእሱ ይርቃሉ? ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥሪ አቅርቧል

የጌታ ኢየሱስ ማዕከላዊ መልዕክት ምን ነበር? ማርቆስ 1 የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረቡን እንደሰበከ እና ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ እና የምሥራቹን ወንጌል ይሰሙ ዘንድ እንዳስጠነቀቃቸው ይነግረናል፡

14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና፦ ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። (ማርቆስ 1)

ኢየሱስ ሊመጣ ያለው መሲህ እና በእርሱ እና በሥራው የሚያምኑ ሁሉ ከኃጢአታቸው እንደሚድኑ እና የዘለዓለም ሕይወትን እንደሚያገኙ ያስተምር ነበር። ኢየሱስ መሲህ መሆኑን በብዙ መንገዶች አሳይቷል። በዮሐንስ 14 ላይ ለህዝቡ ሲናገር እንዲህ ይላል፡  

10 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።

11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። (ዮሐንስ 14)

 

እዚህ ኢየሱስ እየተናገረ ያለውን አስተውሉ የተናገረው ቃል ከአብ መሆኑን ለአድማጮቹ እያስታወሰ ነው እርሱ ያደረጋቸው ተአምራዊ ሥራዎች እንዲሁ በእርሱ ውስጥ የአብ ሥራ ማስረጃዎች እንደነበሩ ይነግራቸው ነበር በመቀጠልም ቃላቱን የሰሙ እና ስራዎቹን ያዩትን የዚያን ዘመን ሰዎች በምላሹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይወስኑ ዘንድ ጥሪ አቅርቧል ለማመን ቁርጠኛ ውሳኔ እንዲያደርጉ አበረታቷቸዋል

11 ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር። (ዮሐንስ 14)

ኢየሱስ ውሳኔን ጠየቀእኔ ከአብ እንደሆንኩ ያምናሉ? በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ያደርጉ ዘንድ ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ ማስረጃዎች በዘመኑ ለነበሩ ሰዎች አቅርቧል እንደ ወንጌል ጸሐፊው እንደ ዮሐንስ ሁሉን እውነታውን አቅርቦ ለእምነት ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀርባል

በእስራኤል ሕዝብና  በበኣል ነቢያት ፊት ቆሞ ነብዩ ኤልያስ እነዚህን ቃላት ተናገረ

20 አክዓብም ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢያቱን ሁሉ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰበሰበ።

21 ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፦ እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በኣል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም። (1 ነገስት 18)

በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር ህዝብ የባዕድ የአህዛብ አምላክ የሆነውን በኣልን ለመከተል ተፈትነው ነበር ስለዚህ ኤልያስ ወቀሳቸው ከዚያም በፊቱ የቆሙትን ከሁለቱ አንዱን ይመርጡ ዘንድ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ጠራቸው እስከመቼ በሁለት የተለያዩ ሃሳቦች ታነክሳላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው እግዚአብሔር ውሳኔ እንዲወስኑ ይጠብቅ ነበር እርሱን ይከተላሉ ወይስ በኣልን ይከተላሉ? በመካከል መኖር አልቻሉምና

ማንን እንደምናገለግል መወሰን እንዳለብን ኢየሱስ በግልፅ ተናግሯል ሁለት ጌቶችን ማገልገል አንችልም አንዱን ወይም ሌላውን መምረጥ አለብን፡

24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። (ማቴዎስ 6)

ሐዋሪያው ያዕቆብ ሁለት ሃሳብ ያለው በመንገዱም ሁሉ እንደሚወላውል ይናገራል (ያዕቆብ 1:8) ። ሁለት ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች አለመወሰናቸውን እንዲሰብሩ እና ለእግዚአብሔር እንዲገዙ ይነግራቸዋል።

 

7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤

8 ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። (ያዕቆብ  4)

 

በሁለት ሃሳብ ማነከስ ሊወገድ የሚገባው ኃጢአት ነው በሁለት ሃሳብ የማነከስ ፈውስ ልንሄድበት ስለሚገባን አቅጣጫ ውሳኔ መወሰን ብቻ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ ያዕቆብ አንባቢዎቹን ለክርስቶስ እንዲገዙ እና ከማንኛውም ነገር ዞር እንዲሉ ያስጠነቅቃል

ኢየሱስ በራዕይ 3 ላይ በሁለት ሃሳብ ስለማነከስ ይናገራል፣እሱ በራድ ወይም ትኩስ ስላልሆነ ነገር ግንለብ ያለ ስለመሆን ይናገራል፡

15 በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።

16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። (ራዕይ 3)

 

ጌታ ኢየሱስ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ለብ ያሉ እንደነበሩ ይነግራቸው ነበር  በራድ ወይም ትኩስ ቢሆኑ ብሎ ይነግራቸዋል። በሌላ አገላለጽ እነሱ ውሳኔ ይወስኑ ዘንድ ይፈልጋል የእርሱ ናቸውን ወይንስ ከእርሱ ውጪ? እሱን ያገለግላሉ ወይንስ ይቃወሙታል? ይህ ለብ ማለት ቀዝቃዛ ከመሆን እጅግ የከፋ ነበር በቤተክርስቲያን ምስክርነት ላይ ትልቁ ጉዳት የሚደርሰው ለጌታ ለኢየሱስ እና ለቃሉ ጽኑ ቃልኪዳን ባላደረጉ ሰዎች ነው እነርሱ ክርስቲያን ነን ይላሉ ዳሩ ግን ዓለምን እና መንገዱን ይወዳሉ እነሱ በጌታ እና በዓለም መካከል ይወዛወዛሉ። ይህ እንደ ኢየሱስ አገላለጽ በእርሱ ዘንድ በጣም አስጸያፊ ስለነበረ እነዚህን አማኞች ከአፉ ይትፋቸዋል

ለብ ያለ መሆን፤በሁለት ሃሳብ ማነከስ እና አለመወሰን እንደ ቀላል ሊወሰዱ አይገባም እነዚህ በንስሃ ልንመለስባቸው የሚገባን ኃጢአቶች ናቸው ማንን እንደሚያገለግሉ መወሰን ስለማይችሉ ሰዎች ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡

 

23 ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። (ሉቃስ 11)

ከክርስቶስ ጋር ናችሁ ወይስ ከእሱ ውጪ ናችሁ? ውሳኔ በማይሰጥበት አጥር ላይ መቀመጥ አትችሉም ክርስቶስን ካልመረጣችሁ እና በእርሱ ላይ ሙሉ እምነታችሁን ካላደረጋችሁ ከእርሱ ውጪ ናችሁ። ሁለት ጌቶችን ማገልገል አትችሉም በሁለት ሃሳቦች መካከል ማነከስ አትችሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝነታችንን እንድንናገር ጥሪ ያደርግልናል፤በእርሱ እና በቃሉ ካፈርን በእኛ ላይ እንደሚያፍር ያስጠነቅቀናል፡

26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ በክብሩ በአባቱና በቅዱሳን መላእክቱ ክብርም ሲመጣ በእርሱ ያፍርበታል። (ሉቃስ 9)

የምንሄድበትን መንገድ ለመምረጥ ይህ ሁላችንም የቀረበ ጥሪ ነው። እግዚአብሔርን ለማገልገል ወይም ዓለምን እና መንገዱን ለመከተል መወሰን አለብን። ይህ እኛ በየዕለቱ ማድረግ የሚገባን ውሳኔ ነው። በመንገዳችን ላይ የሚመጣ እያንዳንዱ ሁኔታ እና ሙከራ ያንን ውሳኔ ይጠይቃል፤የታደሰ ቃልኪዳንን እንዲኖረን ጥሪ ያቀርባል። እርግጠኛ ልንሆን የሚገባን እያንዳንዳችን አንዱን መምረጥ አለብን የሚለው ነው።   ለብ ማለት እና በሁለት ሃሳብ ማነከስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አማራጭ አይደለም።

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር ለመምረጥ ነጻነት ይሰጠናልን?

 

እግዚአብሔር ስለ እኛ የሚያስበው ምንድ ነው? እግዚአብሔር ለእርሱ ፍጹም እንታዘዝ ዘንድ ለምን አያስገድደንም?

 

ዮሐንስ አንባቢዎቹ ያምኑ ዘንድ ወንጌሉን ጽፏል። ኢየሱስ ለሚያምኑት ወንጌልን ሰብኳል እንዲሁም ታዕምራትን ሰርቷል። ማስረጃቸውን እንዳንቀበል የሚያግደን ምንድ ነው?

 

ለብ ያለ እና በሁለት ሃሳብ የማነከስ ኃጢአት ምንድ ነው? ዛሬ ኃጢአት እንዴት የቤተክርስቲያንን ምስክርነት ያጠፋል?

 

ውሳኔ ላይ ሳንደርስ እና በሁለት ሃሳብ እያነከስን ኢየሱስን መከተል እንችላለን?

 

ለጸሎት:

ውሳኔ ላይ ባለመድረስ እና በሁለት ሃሳብ በማነከስ ስለሰራኸው ኃጢአት እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ጸልይ። ራስህን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ መስጠት ትችል ዘንድ ጸጋን እንዲሰጥህ ጸልይ።

 

ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ለክርስቶስ እና ለመንገዶቹ ያላስገዙ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ታውቃለህን? እርሱን ለመከተል ጽኑ መሰጠት ያደርጉ ዘንድ ትነግራቸው ዘንድ እንድትችል እግዚአብሔርን ጠይቅ

 


 

ምዕራፍ 6 - በምንመርጠው ምርጫ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሪት

 

እግዚአብሔር የመምረጥ ችሎታ ስለፈጠረልን አሁን ይህንን መብት እንድንጠቀምበት ይጠብቃል። ብዙ የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን እና በአካባቢያችን ባሉ ሰዎች ሕይወት ላይ አስደናቂ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። የሕይወታችን ቅርፅ እና ሁኔታ በአብዛኛው በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ላይ የተደገፈ ነው። ይህ አቅልለን ልንመለከተው የምንችለው ነገር አይደለም።

እኛ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ከመምረጥ ችሎታ ጋር የፈጠረን እግዚአብሔር እንዲሁ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ላይ እኛን ለመምራት ቃል ገብቷል። በዚህ ጉዳይ ለራሳችን አልተወንም። እግዚአብሔር በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ውስጥ እኛን ከሚመራባቸው የመጀመሪያዎቹ መንገዶች አንዱ ቃሉን በጽሑፍ መልክ በማቅረብ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን መጻሕፍት የተናገረውን ያዳምጡ:

16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። (2 ጢሞቴዎስ 3)

ሐዋርያው ስለ ቅዱሳን መጻሕፍት ለጢሞቴዎስ የነገረውን አስተውሉ። ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ከመሆናቸውም በላይ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ለመውቀስ ይጠቅማሉ። የእግዚአብሔር ቃል የተሰጠን እግዚአብሔር እናከናውነው ዘንድ ለጠራን ስራ እንድንታጠቅ ነው። በሌላ አገላለጽ እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ እንዴት እንድንኖር እና እሱን ማገልገል እንችል ዘንድ ለማሳየት ቃሉን ሰጥቶናል። የሕይወት እና እምነት መመሪያ መጽሐፍ ነውና።

 

እንዴት እንደምንኖር ለማወቅ ከፈለግን ቅዱሳን መጻሕፍትን መመርመር ያስፈልገናል። እውነትን ማወቅ ከፈለግን በእግዚአብሔር በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው ቃል የሚነግረንን ማጥናት ያስፈልገናል። የእግዚአብሔር ቃል ውሳኔዎቻችን ሁሉ የሚደረግበትን መሠረት የሚጥል ነውና።

በመዝሙር 73 ላይ የሰፈረውን የዘማሪውን ቃል እንመልከት፡

24 በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ። (መዝሙር 73)

ዘማሪው ምርጫዎቹን ሁሉ ያለ ጌታ እግዚአብሔር ምክር እና መመሪያ መምረጥ እንደሌለበት በማወቁ ምክንያት ታላቅ እረፍት አግኝቷል። በሕይወቱ ውስጥ እያንዳንዱን ውሳኔ ሲወስን ጌታ በመረጣቸው ምርጫዎች እንደመራው ማረጋገጫ ነበረው።

በመረጥናቸው ምርጫዎች ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል መመሪያ መዝሙር 119 በኃይል ይናገራል። መዝሙሩ የሚጀምረው በእነዚህ ቃላት ነው፡

[119:1] በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው! (መዝሙር 119)

ዘማሪው በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ የተባረኩ እንደሆኑ መናገሩን አስተውሉ። በሁለተኛው ቁጥር አጋማሽ ላይ ይህ ንጹሕ የሆነ ሕይወት እንዴት ሊሳካ እንደቻለ ያስረዳል። በጌታ ሕግ የሚመላለሱ ያለ ነቀፋ ይሄዳሉና። በሌላ አገላለጽ፣እንዴት መመላለስ እንዳለብን ለማወቅ ከፈለግን ቅዱሳን ጽሑፎችን ማጥናት ያስፈልገናል። ጌታን በሚያስደስት እና በረከትን በሚያስገኝ መንገድ እንዴት እንድንኖር የእግዚአብሔር ቃል መመሪያችን ነው። ዓይናችንን በእግዚአብሔር ትዕዛዛት ላይ ስናደርግ ብቻ ነውር በሌለበት ሕይወት መመላለስ እንችላለን፡

6 ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም። (መዝሙር  119)

በመዝሙረ ዳዊት 119:9 ላይ ዘማሪውጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል?የሚለውን ጥያቄ ይጠይቃል፤በሌላ አገላለጽ አንድ ወጣት ወንድ ወይም ሴት በሕይወት ውስጥ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? ምላሹን ያስተውሉ፡

 

9 ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።

10 በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።

11 አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። (መዝሙር 119)

 

በህይወት ውስጥ ትክክለኛ ውሳኔዎችን የማድረግ መንገድ ህይወታችንን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመኖር ነው። አንድ ወጣት ወንድ ወይም ሴት ለሚወስኑት ውሳኔዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ሊጥልላቸው ያስፈልጋል። ያ የተሳካ እንዲሆን እነዚህ ወጣት ወንድ ወይም ሴት ልጆች ልባቸው በእግዚአብሔር ቃል መሞላት አለበት።

በእግዚአብሔር ቃል መሞላት ማለት ምን ማለት ነው? ይህም የእግዚአብሔር ቃልን መርሆዎች ማንበብ፣ማጥናት እና መማርን ያመለክታል። የእግዚአብሔር ቃል የሕይወታችን አካል መሆን ያስፈልገዋል። በተለያዩ የሕይወት አጋጣሚዎች መካከል የመወሰን አስፈላጊነት ሲገጥመን እግዚአብሔር በሕይወታችን ላይ ያለውን ዓላማ ተረድተን በዚያው መሠረት እንድንመላለስ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ወደ ልባችን እና ወደ አዕምሮአችን በጥልቀት እንዲገባ መፍቀድ አለብን። በህይወት ውስጥ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ማድረግ አልቻላችሁም ማለት መጽሐፍ ቅዱስን እያነበባችሁ እና እያጠናችሁ አይደለም ማለት ነው። ኃጢአት እንዳንሠራ ልባችን በእግዚአብሔር ቃል  መሞላት አለበት። በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መመሪያችን ነውና።

ዘማሪው በየቀኑ በሚያደርጋቸው ውሳኔዎች እና ምርጫዎች ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል አስፈላጊነትን ተረድቷል። በእርግጥ እርሱ የእግዚአብሔርን ቃል ለእግሮቹ መብራት አድርጎ ገልጾታል።

105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።

106 የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም። (መዝሙር 119)

 

በጨለማ ውስጥ ሄደው ያውቃሉን? ወዴት እንደምንሄድ ማየት ባልቻልን ጊዜ አንድ ነገርን የመርገጥ ወይም በመንገዳችን ላይ ተሰናክለን የመውደቅ አደጋ ይገጥመናል። ዘማሪው በሕይወት ጎዳና ላይ ለእግሮቹ መብራት ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል ተመለከተ። ቃሉ ሊወገዱ የሚገባቸውን መሰናክሎች እና ኃጢአቶች ገለጠለት። እንዴት መኖር እና ህይወቱን መምራት እንዳለበት የሚረዳውን መርሆዎች አሳየው። በእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች በመመላለስ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ማድረግ ችሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ውስጥ እንደሚመላለስ እና በየቀኑ በሚያደርጋቸው ውሳኔዎች የእርሱ መመሪያ ይሆን ዘንድ ቃል በመግባት ለራሱ ማለ።

ዘማሪው በሕይወቱ ውስጥ ያደረጋቸው ውሳኔዎች ሁልጊዜ ትክክል አልነበሩም። በእርግጥ፣በመዝሙረ ዳዊት 11967 ላይ እንዴት እንደተሳሳተ ይናገራል።

67 እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።

68 አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ። (መዝሙር 119)

ዘማሪው በተሳሳተ ጊዜ ተመልሶ መንገዱን ያገኘው እንዴት እንደሆነ አስተውሉ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁይላልበሌላ አገላለጽ የእግዚአብሔርን ቃል ሲመለከትና የእርሱ መመሪያ እንዲሆን ሲፈቅድለት ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመለስበትን መንገድ አገኘ። እርሱ በጽድቅ ጎዳና ላይ እንዲቆይ እና የጌታን በረከት መለማመድ ይችል ዘንድ ቃሉን እንዲያስተምረው በሚቀጥለው ቁጥር እግዚአብሔርን ይጠይቃል።

ኢየሱስ በዮሐንስ 17 ላይ ለደቀመዛሙርቱ የጸለየውን ጸሎት ተመልከቱ፤

13 አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።

14እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።

15 ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።

16 እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።

17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። (ዮሐንስ 17)

ጌታ ኢየሱስ ወደ አባቱ ለመመለስ ሲዘጋጅ ቃሉን እንደተወላቸው ለአብ ተናግሯል።    ያ ቃል ዓለም እንዲጠላቸው አድርጓቸዋል። ዓለምን በማይመስል ኑሮ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ምሪትን ሰጥቷቸዋል። እነዚህ ደቀመዛሙርት ኢየሱስ የተወውን የቃሉን ትምህርት በመከተል በጨለማ ውስጥ እንደ ብርሃን ነበሩ። እነሱ የትውልዶቻቸውን ኃጢአት እና ክፋት ተጋፍጠው በእሱም ምክንያት የተጠሉ ሆኑ።

ኢየሱስ አብ ደቀመዛሙርቱን በእውነት እንዲቀድሳቸው እንዴት እንደጸለየ በቁጥር 17 ላይ ቃልህ እውነት ነውበማለት የተናገረውን ቃል አስተውሉ። እዚህ ጋር ኢየሱስ እየጸለየ የነበረው ምንድን ነው? ደቀመዛሙርቱ ትቶላቸው የሄደውን ቃል ተጠቅመውበት ቅዱስ ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሔር አብን እየጠየቀ ነበር። ለደቀመዛሙርቱ ትቶላቸው የሄደውን እውነት ለማመን እና በእርሱ ለመመላላስ ሲመረጡ ይወስኗቸው በነበሩ ውሳኔዎች እንዲመራቸው እና ህይወታቸውን እንዲለውጥ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ወደዘረጋልን መንገድ የሚመራን የእግዚአብሔር መንገድ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ለህይወት እና ለእምነት መመሪያችን ነው።                 ምን እንደምናምን ለማወቅ ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ያስፈልገናል። በሕይወት ውስጥ ትክክለኛውን ምርጫ እንዴት ማድረግ እንደምንችል ለማወቅ ከፈለግን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ማሰላሰል አለብን።

እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ የምርጫ መብት ሰጥቶናል።፡ ይህ መብት እጅግ ከባድ የሆነ የኃላፊነት ሸክም ይዞ ይመጣል። የተሳሳቱ ውሳኔዎች አስከፊ መዘዞች ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለዚህም ነው ጌታ በተአምራት ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠብቆ ያቆየን። ይህ ቃል በትምህርት እና መመሪያ የተሞላ ነው። ቃሉ ከእኛ በፊት ስለሄዱ ወንዶች እና ሴቶች ታሪኮች ይናገራል። ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል የተወሰኑት መጥፎ ውሳኔዎችን ወስነዋል። የእነዚህን ውሳኔዎች ውጤት በታሪኮቻቸው ውስጥ እናያለን። በሕይወታችን በምናደርጋቸው ውሳኔዎች እና ምርጫዎች ውስጥ ምሪት እንዲሰጠን እግዚአብሔር ዛሬ ያስተላለፈልን ቅዱሳን መጻሕፍት ለእኛ ተሰጡን።

እግዚአብሔር አንዳንድ መመሪያዎችን፣ምሳሌዎችን እና ትምህርቶችን ሳይሰጠን እንድንመርጥ አይተወንም። ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለማድረግ ከፈለግን በእግዚአብሔር ቃል መመራት አለብን።

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር ቃሉን ለምን ሰጠን?

 

ያለ እግዚአብሔር ቃል ትክክለኛ የሆነ ውሳኔ መወሰን እንችላለን?

 

በመደበኛ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ እና ማጥናት የሳምንቱ የኑሯችሁ አካል ነው? የእግዚአብሔርን ቃል ለእውቀት ማጥናት እና በኑሮ ላይ ተግባራው ለማድረግ ማጥናት ልዩነቱ ምንድ ነው?

 

ለጸሎት:

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ዓላማ በመያዙ ጌታን አመስግን። በምንወስናቸው ውሳኔዎች ብልሆች እንሆን ዘንድ ስለሚረዱን የእምነት ወንዶች እና ሴቶች የሕይወት ትምህርቶች እና መመሪያዎች እግዚአብሔርን አመስግን።

 

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማወቅ እና ለማጥናት ጥልቅ የሆነ መሻት ጌታ እንዲሰጥህ ጸልይ

 

እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ከተቀመጠው የእርሱ ዓላማ ጋር የሚጻረር ውሳኔ ለወሰንክባቸው ጊዜያት ይቅር እንዲልህ ጸልይ 


 

 

ምዕራፍ 7 - የመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና ውሳኔዎቻችን

 

ውሳኔዎቻችንን ብቻችንን እንድናደርግ ጌታ አይተወንም። እንዴት እንደምንኖር መመሪያ ይኖረን ዘንድ ቃሉን በጽሑፍ እንዳስቀመጠልን በመጨረሻው ምዕራፍ ውስጥ ተመልክተናል። ለዚህ ቃል በመታዘዝ የሚመላለሱ ቢሆኑም በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መካከል በመምረጥ ረገድ በጣም አስቸጋሪ በሚሆንባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ራሳቸውን ያገኛሉ።

ወጣት ሳለሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በነበረኝ ቆይታ በሕይወቴ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ውሳኔ ገጠሞኝ ነበር። የሙሉ ጊዜ አገልጋይ እንድሆን የእግዚአብሔር ጥሪ እንደሆነ ተሰምቶኝ ነበር ሆኖም ግን ያ ምን ማለት እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም ነበር። የእግዚአብሔር ቃል የእርሱ አገልጋይ እሆን ዘንድ እንደጠራኝ አውቅ ነበር፣ነገር ግን በዚያ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አገልግሎቴ ምን እንደሚሆን ወይም ያንን አገልግሎት እንዴት መጠቀም እንዳለብኝ የሚነግረኝ ቦታ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መርሆዎችን ይሰጠናል፣ዳሩ ግን ብዙውን ጊዜ ለተለዩ ዝርዝር ጉዳዮች የበለጠ መሪት ያስፈልገናል።

በሞሪሺየስ እና ሪዩኒዮን ደሴቶች ላይ ጌታ ሚስዮናዊ እሆን ዘንድ እንዴት እንደመራኝ በዚህ ጥናት ውስጥ በዝርዝር ለመሄድ ጊዜ የለኝም። ውሳኔው በምክንያታዊነት የወሰንኩት እንዳልሆነ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥዌይኒ ወደ ሞሪሺየስ ሂድየሚል አንድ ምዕራፍ እና ቁጥር አልነበረም ማለት ይበቃል። እኔ ማለት የምችለው ግን ጌታ ያንን ውሳኔ ምሪት ሰጥቶት ነበር እናም የምወስደው መንገድ ይህ መሆኑን ግልፅ አድርጎት ነበር።  

በአማኙ ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ምስጢራዊ ነው ነገር ግን እግዚአብሔር የሚመራን በተጻፈው ቃሉ ብቻ ሳይሆን በመንፈሱ መሪት እና አነሳሽነትም እንደሆነ ጥርጥር የለውም። በሐዋርያት ሥራ 16 ላይ ጌታ ሐዋርያትን የመራበትን መንገድ ተመልከቱ።

 

6 በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤

7 በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤

8 በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።

9 ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።

10 ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።  (ሐዋ  16)

 

ሐዋርያቱ ወደ እስያ ለመሄድ ሲሞክሩበመንፈስ ቅዱስ ተከልክለውነበር። ይህንን በመረዳት ወደ ቢታኒያ ክልል አቅጣጫቸውን ቀይረው እንደገና ለመሄድ ሲነሱ የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም በመጨረሻም አንድ ምሽት ላይ ጳውሎስ ከመቄዶንያ የሚጣራ አንድ ሰው በራዕይ አየ። በውጤቱምወንጌልን እንዲሰብኩላቸው እግዚአብሔር እንደጠራቸውድምዳሜ ላይ ደረሰ።

በእነዚያ ቀናት የተደረጉት ውሳኔዎች በእውነቱ በሐዋርያት የቃሉ ጥናት የተቀረጹ ነበሩ ነገር ግን ከዚያ እጅግ የላቀ ነበር። የእግዚአብሔርን ቃል በሚያጠኑበት ጊዜ ወደ መቄዶንያ እንዲሄዱ የነገራቸው ነገር አልነበረም። ዳሩ ግን ከቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔርን ሥራ እና መሪነት ተረድተዋል። ይህ መረዳት በወሰዱት አቅጣጫ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት አዕምሯቸውን ከፈተላቸው።  መንፈስ ቅዱስ፣ደቀመዛሙርቱን መርቶ እንዲሄዱበት የፈለገውን መንገድ አሳያቸው።

ወንጌላዊው ፊሊጶስም በሰማርያ ሳለ ይህንን የጌታን መሪት ተለማምዶ ነበር። በዚህ ጊዜ ጌታ ድንቅ ነገሮችን ያደርግ ነበር። ፊሊጶስ በሚሰብክበት ክልል ውስጥ መነቃቃት በኃይል ወጥቶ ነበር። በዚህ መነቃቃት ከፍታ ላይ ነበር፣ ሆኖም ግን ጌታ ፊሊጶስን ተናግሮት ወደ በረሃው መራው። የሐዋርያት ሥራ 8 ይህንን ታሪክ ይተርካል።

 

 

26 የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው።

27 ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

28 ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር።

29 መንፈስም ፊልጶስን፦ ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው።

30 ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና፦ በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን? አለው።

31 እርሱም፦ የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል? አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። (ሐዋ 8)

 

በፊሊጶስ ሕይወት ውስጥ የጌታን መሪት አስተውሉ። ሰማርያን ለቆ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ እንዲሄድ የነገረውየእግዚአብሔር መልአክነበር። ፊሊጶስን ያገኘው መረጃ ሁሉ ያ ነበር። በዚያ መንገድ ወደ ጋዛ መጓዝ ነበረበት። ሲደርስ በዚያው ጎዳና ላይ አንድ ሠረገላ ሲጓዝ አየ። የእግዚአብሔር መንፈስ ፊሊጶስንወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ።ያለው በዚያን ጊዜ ነበር። ፊሊጶስ የመንፈስን ምሪት በመታዘዝ ኢትዮጵያዊውን ባለሥልጣን ወደ ጌታ የመምራት ዕድል አግኝቷል።

ፊሊጶስም ይህንን መመሪያ የተቀበለው የሙሴን ሕግ በማንበብ ወይም ከሐዋርያት ከሰማው ወንጌል አልነበረም። እርሱ ያደረጋቸው ውሳኔዎች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ባለው የእግዚአብሔር መንፈስ የተወሰነ አመራር ላይ የተመሰረቱ ነበሩ።

ጌታ መሄድ በሚገባን መንገድ እንሄድ ዘንድ ሊመራን ቃል ገብቷል። ዘማሪው በሚጽፍ ጊዜ ይህን ተረድቷል፡

8 አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።

9 ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። (መዝሙር 32)

 

ከመዝሙር 32:8-9 መረዳት የሚያስፈልገን ነገር ጌታ እንደሚመራን አውቀን ኃላፊነት መቀበል አለብን። በተወሰነ የመንገድ አቅጣጫ እንዲሄድ ለማስገደድ ትንሽ ልጓም እንደሚያስፈልገው እንደ ግትር በቅሎ ወይም ፈረስ መሆን የለብንም። ይልቅ በፈቃደኝነት እና በታዛዥነት የጌታን መሪነት መምረጥ አለብን።

ጌታ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ሲናገር እንደህ በማለት ለሕዝቡ ቃል ገብቷል፡

20 ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥

21 ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ። (ኢሳይያስ  30)

 

ጌታ በኢሳይያስ በኩል በሚሄዱበት መንገድ እንደሚያስተምራቸው የተስፋ ቃልን ሰጥቷል። ጌታመንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ ብሎ ሲናገር ይሰሙ ነበር።

በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ስላለው የእግዚአብሔር ምሪት የሚያስተምሩ ብዙ ተጨማሪ ምሳሌዎች ይገኛሉ። በእርግጥ፣ጌታ ህዝቡን በቃሉ መርቶ ነበር፣ዳሩ ግን በሕይወታቸው  በመንፈሱ እና ምሪት በመስጠት እንዲሁ መራቸው።

ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ለመሆን ከመሄዱ በፊት ለደቀመዛሙርቱ እነዚህን ቃላት ተናግሮ ነበር፡

7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

9-10 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤

11 ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።

12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።

13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

14እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።

15 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ። (ዮሐንስ 16)

 

ጌታ ኢየሱስ ወደ አባቱ በተመለሰበት ቀን ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ነግሯቸው ነበር። በዚህ ወቅት ደቀመዛሙርቱ ሕይወታቸው በጌታ በኢየሱስ ምክር እና ትምህርት ላይ በጣም ጥገኛ ነበር። እርሱ በአካል ከጎናቸው ሳይሆን ሕይወትን መምራት ለእነርሱ የሚታሰብ አልነበረም። የእርሱን ጥበብ በየቀኑ ይፈልጉ ነበር። የኢየሱስ ቃላት በዚያ ቀን ለደቀመዛሙርቱ መጽናኛ ነበሩ።                            እሱ ብቻቸውን እንዲሆኑ አይተዋቸውም። ረዳት ይልክላቸዋልና።

ጌታ መንፈስ ቅዱስ ይሰራል ያለውን አስተውሉ። በመጀመሪያ፣መንፈስ ቅዱስ የሰዎችን ዓይኖች ለኃጢአት ይከፍትና ስለ መጪው ፍርድ ጥልቅ ግንዛቤን ይሰጣቸዋል (ቁጥር 8-11) ። በሁለተኛ ደረጃ፣የእግዚአብሔርን ህዝብ የእግዚአብሔርን እውነት እንዲረዱ ይመራቸዋል (ቁጥር 1213) ። ሦስተኛ፣እንዴት በሕይወታቸው እንደሚኖሩ ገልጦ ለጌታ ኢየሱስ ስም ክብር የሚያመጡ ውሳኔዎችን ይወስናል (ቁጥር 14) ። በመጨረሻም፣እርሱ ለሚሰሙት የጌታ ኢየሱስን ፈቃድ እና ዓላማ ይነግራቸዋል (ቁጥር 15)

ከመምረጥ ነፃነት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ታላቅ ኃላፊነት ስናስብ፣እነዚያን ውሳኔዎች ለመወሰን ብቻችንን አለመሆናችን ለእኛ ጥልቅ መጽናኛ ነው። ምን ማመን እንዳለብን እና እንዴት መኖር እንደሚገባን የሚመራን የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል አለን።                 ቃሉ በሕይወታችን በተግባር እንዲሰራ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል።

ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለማድረግ ከፈለግን የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ብቻ ትጉዎች መሆን የለብንም፤ነገር ግን አስተማሪያችን እና መሪያችን ሆኖ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን መንፈስ ምክር እና ትምህርት ለመስማት ጆሯችንን ለማዳመጥ ማዘጋጀት አለብን።

 

ለግንዛቤ:

መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን እንዴት እንደመራ የሚያሳይ ምሳሌዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቀስ። የዚህ አይነት ምሪት በህይወትህ ታውቃለህን? አብራራ

 

 

የእግዚአብሔር ቃል እንዴት መመላላስ እና ምን ማመን እንዳለብን ግልጽ አድርጎ ቢያስቀምጥም፤በህይወታችን ለምንወስናቸው እያንዳንዱ ውሳኔ የሚናገር ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛልን?

 

የመንፈስ ቅዱስ ሚና ምንድ ነው? ከእግዚአብሔር ቃል መርዎች በተጻረረ መንገድ ይመራናልን?

 

በምንወስናቸው ውሳኔዎች ወስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስን ምሪት እና ምክር ጥልቅ የሆነ እውቀት እንዴት ሊኖረን ይችላል?

 

ለጸሎት:

በምንወስናቸው ውሳኔዎች ሁሉ መሪያችን እና አስተማሪያችን ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ስለሰጠን እግዚአብሔርን አመስግን

 

በሕይወትህ ለመንፈስ ቅዱስ ሚና እና ሕልውና እውቀት ይኖርህ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ጸልይ። ለምሪቱ ጥልቅ የሆነ መረዳት እንዲሰጥህ ጸልይ።

 

ተግሳጹን ባለመስማት እና ለምሪቱ ባለመታዘዝ መንፈስ ቅዱስን ላሳዘንክባቸው ጊዜያት ጌታ ይቅር እንዲልህ ጸልይ


 

ምዕራፍ 8 - እግዚአብሔርን የሚፈሩ አማኖች ምክር

 

እንደ አማኞች የመምረጥ መብታችንን አዘውትረን እንድንጠቀም ተጠርተናል። በምንሄድበት መንገድ እንዲያስተምረን እና እንዲመክረን መጽሐፍ ቅዱስን እና መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንደሰጠን አይተናል። በህይወት ውስጥ ልንወስዳቸው በሚገቡ ውሳኔዎች ውስጥ እግዚአብሔር የሰጠን ሌላ ድጋፍ አለ። ያ ድጋፍ የሚመጣው በዙሪያችን ባሉ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ወንዶችና ሴቶች መልክ ነው።

በብሉይ ኪዳን እጅግ ጥበበኛ ሰው የነበረው ሰለሞን ብዙውን ጊዜ ስለ ጥበባዊ ምክር አስፈላጊነት ይናገር ነበር።

5 ጠቢብ ሰው ብርቱ ነው፥ አዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል።

6 በመልካም ሥርዓት ሰልፍ ታደርጋለህ፤ ድልም ብዙ ምክር ባለበት ዘንድ ነው። (ምሳሌ 24)

 

14 መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል። (ምሳሌ 11)

 

22 ምክር ከሌለች ዘንድ የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፤ መካሮች በበዙበት ዘንድ ግን ይጸናል። (ምሳሌ 15)

 

ሰሎሞን እዚህ ጋር አስፈላጊ ነጥቦችን አስቀምጧል። ያለ እግዚአብሔር ምክር ሰዎች እና ምክራቸው እንደሚወድቅ የነገረንን አስተውሉ። ሰሎሞን ስለዚህ ጉዳይ በጣም ስለተሰማው የሚከተለውን ደግሞ ያክላል፡   

12 ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኸውን? ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው። (ምሳሌ 26)

 

በሌላ አነጋገር፣እናንተ የራሳችሁን ውሳኔ ለማድረግ ያለ ሌሎች ምክር እና ሃሳብ በራሳችሁ ብቻ ጥበበኛ እንደሆናችሁ የምታስቡ ከሆነ እጅግ የከፋ ሞኝ ናችሁ ሰሎሞን በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል ይላል (ምሳሌ 1114) መካሮች ብዛትሲኖሩን እቅዶቻችን ይሳካሉ (ምሳሌ 15:22)ከብዙ አማካሪዎችጋር ድል አለ (ምሳሌ 24:6)

የሰሎሞን ምክር ትክክለኛውን ውሳኔ ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በአካባቢው ያሉትን ጥበበኛ እና አስተዋይ ሰዎች ምክር መጠየቅ አለበት የሚል ነው ትዕቢት ይህንን ምክር ከመፈለግ ያርቀናል ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን የሚፈልግ ብልህ ሰው ውሳኔውን ከማድረጉ በፊት ሌሎችን ለማማከር በጭራሽ ወደ ኋላ አይልም

የሚሰጥ ምክር ሁሉ መልካም ምክር እንዳልሆነ እዚህ ላይ ልብ ሊባል ይገባል የሰለሞን ልጅ ሮብዓም የዚህ አይነት መክር ተመክሮ ነበር የእስራኤል ህዝብ አዲስ ወደተሾመው ንጉስ ሮብዓም ቀርበው አባቱ የጫኑባቸውን ሸክም እንዲያቀልላቸው ጠየቁት ለህዝቡ መልስ ከመስጠቱ በፊት ሮብዓም የሰለሞንን አማካሪዎች ምክር ጠየቀ

6 ንጉሡም ሮብዓም፦ ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።

7 እነርሱም፦ ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት። (1 ነገስት 12)

እነዚህ ብልህ የሆኑ ሽማግሌ አማካሪዎች ሮብዓምን አባቱ በህዝቡ ላይ ያከበደውን ሸክም እንዲያቀል መከሩት። ሮብሃም ግን በዚህ ምክር ደስተኛ አልነበረም ይልቅ የወጣት ጓኞቹን ምክር ፈለገ፡

8 እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ።

9 እርሱም፦ አባትህ የጫኑብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው።

10 ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች፦ አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።

11 አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት።  (1 ነገስት 12)

ሮብዓም ከሽማግሌዎቹ ይልቅ የጓደኞቹን ምክር በመስማት በህዝቡ ላይ ሸክምን ለማከበድ ወሰነ ውጤቱ ግን የሃገሩ መበታተን እና ይሁዳ እስራኤል ላይ ተቀናቃኝ መንግስት ሆኖ መመስረቱ ነበር

እኛ በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ውስጥ የሌሎችን ምክር መፈለግ ጠቃሚ ቢሆንም የፈለግነውን ምክር ሳይሆን የሚያስፈልገንን ምክር የሚሰጡንን ሰዎች በዙሪያችን መሰብሰብ እንደሚቻል የሮብዓም ተሞክሮ ያሳየናል ምክር ሁሉ መልካም አይደለምና ምክር የምንጠይቃቸውን ሰዎች በተመለከተ በማስተዋል መለየት አለብን

ምክር ሁሉ መልካም ባይሆንም፣በዙሪያችን ያሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እና ጠቢባን የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ወገኖችን መስማታችን በጣም አስፈላጊ ነውበእርግጥ፣እነዚህ ወንዶችና ሴቶች ወገኖች እኛን ለማረም ወይም በትክክለኛ ውጎዳና ላይ ሊመሩን ወደ እኛ የተላኩ የእግዚአብሔር መሣሪያዎች ሲሆኑ ይችላሉ በዘፀአት 18 ላይ የሙሴን ጉዳይ እንመልከት፣ሙሴ የእስራኤል ህዝብ መሪ እንደመሆኑ መጠን በየቀኑ ብዙ ውሳኔዎችን እንዲያደርግ ይጠበቅበት ነበር

በአንድ ወቅት የሙሴ አማት ሊጎበኘው መጥቶ ነበር በማግስቱም ሙሴ በማለዳ ተነስቶ ቀኑን ሙሉ ከጠዋት ጀምሮ እስከማታ ድረስ የእግዚአብሔርን ህዝብ ሲፈርድ ዋለ

13 እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። (ዘጸአት 18)

አማቱ ይህን ባየ ጊዜ፤ለምን ቀኑን ሙሉ በእስራኤል ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሲፈርድ እንደዋለ ጠየቀው። ሙሴም ለአማቱ ያለበትን ሁኔታ አብራራ፡

15 ሙሴም አማቱን፦ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤

16  ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው።

 

በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል በርካታ የሆኑ አለመግባባቶች ነበሩ፤ሙሴም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እግዚአብሔርን መፈለግ ያስፈልገው ነበር

የሙሴ አማት ምላሹን ሲሰማ ሙሴን ገሰጸው፡

17 የሙሴም አማት አለው፦ አንተ የምታደርገው ይህ ነገር መልካም አይደለም።

18 ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። (ዘጸአት 18)

 

አማቱ ሙሴን ምን ማድረግ እንዳለበት ምክር ሰጠው ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ከእነርሱ መርጦ ቢያሰለጥን እና እነርሱም በትንንሽ ጉዳዮች ላይ ቢፈርዱ ሸክም እንደሚቀልለት እና ምክር የሚፈልገውም ህዝብ ፈጣን እና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንደሚስተናገድ መከረው። እግዚአብሔር ሰዎችን ለማገልገል የተሻለ መንገድ ለማሳየት የሙሴን አማት ተጠቅሞበታል ሙሴ ይህንን ምክር ባይጠይቅም እግዚአብሔር ወደ እርሱ ላከው ሙሴ ይህን ምክር ከጌታ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆኑ አስፈላጊ ነበር።

በአዲስ ኪዳንም ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷል በሐዋርያት ሥራ 18 ላይ አጵሎስ ስለሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው እናነባለንእርሱ በጌታ መንገድ ታዝዞ እውነትን ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር (ሐዋ 1825) በእውቀቱ ረገድ ግን አንዳንድ ክፍተቶች ነበሩበት

ጵርስቅላ እና አቂላ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወስደውየእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት (የሐዋርያት ሥራ 18:26) አጵሎስ ይህንን ምክር ተቀብሎ የበለጠ ኃይለኛ የእግዚአብሔር ቃል ሰባኪ በመሆን ቀጠለ (ሐዋ 18:28) ። አጵሎስ ይህንን ምክር በእውነቱ እየፈለገ አልነበረም፣ዳሩ ግን እግዚአብሔር ጵርስቅላ እና አቂላን ወደ እርሱ ላካቸው እነዚህ አጵሎስን ለማጎልበት እና ይበልጥ ውጤታማ ሰባኪ ለማድረግ የእግዚአብሔር መሣሪያዎች ነበሩ

ልንወስደው የሚገባውን አቅጣጫ ለማወቅ እንድንችል እግዚአብሔር የጋራ ጥበብን እንዴት እንደሚጠቀም ከቅዱሳት መጻሕፍት አንድ ተጨማሪ ምሳሌ ልጨምር በሐዋርያት ሥራ 15 በአንጾኪያ ውስጥ ስለተፈጠረው ሁኔታ እናነባለን ከይሁዳ የመጡ ሰባኪዎች ወደ አከባቢው መጥተው አንድ ሰው በሙሴ ሕግ ካልተገረዘ በቀር መዳን እንደማይችል ይሰብኩ ነበር ይህ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ባሉ ምእመናን መካከል ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር ጳውሎስና በርናባስ ይህንን ትምህርት በመቃወም ከይሁዳ የመጡ አስተማሪዎችን ተቃወሙ ቤተክርስቲያኗ ተከፋፈለች በምዕመናን መካከል በተፈጠረው አለመግባባት በጳውሎስና በርናባስ የተመራው የምዕመናን ልዑክ በሐዋርያቱና በሽማግሌዎቹ ፊት ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመጠየቅ ወደ ኢየሩሳሌም ተላከ

2 በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ። (ሐዋሪያት ሥራ 15)

ከብዙ ውይይት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ምክር ቤት ወደ ውሳኔ መጣ። ውሳኔው በጽሑፍ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡

[28-29] ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ። (ሐዋ 15)

እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤የሚለውን ሐረግ አስተውሉበሌላ አገላለጽ ምክር ቤቱ ባስተላለፉት ውሳኔ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ቀጥተኛ ምሪት ነበረው ይህ የሰው ክርክር ውጤት ሳይሆን በቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ዘንድ የሚሰራ የእግዚአብሔር መንፈስ ሥራ ነው እግዚአብሔር በእነዚያ መሪዎች መካከል በመመላላስ እርሱን የሚያከብር እና ለህዝቦቹ መዳን ዓላማውን የሚያሳካ ውሳኔ እንዲወስኑ በሚከራከሩ ጊዜ ምሪትን ይሰጣቸው ነበር የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የሐዋርያትንና የሽማግሌዎች ምክር ቤት በመፈለጋቸው ምክንያት አንድ ሰው ለመዳን መገረዝ ያስፈልገዋል የሚለው ጉዳይ ተፈታ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት እነዚህ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የእግዚአብሔርን ዓላማ በመለየት የአንጾኪያ ወንድሞችንና እህቶችን መምከር ችለዋል

በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ውስጥ የምናየው ጌታ እግዚአብሔር በምንሄድበት መንገድ ሊመክሩን የሚችሉ ሰዎችን ሊልክ ይችላል ትክክለኛ ምርጫዎችን ለማድረግ ከፈለግን በዙሪያችን ያሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወንዶችና ሴቶችን ለማዳመጥ ፈቃደኞች መሆን ያስፈልገናል። እግዚአብሔር እኛን ለመምራት ቅዱስ ቃሉን ይሰጠናል እርሱ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና በመንገዳችን በሚልካቸው ሰዎች መልካም ምክር ይመራናል።

 

ለግንዛቤ፡

ሰሎሞን ያለ ምክር እቅድ እንደማይሳካ ይናገራል። የሌሎችን ምክር እንዳንሰማ የሚያግደን ምንድ ነው?

 

መልካም መካሪዎችን ከክፉ መካሪዎች የምንለየው አንዴት ነው?

 

እግዚአብሔር ለምክር ሰዎችን ወደ አንተ ልኮ ያውቃለን? ያንን ምክር ሰምተህ ታውቃለህን?

 

በሐዋሪያት ሥራ 15 ላይ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ምክር ቤት የተወሰኑትን ውሳኔዎች ተመልከት። ውሳኔ በመወስን ሄደት ላይ የሕዝብ ክርክር እና ጸሎት ሚናው ምንድ ነው?

 

ለጸሎት:

ጌታ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎችን ምክር እና ተግሳጽ ለመፈለግ ፈቃደኛ እንዲያረግህ ጸልይ 

 

በዙሪያ ያሉ ሰዎችን ምክር ችላ በማለት በራስህ መንገድ ለተጓዝክባቸው ጊዜአት እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ጸልይ

 

ትክክለኛውን ውሳኔ እንወስን ዘንድ እኛን ለመርዳት ጌታ ሌሎችን ሰዎች ስለመጠቀሙ ጌታን አመስግን። የጥበብን ምክር ጠቢብ ካልሆነው የምትለይበትን መለየት እንዲሰጥህ ጸልይ።

 


 

ምዕራፍ 9 - ውሳኔዎቻችንን የሚከታተል አምላክ

 

ጌታ እግዚአብሔር ለልጆቹ እግዚአብሔርን መፍራት ማዕከል ያደረገ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ድጋፍ ቢሰጣቸውም፣ማናቸውም የጌታን ምክር አይሰሙም ነበር። ውሳኔዎች በየቀኑ ከእግዚአብሔር ዓላማ ጋር የሚቃረን መልኩ የሚወሰኑ ናቸው። ከእነዚህ ውሳኔዎች መካከል አንዳንዶቹ እኛን የሚጎዱ ናቸው። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር እኛ ከምናደርጋቸው እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለባቸው ምርጫዎች ሊጠብቀን እና ሊመራን ይፈልጋል።

ዮሴፍ የአባቱ ያዕቆብ ተወዳጅ ልጅ ነበር። ይህ አድልዎ እሱን መጥላት የጀመሩትን የወንድሞቹን ቅናት ቀሰቀሰ። ይህ ጥላቻ በጣም የበረታ ከመሆኑ የተነሳ ዕድሉ በተገኘ ጊዜ ወንድሞቹ ዮሴፍን ለባርነት በመሸጥ አንድ የዱር እንስሳ እንደበላው አድርገው ለአባቱ ነገሩት። ዮሴፍን ለማስወገድ የወሰኑት ውሳኔ ከክፉ የቅናት እና የቁጣ ልብ የመጣ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ሁኔታውን ወደ መልካም ነገር ለወጠው።

ዮሴፍ በግብፅ ኃያል መሪ ሆነ እናም በአካባቢው ረሃብ ሲከሰት ያዳነው የግብፅን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ህዝብም ጭምር ነው። አባታቸው ያዕቆብ ከሞተ በኋላ በወንድሞቹ ፊት ቆሞ ዮሴፍ እንዲህ አለ፡

19 ዮሴፍም አላቸው፦ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?

20 እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። (ዘፍጥረት 50)

የዮሴፍ አምላክ ከወንድሞቹ ክፉ ውሳኔ በመጠበቅ የእስራኤልን ህዝብ ለማዳን ክፉ ምርጫዎቻቸው ተጠቅሟል።

መሣፍንት 13-14 ውስጥ የብዙ የሳምሶን መጥፎ ውሳኔዎች ታሪክ ነው። በመሣፍንት 14 ላይ ሳምሶን ወደ ተምና እንዴት እንደወረደ እና እዚያ ሊያገባት ከሚፈልጋት ሴት ጋር እንዴት እንደ ተገናኘ እናነባለን። የባዕድ ሴት ለማግባት መፈለጉ ከሙሴ ሕግ ጋር የሚቃረን ነበር። የሳምሶን ወላጆች ለሙሽራ ምርጫው የሰጡትን ምላሽ ልብ ይበሉ፡

3 አባቱና እናቱም፦ ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለምን? አሉት። ሶምሶንም አባቱን፦ ለዓይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ አለው። (መሳፍንት 14)

ሳምሶን የወላጆቹን ምክር ባለመስማት የተምናን ሴት ለማግባት አጥብቆ ጠየቀ ሴቲቱን ለማጨት ከወላጆቹ ጋር ወደ ተምና በሚሄድበት ጊዜ ሳምሶን ከአንበሳ ጋር ተገናኘ ያን አንበሳ ገድሎ ሬሳውን በሜዳ ውስጥ ትቶ ሄደ ለጋብቻ ሥነ ሥርዓቱ ሲመለስ ሳምሶን በአንበሳው ሬሳ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፥ ማርም ነበረበት።  በእጁም ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ መጣ፥ ማሩንም ሰጣቸው።

እዚህ ጋር መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር ሳምሶን ፀጉሩ እንዲረዝም እና የሞተ አካልን በጭራሽ እንዳይነካ በእግዚአብሔር ዘንድ ግዴታ የተጣለበት ናዝራዊ ነበር ሳምሶን ወደዚያ ወደ አንበሳው ሬሳ ሄዶ ማር ወስዶ በመብላት በጌታ ዘንድ የነበረውን ቃል ኪዳን ችላ ማለት መረጠ

ወደ ተምና ሲደርስ ሳምሶን አንድ እንቆቅልሽ ለጓደኞቹ አቀረበ፡ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፥ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ አላቸው።” (መሣፍንት 1414) በሦስት ቀናት ውስጥ እንቆቅልሹን መፍታት ከቻሉ ሠላሳ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እንደሚሰጣቸው ነገራቸው ካልቻሉ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ ለእርሱ ይሰጡታል። ጓደኞቹ ወደ ሳምሶን እጮኛ ቀርበው የእንቆቅልሹን መልስ ካላገኘች እሷን እና ቤተሰቧን እንደሚገድሉ ነገሯት እነዚህ ጓደኞች እንቆቅልሹን ሲመልሱ ሳምሶን ምን አድርገው እንደነበር አወቀ በንዴት ወጥቶ ከከተማይቱ ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፣ልብሳቸውን ወደ ጓደኞቹ አመጣና ከተማውን ለቆ ወጣ የሳምሶን አማት ከተማውን ለቆ እንደወጣ ባየ ጊዜ ሚስቱን ለሌላ ሰው ሰጣት

ሳምሶን ከሚስቱ ጋር ለመሆን በተመለሰ ጊዜ ለሌላ ሰው መሰጠቷን አወቀ፤ከዚያም በመከር ወቅት የእህል ማሳዎችን እና የፍራፍሬ እርሻዎችን ሁሉ አቃጠለ ይህም የከተማይቱን ሰዎች በጣም ስላበሳጨ የሳምሶንን ሚስት እና ቤተሰቦችን ገደሉ ሳምሶን ይህንን ደም እስኪበቀል ድረስ እንደማይቆም በዚያ ቀን አሳወቀ (መሣፍንት 157) በቀሪው የሕይወት ዘመኑ ሳምሶን እንደ እስራኤል ጠላቶች ፍልስጤማውያንን ይዋጋ ነበር

በሳምሶን ዘመን ፍልስጤማውያን የእስራኤል ቁጥር አንድ ጠላት ነበሩ እስራኤልን ለአርባ ዓመታት ሲጨቁኑ ኖረዋል እስራኤል ለማዳን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ

 

እግዚአብሔር ማኑሄ የተባለች አንዲትን መካን ሴት ተናግሮ እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን  እጅ  ነጻ የሚያወጣ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡

3 የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፦ እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፥ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።

4 አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ።

5 እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል። (መሣፍንት 13)

 

በተከታታይ መጥፎ ውሳኔዎች ምክንያት ሳምሶን ይህንን ጥሪ በሕይወቱ አውቋል የባዕድ ሃገር ሴት ማግባትን መርጧል እንደ ናዝራዊ የተሰጠውን ጥሪ ችላ በማለት የአንበሳውን ሬሳ ነካ ጓደኞቹን ስለዚያ አንበሳ እንቆቅልሹን እንዲመልሱ ጋበዛቸው ሆኖም የእንቆቅልሹን መልስ በተመለከተ እጮኛው በሚስጥር እንደምትይዘው እምነት ጣለባት በከተማው ውስጥ ሠላሳ ሰዎችን ገድሎ የፍልስጥኤማውያንን የእርሻ ማሳዎች አቃጠለ እነዚህ በችኮላ እና እግዚአብሔርን ባለመፍራት የተወሰኑ ውሳኔዎች የሳምሶን ልብ በፍልስጥኤማውያን ላይ በጥላቻ እና ምሬት እንዲሞላ አደረገው ውጤቱ የነበረው ቀሪ ሕይወቱን ያ የእግዚአብሔር ህዝብ ጠላት የሆነውን በማጥፋት ላይ ያተኮረ ነበር ሳምሶን በመጨረሻ በፍልስጥኤማውያን እጅ ሕይወቱን የሚያጣ ቢሆንም፣የእስራኤል ተከላካይ እና ህዝቡን የሚጠበቅ ኃያል ተዋጊ በመሆን በታሪክ ውስጥ ሰፍሯል የሕይወቱ ምርጫዎች እግዚአብሔርን በመፍራት ላይ የተመሰረቱ ባይሆኑም እንኳን እግዚአብሔር ግን ተጠቅሞበታል

እግዚአብሔር ሳምሶንን ወይም የዮሴፍ ወንድሞችን መጥፎ ውሳኔዎችን ከመወሰን ባያግዳቸውም፣ዳሩ ግን እሱ በመጨረሻው ላይ ጣልቃ በመግባት ውሳኔአቸውን ለመልካም ለውጦታል ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነት በጣም ሚስጥራዊ ነገር አለ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን በምናደርግበት ጊዜም እንኳን እግዚአብሔር እነዚህን ውሳኔዎች የራሱን ዓላማ ለማሳካት ሊጠቀምባቸው ይችላል እሱ ከእኛ ውሳኔዎች እና ምርጫዎች ይበልጣል በሆሴዕ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር የሕዝቦቹን ውሳኔ እንዴት እንደሚቆጣጠር የሚናገር አንድ አስደናቂ ክፍል አለ፡

 

7 እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ ብላ አስነወረቻቸው።

8 ስለዚህ፥ እነሆ፥ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ።

9 ውሽሞችዋንም ትከተላለች፥ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ ትፈልጋቸውማለች፥ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ እርስዋም፦ ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ይሻለኝ ነበርና ተመልሼ ወደ ቀደመው ባሌ እሄዳለሁ ትላለች። (ሆሴዕ 2)

 

በሆሴዕ 2 ውስጥ ጌታ ሕዝቡን በክህደታቸው ይከሳቸዋል ሌሎች ፍቅረኞቿን ተከትላ አንድ እውነተኛ አምላክዋን ትታለች ሲል ከሷታል እስራኤል በታሪኳ በዚህ ወቅት ከእግዚአብሔር መራቅን እና ሌሎች አማልክትን ማሳደድን መረጠች ለዚህ ውሳኔ የእግዚአብሔር ምላሽ ምን እንደሆነ አስተውሉ መንገዷን በእሾህ ይዘጋል፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን ያጥርባታል። ፍቅረኛዎቿን ብትከታተልም ስለማትደርስባቸው አታገኛቸውም

እግዚአብሔር ለሕዝቦቹ የጥፋት መንገዳቸውን ለማደናቀፍ እንቅፋቶችን አዘጋጅቷል በመረጠችው መንገድ ላይ እሾህ እና ቅጥርን አስቀመጠ እርሱ ያደረገው ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ ነው እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠቸውን ውሳኔ ባያስቀርም የክፋትን ጎዳና ለእሷ ቀላል አያደርግላትም

ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ ይህ ገጥሞታል እሱ ሃይማኖታዊ ሕይወትን መርጦ ነበር፤እንግዲህ የዚያ ክፍል ዓላማ የአምላኩን ስም የሚሳደቡትን ሁሉ ማስወገድ ነበር ክርስትናን የዚህ ስድብ አካል አድርጎ ተመልክቶታልና ወደ ደማስቆ እየተጓዘ እያለ እግዚአብሔር ዓይነ ስውር በሚያደርግ ብርሃን መታው አንድ ድምፅ ከዚያ ብርሃን ወጥቶሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃልአለው (ሐዋሪያት ሥራ 2614)

የመውጊያ ብረት ከብቶችን ለመምራት የሚያገለግል ሹል ዘንግ ነበር እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለጳውሎስ እየተናገረ ያለው እርሱ ባዘጋጀለት ጎዳና ጳውሎስን ለመንዳት በመሳሪያ እየተጠቀመ እንደነበር ነው ጳውሎስ የተሳሳቱ ውሳኔዎቹን እያደረገ ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሔር ያንን ውሳኔ እየተቆጣጠረው ነበር እግዚአብሔር ጳውሎስን በአመጽ ላይ ሳለ ተከታተለው የጌታ ጽኑ እምነት በሄደበት ሁሉ ይከተለው

 

ነበር ዓይነ ስውር ከሚያደርገው የጌታ ብርሃን በፊት ተንበርክኮ ጳውሎስ ውሳኔውን ለመቀየር ተገደደ ሊያጠፋው እና ይዋጋው ለነበረው እምነት እጁን አሳልፎ ይሰጣልን? በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የጳውሎስ ኩራት ተሰብሮ ልቡን ለኢየሱስ ክርስቶስ እውነት በነፃነት ከፍቷል። በአንድ ወቅት ሊያጠፋው ይፈልገው በነበረው እምነት ምክንያት መከራ እየተቀበለ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታላቁ ሚስዮናዊ ሆኗል

ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ምን እንማራለን? ነፃ ምርጫን የሚሰጠን አምላክ፣የእርሱን ቁጥጥር አሳልፎ አይሰጥም። በሕይወቴ ጉዳዮች ላይ በሉዓላዊነት መቆጣጠርን ቀጥሏል። እኔ ጥሩ ብዬ የምወስናቸውን መጥፎ ውሳኔዎች ለመልካም ሊጠቀም ይችላል። ጉዞዬን አስቸጋሪ ለማድረግ የምሄድባቸውን መንገዶች ሊዘጋቸው ወይም በእሾህ ሊያጥራቸው ይችላል። የተሳሳተ ጎዳና ስመርጥ እኔን ይከተለኛል ውሳኔዎቼን ሳደርግ እርሱ ይጠብቀኛል

እግዚአብሔር የስነ ፍጥረት ሙሉ ቁጥጥር ለሰው ልጆች እና ውሳኔዎቻቸው አሳልፎ ስለማይሰጥ ምንኛ አመስጋኞች መሆን አለብን እኔ ውሳኔዎችን ለማድረግ ነፃ ነኝ ዳሩ ግን የምወስናቸው ውሳኔዎች ሁሉ የሚመለከት እና በመንገዴም የሚመራኝ አንድ አምላክ አለ

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር የዮሴፍ ወንድሞችን ክፉ ውሳኔ እንዴት ወደ መልካም ቀየረው?

የሳምሶን መጥፎ ውሳኔዎች እግዚአብሔር እርሱን ከመጠቀም አግዶታልን? አብራራ።

እግዚአብሔር መጥፎ ውሳኔዎችን ከመወሰን ጠብቆህ ያውቃልን? አብራራ።

ጳውሎስ አማኞችን በሚያሳድድበት ጊዜ እግዚአብሔር ጳውሎስን ይከታተለው ነበር። በእግዚአብሔር ክትትል ውስጥ ሆነህ ታውቃለህን?

እግዚአብሔር የመምረጥ ነጻነት ቢሰጠንም፤እርሱ ፍጹም የሆነ ቁጥጥር በሰው ልጆች ላይ ያደርጋልን?

 

ለጸሎት:

ጌታ መጥፎ ውሳኔአችንን ወስዶ በሕይወታችን ለመልካም ስለሚለውጣቸው እግዚአብሔርን አመስግን።

በሕይወትህ መጥፎ ውሳኔዎችን ከመወሰን እግዚአብሔር ስለጠበቀህ ጊዜአት እግዚአብሔርን አመስግን።

እግዚአብሔር የህይወትህን ገጠመኞች ስለሚቆጣጠር አመስግን። የምርጫ ነጻነት ቢኖርህም እግዚአብሔር ግን አሁን ስለሚመለከትህ እና የአንተን መልካም ስለሚፈልግ አመስግን።

 


ምዕራፍ 10 - በውሳኔአችን እግዚአብሔርን መፈተን

 

በምናደርጋቸው ውሳኔዎች ውስጥ እግዚአብሔር ትልቅ ድጋፍ ቢሰጠንም የእርሱን ምክር ችላ ማለት እንችላለን ሁሉም ሰው እንደ እግዚአብሔር ቃል መርሆዎች ምሪት አይመላለስም የእግዚአብሔርን መንፈስ መሪነት መቃወም እንችላለን አንዳንድ ጊዜ ይህ ያልታሰበ ነው፣ነገር ግን በሌላ ጊዜ፣በልባችን ጥንካሬ እና በፈቃዳችን ግትርነት ምክንያት፣ሆን ብለን ላለመታዘዝ እና የእግዚአብሔርን ዓላማ ለህይወታችን ላለማክበር ሆን ብለን እንመርጣለን፡

እግዚአብሔር በዘዳግም 6 ላይ በሙሴ በኩል የተናገረውን ቃል እንመልከት፡

16 በማሳህ እንደ ፈተናችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት።

17 ለእናንተ ያዘዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ምስክሩንም ሥርዓቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ።

18-19 መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ። (ዘዳግም 6)

 

እግዚአብሔር ሕዝቡ ትዕዛዛቱን በመጠበቅ እንዲመላለሱ አዟል እስራኤል አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲፈታተኑት አልነበረም እግዚአብሔርን መፈተን ምን ማለት እንደሆነ አንድ ምሳሌ እንመልከት፤ሙሴ በማሳህ የሆነውን ለሕዝቦቹ ያስታውሳል

ዘጸአት 17 በማሳህ ላይ ስለተከናወነው ነገር ይተርካል እስራኤል በምድረ በዳ መጓዙ ሰልችቷቸው ለሙሴ ቅሬታቸውን ገለፁ ወደ ተስፋይቱ ምድር የጌታን መመሪያ ከመከተል ይልቅ ወደ ግብፅ መመለስ እንደሚፈልጉ ነገሩት እነርሱ የተራቡ እና የተጠሙ በመሆናቸው እና የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመፈጸም ምንም እንደማይፈልጉ በመናገር ብስጭታቸውን ገልጸዋል ማሳ በእግዚአብሔር መንገዶች ለመመላላስ ፈቃደኛ ያልሆነውን መራራ እና ዓመፀኛ የሆነውን የሰውን መንፈስ ይወክላል

ዘማሪው ስለዚህ ግትር ስለሆነ ልብ በመዝሙር 95 ላይ ይናገራል፡

7 እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና።

8 በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ።

9 የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ።

10 ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ።

11 ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ። (መዝሙር 95)

 

ዘማሪው የእግዚአብሔርን ድምፅ ከሰማን ልባችንን እንዳናደነድን እንዴት እንደሚያስጠነቅቀን አስተውሉ አንባቢው እንዲያስተውል በማሳህ የተከናወነውን ምሳሌ ይጠቅሳል የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት እና ልባችንን በእርሱ ላይ ማደንደን እንችላለን ዘማሪው ይህ እግዚአብሔርን መፈታተን እንደሆነ ይናገራል እግዚአብሔርን መፈታተን የሚያስገኘውን ውጤት አስተውሉ፡ እግዚአብሔር ያንን ትውልድ ተቃወመው (ቁጥር 10) ወደ ዕረፍቱም እንደማይገቡ ማለ (ቁጥር 11)

በመዝሙር 81 ውስጥ ዘማሪው እስራኤል ድምፁን ስላልሰሙ እግዚአብሔር እልከኛ ለሆነ ልባቸው አሳልፎ እንደሰጣቸው ይነግረናል፡

11 ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም።

12 እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ። (መዝሙር 81)

 

እግዚአብሔር ህዝቡ የሚፈልገውን ሰጠው ነገር ግን በምላሹ ዋጋ የሚከፍሉ ይሆናሉ

ጳውሎስ በሮሜ 1 ላይ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፡

18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤

19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።

20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።

22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥

23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤

25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። (ሮሜ 1)

 

ጳውሎስ በዘመኑ በነበረው እግዚአብሔርን ያለመፍራት ድርጊቶች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ እየተገለጠ መሆኑን ለሮሜ ሰዎች ይነግራቸዋል እግዚአብሔር ህልውናውን የገለጠ ቢሆንም፤ዳሩ ግን የሮሜ ሰዎች እርሱን ወይም የእርሱን ዓላማ ለመመልከት ፈቃደኛ አልነበሩም ይልቁንም የእግዚአብሔርን ክብር በጣዖታት እና ምስሎች ለመለወጥ መረጡ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይልቅ የልባቸውን ምኞቶች መከተል መረጡ ውጤቱ እግዚአብሔር ለፍላጎታቸው እና ለኃጢአተኛ ምኞታቸው አሳልፎ ሰጣቸው ውጤቱን ለመግለጽ ጳውሎስ በሮሜ 1 ይቀጥላል፡

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።

28እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤

29 ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥

30 ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥

31 የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤

32 እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።  (ሮሜ 1)

 

የሮማውያን ማህበረሰብ በስነምግባር ጉድለት፣በዝሙት፤በእርኩሰት፣ምቀኝነት፣ነፍስ መግደል፣ማታለል፣ሐሜት፣ጥል፣ክርክር፤አክብሮት መጓደል እና አላዋቂነት ተሞልተው ነበርሰዎች በፊታቸው ደስ ያሰኛቸውን በሚያደርጉ ጊዜ ሕብረተሰባቸው እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ይከፍል ነበርእነርሱ የእግዚአብሔርን ዓላማ ችላ ለማለት መርጠዋል ስለዚህም እግዚአብሔር ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጣቸውእነዚያ ከንቱ ፍላጎቶች እና ምኞቶች አጠፋቸው

በሆሴዕ ዘመን እግዚአብሔር ለህዝቡ ሲናገር እንዲህ ይላል፡

17 ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ተወው።

18 ስካርን ፈጽመዋል፥ ግልሙትናንም አብዝተዋል፤ አለቆችዋም ነውርን እጅግ ወደዱ።

19 ነፋስ በክንፍዋ አስሮአታል፤ ከመሥዋዕታቸውም የተነሣ ያፍራሉ። (ሆሴዕ 4)

 

ኤፍሬም ከእግዚአብሔር ተለይቶ ጣዖታትን ማምለክን፣በስካርና በግልሙትና መኖርን መርጧልእግዚአብሔርምተዉት”“እነርሱ ያፍራሉበማለት ተናገረ ኤፍሬም ስለአመፁ እና ስለባከነ ህይወቱ በጥልቀት እፍረት ወደኋላ የሚመለከትበት ቀን ይመጣልበዚህ መንገድ  ከቀጠለ እግዚአብሔር አያቆመውም ዳሩ ግን በመጨረሻ ለእሱ ሞኝነት ዋጋውን የሚከፍል ይሆናል

በኢየሱስ ዘመን የነበሩት ፈሪሳውያን እርሱ ሲሰብክ የመስማት እድል ነበራቸው ተዓምራቶቹን አይተው በግል ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፣ዳሩ ግን እሱን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም እነርሱ በግትርነት እርሱን እና መልዕክቱን ተቃወሙ ጌታ ኢየሱስ ስለ እነዚህ ፈሪሳውያን ሲናገር:

14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ። (ማቴዎስ 15)

ጌታ ፈሪሳውያንን ለዓመፀኛ ልባቸው አሳልፎ ሰጣቸው እነርሱ መንገዳቸውን ማግኘት ይችሉ ነበር፣ነገር ግን ዋጋቸው በጣም ከፍተኛ ነበር እንደ ዓይነ ስውር መሪዎችወደ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ። በዚያ ጉድጓድ ውስጥ እነርሱ ከናቁት አምላካቸው ለዘላለም ይለያሉ ለዚህ ጥፋተኛ የሚሆኑት ራሳቸው ብቻ ናቸው

እስጢፋኖስ በከሳሾቹ ፊት ሲመሰክር የተናገረውን አስተውሉ፡

39 ለእርሱም አባቶቻችን ሊታዘዙት አልወደዱም፤ ነገር ግን ገፉት በልባቸውም ወደ ግብፅ ተመለሱ፤

40 አሮንንም፦ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና አሉት።

41 በዚያም ወራት ጥጃ አደረጉ ለጣዖቱም መሥዋዕት አቀረቡ፥ በእጃቸውም ሥራ ደስ አላቸው።

42እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በነቢያትም መጽሐፍ፦ እናንተ የእስራኤል ቤት፥ አርባ ዓመት በምድረ በዳ የታረደውን ከብትና መሥዋዕትን አቀረባችሁልኝን?

43 ትሰግዱላቸውም ዘንድ የሠራችኋቸውን ምስሎች እነርሱንም የሞሎክን ድንኳንና ሬምፉም የሚሉትን የአምላካችሁን ኮከብ አነሣችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰዳችኋለሁ ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል። (ሐዋሪያት ሥራ 7)

 

እስጢፋኖስ አባቶቻቸው ጌታን ለመታዘዝ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እና በግትርነት ወደ ግብፅ መመለስ ይናፍቁ እንደነበር ለሚሰሙት ያካፍል ነበር አንድ እውነተኛውን አምላክ ክደው በምትኩ የጥጃ አምላክን አመለኩ ውጤቱእግዚአብሔር ግን ዘወር አለ የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፥”(ቁጥር 42) ይላል ይህ በመጨረሻ እስራኤል አገሯን እና የነበራትን ሁሉ ወዳጣችበት ወደ ባቢሎን እንድትሰደድ ምክንያት ሆኗል (ቁጥር 43) ይህ የሆነበት ምክንያት የጌታን ምክር በመቃወማቸው እና እርሱን ስለ ገፉትነው (ቁጥር 39)

ጳውሎስ በኤፌሶን 4 ላይ ስለማያምኑ አህዛብ የተናገረውን እንመልከት፡

17እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።

18 እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤

19 ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።

20 እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤ (ኤፌሶን 4)

ጳውሎስ አሕዛብ ከንቱ የሆነ ልብ እንዳላቸው ያስረዳል። ይህ ከእንግዲህ ለስላሳ ወይም የእግዚአብሔርን ቃል ወይም የመንፈሱን ምሪት የማይቀበል ልብ ነው። ጳውሎስ እነዚህን አሕዛብን እንደ ምሳሌ ተጠቅሞእናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤” (ቁጥር 20) በማለት ይደመድማል። በሌላ አገላለጽ ቅን የሆነ የክርስቲያን ልብ ለስላሳ እና የእግዚአብሔርን ምክር የሚቀበል ነው።

2 ተሰሎንቄ 2 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ መጪው ጊዜ በትንቢት ተናግሯል። በሐሰት ምልክቶች እና ድንቆች የታጀበ ዓመፅ ወደዚህ ምድር እንደሚመጣ ተናግሯል፡

9-10  ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።

11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል። (2 ተሰሎንቄ 2)

 

በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ቢኖር ብዙዎች እውነትን ከመውደድ ይልቅ የሕገወጥነትን ሐሰት እንደሚያምኑ ነው እንደ ጳውሎስ ገለጻ በውጤቱም ጌታ ለማይረባ አዕምሮ እና የስህተት አሰራር አሳልፎ ይሰጣቸዋል። በመጨረሻ እነዚህ ግለሰቦችበእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉፍርድን ይቀበላሉ (ቁጥር 12)

እነዚህ ቁጥሮች የሚያሳየን የጌታን ምክር ውድቅ ማድረግ እንደሚቻል ነው የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት አለመታዘዝ እንችላለን። በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመከተል እምቢ ማለት እንችላለን። አማኞች እንኳን ሳይቀሩ እግዚአብሔር ካወጣው ደረጃ የጎድላሉ። እግዚአብሔር አሳልፎ በሰጠን በአመፃችን እንዲሁ መጽናት ይቻላል ይሁን እንጂ በሕይወታችን ውስጥ የሚያስከትለውን መዘዝ ልንቀበል እንገደዳለን።

ምናልባት የሌላውን በደልን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ያልሆነ አንድ ወንድም ወይም እህት አጋጥሟችሁ ያውቅ ይሆናል። ምናልባት አንድ ወንድም ወይም እህት በንስሐ ባለመመለስ የመንፈስን እምነት በመቃወም በኃጢአተኛ አኗኗር ሲቀጥል ተመልክተው ይሆናል። ኃጢአት የሚኖረው የእግዚአብሔርን ምክር ባለመቀበል ነው። በዓለማችን የምናየው መከራ እና ሥቃይ የመጥፎ ምርጫ ውጤት ነው። ሔዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ችላ በማለት የተከለከለውን ፍሬ በልታ በዚህች ምድር ላይ የኃጢአት እርግማን አመጣች። ይህ ኃጢአት ዛሬ የምናየውን ምስቅልቅል የሆነ ሕይወት እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል።

የእግዚአብሔርን ቃል እና የመንፈሱን እውነት በመቃወም ስንቀጥል፣በኃጢአት  ምክንያት በሕብረተሰባችን እና በግል ሕይወታችን ላይ የሚደርሰው መከራ ይቀጥላል። እግዚአብሔር ምርጫ ሰጥቶናል። የእውነት መመሪያችን ይሆን ዘንድ ቃሉን በተአምራዊ ሁኔታ ጠብቆ አቆይቶልናል። እኛን ለማስተማር እና በሄድንበት መንገድ እንዲመራን መንፈስ ቅዱስን ልኮልናል። እንዲያውም ምርጫዎቻችንን ለመመልከት እና መጥፎ ውሳኔዎቻችንን ወደ ጥሩነት ለመለወጥ ቃል ገብቷል። እርሱ የእርሱን ምክር እንድንሰማ እና የእርሱን ምሪት እንድንከተል ይጠብቀናል። በፈቃደኝነት ለዓላማው እንድንሰጥ ይፈልጋል። የእርሱ ሃሳብ በመታዘዝ እንመላለስ ዘንድ ይገባናል። እርሱ የተናገረውን እንድንጥል ነፃነት ይሰጠናል ግን እንድናዳምጥ ደግሞ ይለምናል፡

7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፦

8-9 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። (ዕብራውያን 3)

 

ባለመታዘዝ ምክንያት በሚመጡ መዘዞች የምንሰቃይ ከሆነ እግዚአብሔር አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ባለማድረጉ ምክንያት ሳይሆን ነገር ግን እሱን ስለተፈታተንን እና ድምፁን ለመስማት በመቃወማችን ምክንያት ነው። የእሱን ድምፅ መስማት ከቻልን ልባችንን በእሱ ላይ ማጠንከር የለብንም። ይልቁንም የጽድቅን እና የበረከትን መንገድ እንድንመርጥ ልባችንን ለእርሱ እና ለምሪቱ ንፁህ እና የተዘጋጀ ማድረግ አለብን።

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ዓላማ መቃወምና የተሳሳቱ ውሳኔዎችን መወሰን ይቻላልን?

ለአማኞች የተሳሳቱ ውሳኔዎችን መወሰን እና በኃጢአት መኖር ይቻላልን?

እግዚአብሔር ለኃጢአተኛው ልባቸውን አሳልፎ ሰጠን ማለት ምን ማለት ነው? በሕይወታችን የኃጢአት ውጤት ምን ያመጣል?

በማህበረሰባችን ውስጥ እግዚአብሔርን እና ዓላማውን የመቃወም ነገር ትመለከታለህን? አብራራ

ለእግዚአብሔር እና ለሕይወት ላለው ፈቃዱ የሚገዛ ለስላሳ ልብ እንዴት ልታሳድግ ትችላለህ? ልባችንን ለእግዚአብሔር ነገር የሚያጠነክረው ምንድ ነው?

እግዚአብሔር ዛሬ እንድታስወግደው የሚናገርህ ኃጢአት በሕይወትህ አለን? ምንድ ናቸው? ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

 

ለጸሎት፡

እግዚአብሔር ለቃሉ እና ለመንፈሱ ምሪት ልብህን እንዲያለሰልስ ጸልይ። ለመታዘዝ ትችል ዘንድ የሚሰማ ጆሮ እና ፈቃደኛ የሆነ ልብ እንዲሰጥህ ጸልይ።

እርሱን ለመምረጥ ነጻነት ስለጠን እግዚአብሔርን አመስግን። በውሳኔዎቻችን ምሪትን ስለሚሰጥን አመስግን። በሕይወትህ ለምሪቱ እና ለእምነቱ ታዛዥ ትሆን ዘንድ እንድትችል ጸልይ።    

በኃጢአት ለተሞላ የሕይወት ዘይቤአቸው ተላልፈው ለተሰጡ ሰዎች ለመጸለይ ጊዜ ውሰድ። በኃጢአት ለሚኖሩት በንስሃ ይመሉ እና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ህብረታቸውን ያድሱ ዘንድ ለስላሳ ልብ አንዲሰጣቸው ጸልይ።


 

ምዕራፍ 11  - ኃጢአት፡ አመጸኛ ፈቃድ

 

ኃጢአትን እንዴት ትገልጸዋለህ? ኃጢአትን ለመግለፅ ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣በዚህ ጥናት አውድ መሠረት ለዚህ ጥያቄ በከፊል መልስ ለመስጠት ጥቂት ጊዜ ልወስድ። ኃጢአት በብዙ መንገዶች ከእግዚአብሔር ዓላማ ጋር የሚቃረን አመጸኛ ህሊና ወይም ውሰጠ ህሊና ፈቃድ ነው።

በኤደን ገነት ውስጥ ሔዋን መልካም እና ክፉ በምታስታውቀው ዛፍ ፊት ቆመች። በዚያን ቀን ከሰይጣን ጋር በመነጋገር ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ለመብላት ተፈተነች። ጌታ ከዛፉ እንዳትበላ እንዳዘዛት ታውቅ ነበር፤ነገር ግን ፍሬውን በመቅመስ ስለምታገኛቸው የተገለጡ ጥቅሞች በመደነቅ ጌታን ትዕዛዝ ተላለፈች። ይህ እሷ እያወቀች የመረጣችው እና አመከንዮታዊ ምርጫ ነበር። እርሷ ራሷን እግዚአብሔርን በሚቃወም ስፍራ አስቀመጠች። ይህ የመጀመሪያው ኃጢአት ነበር።

በገነት ውስጥ የተከናወነው ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ቀጥሏል። እስራኤል የእግዚአብሔርን ዓላማ በማመጽ የራሱን መንገድ መርጠ። ዘማሪው በመዝሙር 78 ላይ ሲጽፍ በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች እልከኞች እና ዓመፀኞች እንዲሁምመንፈሳቸው ለእግዚአብሔር ታማኝ እንዳልነበሩት አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ያስታውሳቸው ነበር።

5 ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ፥ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፤

6 የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ፤

7 ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፤

8 እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ፥ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ ነፍስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች፤ (መዝሙር 78)

 

አባቶቻቸው ለእርሱ የማይታመን ሕይወት ለመኖር በመምረጥ በእግዚአብሔር አምላክ ላይ ኃጢአት ሠሩ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል አመፅ ይናገራል። ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ህዝቡን በአመፅ ሲከስ እንመለከታለን፡

9 ዓመፀኛ ወገንና የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና፤ (ኢሳይያስ 30)

እንዲሁም በነብዩ በኢሳይያስ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡

2 መልካም ባልሆነው መንገድ፥ አሳባቸውን እየተከተሉ፥ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ። (ኢሳይያስ 65)

 

ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመስማት ፈቃደኛ ስላልሆኑ እና የራሳቸውን መንገድ ለመከተል ስለመረጡ ሰዎች ይናገራል። ጆሮአቸውን በመድፈን የራሳቸውን መንገድ ለመከተል መርጠዋል ይላል።

 

ሕዝቅኤል በእርሱ ዘመን የነበሩ ሰዎችን አመጸኛ ቤት ብሎ ይገልጻቸዋል፡ 

7 እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ቃሌን ትነግራቸዋለህ። (ሕዝቅኤል 2)

በሕዝቅኤል 12 ውስጥ ይህን አመጽ እንዴት እንደገለጸው ተመልከቱ፡

1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፤ ያዩ ዘንድ ዓይን አላቸው እነርሱም አያዩም፥ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው እነርሱም አይሰሙም፤ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና። (ሕዝቅኤል 12)

ሕዝቅኤል የተናገራቸው ሰዎች የሚያዩ ዓይኖች ነበሯቸው ግን አያዩም። የሚሰሙ ጆሮዎች ነበሯቸው ግን አይሰሙም። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተናግሮ ነበር፣ዳሩ ግን እሱ የሚናገረውን ለመስማት ፈቃደኛ አልነበሩም። እርሱ በመካከላቸው መገኘቱን ገልጦ ነበር፣ዳሩ ግን ሊያሳያቸው የፈለገውን ለማየት እንቢ አሉ። እርሱን እና ቃሉን ባለመቀበል ኃጢአት ሠሩ።

ለባቢሎን ህዝብ ሲናገር ነብዩ ኤርሚያስ እንዲህ ይላል፡

29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት። (ኤርምያስ 50)

ኤርሚያስ ባቢሎን በትዕቢት እግዚአብሔርን ባለመታዘዟ ምክንያት እንዴት እንደከሰሳት አስተውሉ። በእርሱ ላይ አምጻለች፤ህዝቡንም  አጥፍታለች።                     ኃጢአቷም ለእግዚአብሔር አስቸግሯል እንዲሁም ራሷን የዓላማው ተቃዋሚ አድርጋ አስቀምጣለች።

እንቢ ማለትየሚለውን ሐረግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስንመረምር በጣም አስደናቂ የሆነ ውጤት እገኛለን

26 በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ ወደ እርስዋ መውጣትን እንቢ አላችሁ (ዘዳግም 1)

በዚህ ቁጥር ውስጥ ሙሴ እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመምራት እንዴት ዝግጁ እንደነበረ ይናገራል፤ነገር ግን ህዝቡ ጠላቶቻቸውን እንደማያሸንፉ በመፍራት ጠላትን ይዋጉ ዘንድ መሣሪያ ለማንሳት ፈቃደኛ አልነበሩም ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ህዝብ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለእነሱ የነበረውን ዓላማ በመጣስ ያደረገው ውሳኔ ነበር።

ጌታ በኤርምያስ ሕዝቡን ይገስጻቸው ነበር ምክንያቱም ምንም እንኳን በቋሚነትእንዲያስጠነቅቋቸው ነቢያትን ቢልክላቸውም እነርሱ ግን ለመስማት እንቢ አሉ። ይልቅ እነዚያ ከእግዚአብሔር የተላኩትን ነቢያት እና ያመጡትን መልዕክት ላለመቀበል መረጡ

19 ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ (ኤርምያስ 29)

 

በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታቸው ስላለው የእግዚአብሔር ዓላማእምቢተኞችስለነበሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ይናገራል። ይህ እምቢታ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ግለሰቦች በኩል እየታወቀ የተደረገ ውሳኔ ነበር። ዘማሪው በመዝሙር 78 ላይ እንዲህ ሲል ይገልጻል፡

 

10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፥ በሕጉም ለመመላለስ እንቢ አሉ፤ (መዝሙር 78)

የእግዚአብሔር ሕዝብ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል እና ህግ ችላ ለማለት በመወሰን በራሳቸው መንገድ ተጓዙ

ኤርሚያስ ተግሳጽን ተቀብለው ንስሃ ለመግባት እንቢ ያሉትን እና ፊታቸውን ከዓለት የበለጠ ስላጠነከሩ ሰዎች ይናገራል፡ 

3 አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ። (ኤርምያስ 5)

ነብዩ ዘካርያስም እንዲህ ይላል፡

11 እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፤ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።

12 የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ። (ዘካርያስ 7)

 

የእግዚአብሔር ሕዝብ እርሱን ለመስማት ፈቃደኛ አለመሆናቸው በእነሱ ዘንድ ሆን ተብሎ የተደረገ ውሳኔ መሆኑን ሳያውቁ ዘካርያስ 7:11-12ን ማንበብ ከባድ ነው። እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩይላልና። ህጉን እንዳይሰሙ ልባቸውን ከአልማዝ አጠነከሩ። ስህተቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ትከሻ ላይ በትክክል አርፏል። ጌታን እና መንገዶቹን ለመቃወም እና ላለመቀበል የመረጡት እነርሱ ነበሩ። የመምረጥ ነፃነታቸውን ተጠቅመው ለእግዚአብሔር አምላክ ጀርባቸውን አዞሩ።

በስተመጨረሻም፤በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያው ጳውሎስ፤ለተሰሎንቄ ሰዎች ሲጽፍላቸው፤ይህን የሚናገረው አማኝ ላልሆነ ሰው እንደሆነ ልብ ይሏል፡

9-10  ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው። (2 ተሰሎንቄ 2)

ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች ጓደኞቻቸው እና የሚወዷቸው ያልዳኑበት ምክንያት እውነትን ለመውደድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ይናገራል።

ለመጥፋታችን ምክንያት የሆነውን የመጀመሪያውን ኃጢአት መውቀስ ቀላል ቢሆንም፣የተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በዚህ አመፅ ለመቀጠል ራሳችን የመረጥን መሆናችንን መገንዘብ እንዳለብን ያሳያሉ። ኃጢአት በክርስቶስ ፊት ያለንበት ሁኔታ ነው ነገር ግን እኛ ያደረግነው የግል ውሳኔም ነው። ሁሉንም ጥፋቶች በአዳምና በሔዋን ላይ ማድረግ አንችልም። እኔ የመረጥኩትን እመርጣለሁ። በሕይወቴ የእግዚአብሔርን ምክር እቃወማለሁ። የራሴን ነገር ለማድረግ ቃሉን አግፋፍቻለሁ። ለኃጢአቴ መፍትሄ እንዲሆን ጀርባዬን ለክርስቶስ ሰጥቻለሁ። ለእግዚአብሔር ፈቃድ ልቤን አደንድኛለሁ። በኩራት ተሞልቼ በእግዚአብሔር ፊት እራሴን ከፍ ከፍ አድርጌአለሁ። ለሥጋዊ ፍላጎቶቼ እና ምኞቶቼ ተማረክሁ። ይህንን መንገድ እንድመርጥ ያስገደደኝ የለም። እኔ በራሴ ፍላጎት እና ነፃነት መረጥኩ። ኃጢአት በእግዚአብሔር ዓላማ ላይ ለማመፅ የግል ምርጫ ነው። እኔ በራሴ ምርጫ ጥፋተኛ ነኝ።

 

ለግንዛቤ፡

ኃጢአት ምንድ ነው?

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ኃጢአት ከመስራት ይጠብቀናልን? ኃጢአት ላለመስራት ምርጫ  አላችሁን?

የእግዚአብሔርን ቃል ላለመስማት ፍላጎት አሳይተህ ታውቃለህን ወይስ የራስህን ስራዎች ትክክለኝነት ለማጽደቅ እውነትን አጣመህ ታውቃለህን?

በተፈጥሮ ኃጢያተኛ ነኝ ማለት ከእንግዲህ ለኃጢአቴ ኃላፊነት መውሰድ የለብኝም ማለት ነውን? በኃጢአተኛ ተፈጥሮዬ ምክንያት ኃጢአት እንድሰራ እገደዳለሁን ወይስ ኃጢአት እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ የምወስነው ውሳኔ ነው?

 

ለጸሎት፡

እግዚአብሔር ከአመጸኛ ልብ እንዲጠብቅህ ጸልይ

ከኃጢአተኛ ተፈጥሮ ሳይሆን አንተ በግልህ በአመጽ ለመመላለስ በመምረጥህ ምክንያት ስለስራኸው ኃጢአት ንስሃ ግባ። በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን እመን እና ለይቅር ባይነቱ እሱን አመስግን

በሕይወታቸው እግዚአብሔርን እና ፈቃዱን የሚቃወሙ ሰዎችን ታውቃለህን? አመጸኝነትን እንዲሰብርላቸው እና ራሳቸውን ለእርሱ ያስገዙ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጸልይላቸው


 

ምዕራፍ 12 - ደህንነት፡ የፈቃድ መታደስ

 

በመጨረሻው ምዕራፍ፤ኃጢአት የዓመጽ ፈቃድ ውጤት እንደሆነ ተመልክተናል። እኛ ኃጢአተኞች የሆነው ከአዳም እና ሔዋን የተነሳ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በራሳችንም ምርጫ ጭምር ነው። ነብዩ ኤርምያስ ስለ ሰው ልብ የሚከተለውን ይናገራል፡

9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?

10 እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ። (ኤርምያስ 17)

 

በጣም በጠና የታመመልብ ያለን መሆኑን መቀበል ለእኛ ቀላል አይደለም። በየጊዜው በልቤ ያለውን ለመመልከት በአጭሩ ሰከንድ እወስዳለሁ። ያ ለልቤ ያለገደብ እና ያለምንም ከልካይ የፈለገውን እንዲያደርግ ብፈቅድ ይቻል ይሆን ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። የሚሰማኝን ፈተና አውቃለሁ። በአዕምሮዬ እታገላቸው የነበሩትን እነዚያን ሃሳቦች እና አመለካከቶች አውቅ ነበር። በሕይወቴ ያለ እግዚአብሔር ህልውና ዛሬ ባለሁበት እንደማልሆን አውቃለሁ። በውስጤ አመፀኛ ተፈጥሮ እንዳለ አውቃለሁ። ይህ ልብ ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር እንደሚታገል አውቃለሁ። እግዚአብሔርልብን እና አዕምሮን ቢመረምርእሱ ካለው መስፈርት እጅግ የጎደለ እንደሆነ አውቃለሁ። በተፈጥሮ ያለን የእርሱን ዓላማ እና ፈቃድ የሚቃወም ልብ እና አዕምሮ ነው።

ጌታ እግዚአብሔር በኖኅ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ልብ እና አዕምሮ በተመለከተ ጊዜ የተናገረውን ተመልከቱ፡

 

5 እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።

6 እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።   (ዘፍጥረት 6)

 

የሰው ልብ አሳብ እና ምኞት ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ ነበርየሰው ልብ አሳብ ምኞትም ከእግዚአብሔር ዓላማ ጋር የሚስማማ አልነበረም።

የእግዚአብሔር ክብር ያልጎደለው አንድም ሰው እንደሌለ ሐዋሪያው ጳውሎስ ግልጽ አድርጎ ያስቀምጣል

23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ( 3)

ኃጢአት በሕይወታችን እግዚአብሔርን እና ዓላማውን ለመቃወም የምንመርጠው ምርጫ ነው። ይህ የሚመጣው ራስን ለእግዚአብሔር እና ለዓላማው ከማያስገዛ ልብ እና አዕምሮ ነው። የሰው ልጅ በኃጢአት በመውደቁ ምክንያት ከታመመው ልብ የሚወጣ ነው።

ዘማሪው ዳዊት ከጎረቤቱ ሚስት ጋር በዝሙት ከወደቀ እና እውነቱ እንዳይታወቅ ባሏን ካስገደለ በኋላ የልቡን ኃጢአተኝነት ተረዳ። ዳዊት የዚህን የሕይወቱን ጊዜ በማሰላሰል እንዲህ ሲል ጽፏል፡

1 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።

2 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤(መዝሙር  51)

 

ዳዊት የወሳናቸው ውሳኔዎች ከእግዚአብሔር ሃሳብ ውጪ መሆኑን ተረድቷል። ውሳኔዎቹ ሁሉ ቅዱሱን እግዚአብሔርን ያሳዘኑ ነበር። በነጻነት ላደረጋቸው መጥፎ ምርጫዎች እግዚአብሔርን ይቅር እንዲለው ለመነ። በመዝሙር 51:7-8 ውስጥ ከእርኩሰቱ እንዲያነፃው እና በልቡ ውስጥ ደስታን እና ሃሴትን እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።

 

7 በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

8 ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።  (መዝሙር 51)

 

ቁጥር 10 ላይ እግዚአብሔር አዲስ ልብ እንዲሰጠው እና የቀናውን መንፈስ በውስጡ እንዲያድስ በመጠየቁን ይቀጥላል፡

10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። (መዝሙር 51)

ዳዊት አዲስ ልብን መስጠት ለእግዚአብሔር እንደሚቻል ያምናል። የእርሱ ሀሳብ እና ምኞት ከፉ እንደሆነ ተረድቷል። የቀናውን መንፈሱን በውስጡ በማደስ እግዚአብሔር እንዲለውጠው ፈለገ።

አዲስ ልብ ለእኛ መስጠት የሚቻል ብቻ ሳይሆን፣ዳሩ ግን ይህን ማድረግ የእግዚአብሔር ደስታ ነው። እግዚአብሔር በሙሴ ዘመን ለሕዝቡ ልባቸውንና የዘሮቻቸውን ልብ እንደሚገርዝ ተስፋን ሰጥቶ ነበር፡

6 በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህእንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሔር ልብህን የዘርህንም ልብ ይገርዛል። (ዘዳግም 30)

የልብ መገረዝ ውጤትን ልብ ይበሉ አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም ውደድ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ያለውን ፈቃድ ይለውጣል ከዚያም እግዚአብሔርን የመፈለግ መሻት ይሰጣቸዋል።

እግዚአብሔር ተመሳሳይ ነገር በኤርሚያስ በኩል ቃል ገብቷል፡

38 እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።

39 ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘላለም እንዲፈሩኝ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።

40 ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።

(ኤርምያስ 32)

ሕዝቡ ለዘላለም እርሱን ይፈሩ ዘንድ ጌታ አዲስ ልብን እንደሚሰጣቸው በኤርምያስ በኩል ቃል ገብቷል። ይህ አዲስ ልብ ጌታ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ እና እንዲታዘዙ ያደርጋቸዋል። በህይወት ውስጥ ባደረጓቸው ውሳኔዎች እና ምርጫዎች ውስጥ የእርሱን ዓላማ እንዲያስቡ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል። እግዚአብሔርን ማገልገል እና ስሙን ማክበር በዚህ አዲስ ልብ ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጠው ቦታ ይኖረዋል።

እግዚአብሔር የድሮውን የድንጋይ ልባቸውን አስወግዶ አዲስ የሥጋ ልብ እንደሚሰጣቸው በሕዝቅኤል በኩል ለሕዝቡ ነግሯቸዋል፡

25 ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።

26 አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።

27 መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። (ሕዝቅኤል  36)

 

የዚህን አዲስ ልብ እና መንፈስ ውጤት እንደገና ልብ ይበሉ። የእግዚአብሔር ሰዎች በሕጎቹ እንዲራመዱ እና ደንቦቹን ለመታዘዝ እንዲጠነቀቁ ያደርጋቸዋል (ቁጥር 27) ። አዲስ ታማኝነት እና ፍቅር ይኖራል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጠው ልብ የተነሳ ከእርሱ ጋር በአንድነት ለመራመድ ይናፍቃሉ።

እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባን ነገር፤እግዚአብሔር ለሕዝቡ አዲስ ልብ ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም ለዚህ ሕይወትን የሚቀይር ለውጥ እርሱን እንዲጠይቁት ይፈልግ ነበር። ዳዊት በሕይወቱ ወደትክክለኛው መንፈስወደ እግዚአብሔር የጮኸበት ቦታ እንዴት እንደመጣ ቀደም ብለን ተመልክተናል። ከዚህ ጩኸት በስተጀርባ ዳዊትን በአመጹ ምክንያት ማሳደዱ ይቀጥል ዘንድ የእግዚአብሔር ሥራ ነበር። እግዚአብሔር በዘማሪው ዓመጸኛ ልብ ውስጥ ሥራን ሠርቷል። ከቤርሳቤህ ጋር ከሠራው ኃጢአት በኋላ እግዚአብሔር በሕይወቱ ላይ ያለው እምነት በጣም ኃይለኛ ስለነበረ የዳዊት የድንጋይ ልብ ተሰበረ ከዚያም በውስጡ አዲስ መንፈስ እንዲሰጠው እግዚአብሔርን ለመነ። ለአዲስ ልብ የዳዊት ጩኸት የግል ምርጫ ነበር ነገር ግን በሕይወቱ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ ባለው እምነት የተነሳ የተደረገ ምርጫ ነበር።

እግዚአብሔር አዲስ ልብ ሊሰጠን ይፈልጋል። በሕዝቅኤል 1820 ላይ በሕይወታቸው ውስጥ ይህን ሥራ ይሰራ ዘንድ እንዲፈቅድለት እንዴት ሕዝቡን እንደሚለምን ልብ ይበሉ፡

30 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

31የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ?

32የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።  (ሕዝቅኤል 18)

 

የእግዚአብሔር ተግዳሮት ለሕዝቡ ኃጢአታቸውን እና ዓመፃቸውን ጥለው አዲስ ልብ እና መንፈስ እንዲያደርጉ ነበር (ቁጥር 31) ይህን አዲስ ልብ እና መንፈስ ለመቀበል እንዴት ተቻላቸው? ከኃጢአታቸው ተመልሰው ወደ እግዚአብሔር መጮህ ነበረባቸው። እሱን ከፈለጉ ይህን አዲስ መንፈስ ይሰጣቸዋል። እሱ ማድረግ የፈለገው ነገር ይህ ነበር፤ዳሩ ግን ምርጫ አቀረበላቸው። ስለ ምን ትሞታላችሁ?”ሲል ይጠይቃቸዋል። ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ” (ቁጥር 32) ። የእግዚአብሔር ህዝብ ይህን ለማድረግ ውሳኔ ነበረው። እነርሱ በአመፀኛ የኃጢአት ልብ ምክንያት በአመፅ ሊሞቱ ይችላሉ፣ወይም ወደ እርሱ በመጮህ አዲስ ልብ ይሰጣቸዋል።

ሐዋሪው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍላቸው እንዲህ ይላቸዋል፡

17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

18 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ (2 ቆሮንቶስ 5)

 

መዳን ምንድ ነው? እንደ ጳውሎስ ገለጻ በክርስቶስ ሥራ አዲስ ፍጥረት መሆን ማለት ነው። አዲስ ሰው ማለት ምን ማለት ነው? አዲስ ልብ እና መንፈስ መቀበል ማለት ነው። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን በነቢያቱ አማካይነት ቃል የገባው ይህን ነው። የእግዚአብሔርን ማዳን የሚለማመዱ ሰዎች በፈቃዳቸው ይለወጣሉ። ፍላጎቶቻቸው እና ቅድሚያ የሚሰጡት ነገር ሁሉ አዲስ ይሆናል። የተቀበሉት አዲሱ ልብ ክርስቶስንና የእርሱን ዓላማ ይናፍቃል። አሮጌው ሃሳብ እና ምኞት አልፏል። አሁን በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ መመላለስ እና ከእሱ ጋር ህብረት ማድረግን ይሻሉ።

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቲቶ ሲጽፍ የመዳንን ሥራ በኢየሱስ ሥራ በኩል በሚደረግ የመንፈስ ቅዱስ መታጠብና መታደስ እንደሆነ አብራርቷል።

4 ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥

5 እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

6-7 ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው። (ቲቶ 3)

ከጳውሎስ ስለ ጢሞቴዎስ ከተላከው መልዕክት ማየት የሚገባን ነገር መዳን ኃጢአታችንን ማጠብ ወይም ማጥራት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ መታደስም ጭምር ነው። በሌላ አገላለጽ እኛ ይቅር የተባልን ብቻ ሳይሆን የተለወጥን ነን።               ልባችን እና አዕምሯችን በእግዚአብሔር መንፈስ ውስጣዊ ሥራ ታድሰዋል። ፈቃዳችን የተለወጠው ጌታ እግዚአብሔርን እና በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ዓላማ እንዲፈልጉ እና እንዲናፍቁ ነው።

ኃጢአት ከፍቃዳችን አመፅ ጋር የተያያዘ ቢሆንም መዳን የፍቃዳችን መታደስ ነው። እግዚአብሔር የድሮውን የድንጋይ ልብ አስወግዶ በለሰለሰ የሥጋ ልብ ተክቶታል።   እሱ ዓመጸኛውን መንፈሳችንን እንደ ፈቃዱ እና ​​መሻቱ መሰረት በሚያስደስት መንፈስ ይቀይራል። መዳን የኃጢአታችን ይቅርታ ብቻ ሳይሆን የልባችን እና የመንፈሳችን መታደስ ነው። እሱ እኛነታችንን የሚቀይር የህይወት ለውጥ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ለመኖር ሲመጣ ከውስጣችን ይለውጠናል። ከአሁን በኋላ ያው ሰው አይደለሁም። የእኔ ፍላጎቶች ተቀይረዋል። ቅድሚያ የምሰጣቸው ነገሮች ተለውጠዋል። የእኔ አመለካከቶች ተለውጠዋል። አሁን የማደርጋቸው ምርጫዎች ከታደሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ህብረት የመጣ ነው።

 

ለግንዛቤ፡

መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልብ እንዴት ይገልጸዋል?

ዳዊት የልቡን ኃጢአተኝት ወደ መረዳት እንዴት መጣ?

ኃጢአተኛ ልባችንን ለማወቅ የእግዚአብሔር መንፈስ ምን አይነት ሚና ይጫወታል?

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እግዚአብሔር ለእኛ አዲስን ልብ ለመስጠት ያለውን ፍላጎት በተመለከተ ምን እንማራለን?

እግዚአብሔር ልባችንን ሲያድስ ወይም አዲስ ልብን ሲሰጠን ምን አይነት ለውጦች ይመጣሉ? የዚህ ፈቃድ መታደስ በምንወስነው ውሳኔ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል?

 

ለጸሎት፡

እግዚአብሔር ልባችሁን እና አዕምሯችሁን ለውጦታልን? ከሆነ፤ለሰጣችሁ አዲስ ሕይወት ለማመስገን ጊዜ ውሰዱ፤ካልሆነ፤ዛሬ ልባችሁን እንዲያድሰው ጸልዩ

መንፈስ ቅዱስ ፈልጎ ስላገኛችሁ እና ስለ ለወጣችሁ አመስግኑ። ኃጢአታችንን እና የእግዚአብሔር ማዳን እንደሚያስፈልግን ስለገለጠልን አመስግኑ።

በልብ እና በአዕምሮ መታደስ ትኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳችሁ ጸልዩ። እርሱን የሚያከብር ውሳኔዎችን መወሰን እንድትችሉ ጸጋን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ። 


 

ምዕራፍ 13 - ቅድስና፡ የፈቃዳችን መማረክ

 

በመጨረሻው ምዕራፍ እግዚአብሔር እንዴት አዲስ ልብ ሊሰጠን እንደሚፈቅድ ተነጋግረናል። መረዳት የሚያስፈልገን ነገር አዲስ ልብ እና ፈቃድ የተሰጣቸው ሰዎች እንኳን ከእግዚአብሔር እና ከዓላማው ሊርቁ እና በሕይወት ውስጥ እግዚአብሔርን የማይፈሩ ውሳኔዎችን ሊያደርጉ ይችላሉ።

በአዲሱ ኪዳን ጌታ ህዝቡን ወደተማረከ የመታዘዝ ሕይወት ጠርቷል። አዲስ ልብን በተቀበሉ ሰዎች እንኳን በሥጋ ሃሳብ የመመላለስ ፈተና ይኖራል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ተጋድሎ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡

 

14 ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ።

15 የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።

16 የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። (ሮሜ 7)

 

ሐዋርያው ጳውሎስ በሥጋውና እና እግዚአብሔር በሰጠው በአዲሱ ልብ መካከል ጦርነት ገጥሟል። በልቡ ኃጢአትን እና በእግዚአብሔር ላይ ማመጽን ይጠላል ዳሩ ግን ሥጋው እግዚአብሔርን በማይፈራ ሕይወት ሲኖር ያገኘዋል። በውጤቱም አንድ ውጊያ በእሱ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ ውጊያ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ይካሄዳል። ጳውሎስ የሮማ ክርስቲያኖችን በመንፈስ  እንዲመላለሱ እና የሥጋ ሥራዎችን እንዲገድሉ አበረታቷል፡

 

13 እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። (ሮሜ 8)

አማኖች ለሥጋ ምንም እድል እንዳይጡ ይመክራል፡

14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። (ሮሜ 13)

ጳውሎስ ለገላቲያ ሰዎች ጽፍላቸው እንዲህ በማለት ይናገራል፡

16 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።

17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። (ገላትያ  5)

 

የክርስቶስ የሆኑት እና ይህንን አዲስ ልብ የተቀበሉ ሥጋዊ ፍላጎቶቻቸው እና ምኞቶቻቸውን በመስቀል ላይ ይሰቅላሉ የሚለው የሐዋርያው ጳውሎስ ተስፋ ነበር:

24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። (ገላትያ  5)

ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሲጽፍ ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ ያንጸባርቃል፡

1-2 ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና። (1 ጴጥሮስ 4)

እንደ ጴጥሮስ ገለጻ ከሆነ፤ከሥጋ እና ከስሜቱ ጋር ለመታገል ራሳቸውን ማስታጠቅ የአማኞች ግዴታ ነው። አዲስ ልብን ተቀበልን ማለት ኃጢአተኛ ከሆነው ሥጋዊ ምኞቶች ጋር በጭራሽ አንታገልም ማለት አይደለም። ውጊያ ካለ፤ስለ ለረከሱ ምኞቶች የበለጠ እንድንገነዘብ ያደርገናል። በውስጣችን ያለው የክርስቶስ ብርሃን የኃጢአትን ጨለማ ይገልጣል። ይህ ደግሞ ከሥጋ ጋር ያለንን ውጊያ ይጨምራል። ሁለቱም ሐዋሪያት ጳውሎስና ጴጥሮስ አማኞች ያን ውጊያ በማስተዋል እንዲመለከቱ ያሳስቧቸዋል። አማኞች ለእግዚአብሔር ዓላማ እንዴት እጅ መስጠት እና የክፉ ሃሳቦችን መቃወም እንደሚችሉ መማር አለባቸው።

ጳውሎስ የሮሜ ሰዎች ሰውነታቸውን እንደ ሕያው መስዋዕት አድርገው ለጌታ እንዲያቀርቡ ያበረታታቸዋል፡

1 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

2 የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። (ሮሜ 12)

 

11 ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤

12-13 ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ (ቲቶ  2)

 

ኢየሱስ በዮሐንስ 17 ላይ ለደቀመዛሙርቱ የጸለየውን ጸሎት እንመልከት፡

16 እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።

17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። (ዮሐንስ   17)

ኢየሱስ እግዚአብሔር አብ ደቀመዛሙርቱን በእውነት እንዲቀድሳቸው ይጠይቃል። ጳውሎስ በሮሜ 12 አማኞች በአዕምሯቸው መታደስ እንዲለወጡ ያሳስባቸዋል። እነዚህ አማኞች አዲስ ልብ የተቀበሉ ቢሆንም የእግዚአብሔር የውጥ ሂደት ይቀጥል ዘንድ እንዲፈቅዱለት ተበረታተዋል። ይህ ለውጥ የአንድ ጊዜ ኩነት ሳይሆን በሕይወት ዘመን የሚቆይ ሂደት ነው ስለሆነም በየዕለቱ ፈቃዳችንን ለእግዘአብሔር ዓላማ ማስገዛትን የሚጠይቅ ነው።

እንዲሁም ቲቶ አንባቢዎቹን ኃጢአተኝነትን እና ዓለማዊ ምኞትን የሚያስክድ የእግዘአብሔርን ጸጋ አንደተቀበሉ ያስታውሳል፡

 

ቀጥሎም ያ እውነት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መገኘቱን ይነግራቸዋል። እዚህ ጋር ሁሉም አማኝ እርሱን ይመስሉ ዘንድ የእርሱ ፈቃድ ነው ጌታ ኢየሱስ ይናገራል። እርሱን የሚመስሉበት መንገድ እውነት ነው። ቃሉን ሲያሰላስሉ እና ሲታዘዙ እርሱን ወደ መምሰል ይመጣሉ። ክርስቶስን ቢመስሉ ሥጋቸውን ከመሻቱ እና ምኞቱ ጋር መዋጋት እና በክርስቶስ እውነት ለመመላለስ መምረጥ ነበረባቸው። ፈቃዳችን ለእርሱ እና ለዓላማው ሳናስገዛ በክርስቶስ ወደ ማደግ ልንመጣ አንችልም።

መቀደስ ፈቃዳችንን ለእርሱ አሳልፈን በመስጠት ኢየሱስን እየመሰልን ይበልጥ የምናድግበት ሂደት ነው። ይህ ለሥጋችን ምኞት ለመሞት ውሳኔን ይጠይቃል። ከክርስቶስ ጋር ባለን ህብረት ማደግ ከፈለግን የሚወሰድ ውሳኔ አለ። በሁሉም ነገር የእርሱን ዓላማ በመምረጥ ቁርጠኝነት ማድረግ አለብን። የራሳችንን ሀሳቦች መደርደር እና በእርሱ ፈቃድ ለመራመድ ቀዳሚ ማድረግ አለብን። በብዙ መንገዶች በማደግ እና ባለማደግ መካከል ያለው ልዩነት የምርጫ ጉዳይ ነው። በክርስቶስ ያደጉ ሰዎች ፈቃዳቸውን ለእርሱ አሳልፈው ለመስጠት የወሰኑ ናቸው። ምንም ያህል ወጪ ቢጠይቅም በመታዘዝ ለመራመድ ወስነዋልና።

ይህ ሁላችንም ማድረግ ያለብን ውሳኔ ነው። በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ለመራመድ እንመርጣለን ወይስ ለሥጋችን ምኞቶች እጅ እንሰጣለን? እኛ ፍጹም ታዛዥ ለመሆን ራሳችንን እንሰጣለን ወይንስ ክርስቶስን ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ ላለማድረግ እናመቻምቻለን?

 

ለግንዛቤ፡

አዲስ ልብ ተቀበለናል ማለት ፈተና አይገጥመንም ማለት ነውን?

በሥጋ እና በአዲሱ ልብ መካከል ያለውን ውጊያ አብራራ? ይህን ተግዳሮት በግል ሕይወትህ አጋጥሞህ ያውቃልን?

ሁሉም አማኞች ያደጉ ናቸውን? በክርስቶስ ስናድግ ውሳኔአችን ምን አይነት ሚና ይኖረዋል?

ፈቃዳችንን ለእርሱ ሳናስገዛ በክርስቶስ ማድግን ልንለማመድ እንችላለን?

 

ለጸሎት፡

በመታዘዝ ለመመላላስ ትክክለኛ ምርጫዎችን በማድረግ የተሰጣችሁን አዲስ ልብ መጠበቅ ትችሉ ዘንድ እንዲረዳችሁ ጸልዩ

በሕይወታችሁ ለአግዚአብሔር አና ለዓላማው ያልተገዛ ክፍል ካለ ጌታ እንዲያሳያችሁ ጸልዩ። እርሱን እና ዓላማውን ትመርጡ ዘንድ የሚረዳችሁን ይቅርታ እና ጸጋን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።


ምዕራፍ 14 - እምነት: ከፍጻሜ የመድረስ ጥንካሬ

 

ጌታ ሲያድነን እርሱ ኃጢአታችንን ብቻ ሳይሆን ይቅር ያለን አዲስ ልብ እና ፈቃድም ሰጥቶናል። በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ አዲስ ልብ ተቀብለናል ስንል ከሥጋ ምኞት ጋር በጭራሽ አንታገልም ማለት እንዳልሆነ ተመልክተናል። በተቀበለው አዲስ ልብ ምክንያት በአማኙ ወይም በአማኟ ሕይወት ውስጥ ውጊያ ይነሳል። ሥጋ የዚህን ዓለም ነገር ይመኛል የእግዚአብሔርንም ዓላማ ይቃወማል። የተቀበልነው አዲስ ልብ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እና እርሱን እና የእርሱን ዓላማ የሚሻ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ ያሉ አማኞችን ሥጋን ከክፉ መሻቱ እና ከምኞቱ ጋር እንዲሰቅሉ እና  (ገላትያ 5:24) በመንፈስ መመላለስን ይማሩ ዘንድ ያበረታታቸዋል (ገላትያ 5 16)

በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ አማኞች ለራሳቸው እንዲሞቱ፣መስቀላቸውን አንስተው ጌታ ኢየሱስን ይከተሉ ዘንድ ጥሪ ያቀርባል። በዮሐንስ 12 ውስጥ ኢየሱስን የተናገረውን ተመልከቱ፡

24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።

25 ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። (ዮሐንስ 12)

 

ኢየሱስ እርሱን ለመፈለግ ሁሉን ትተን እንከተለው ዘንድ ጥሪን ያቀርባል። ማቴዎስ 4 ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን እንዲከተሉ ያቀረቡትን ጥሪ ይተርካል፡

18 በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።

19 እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

20 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

21 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።

22 እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።(ማቴዎስ 4)

ኢየሱስ እነዚህ ሰዎች ሥራቸውን ትተው የእርሱ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ እንዴት እንደጠየቃቸው አስተውሉ። ኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ ላይ ሙሉ ታማኝነትን ይጠብቃል፣ይህም ደግሞ መስዋዕትነት ይጠይቃል።

13 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልናሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል።ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። (ሉቃስ 16)

አንድ ቀን አንድ ሀብታም ወጣት ገዥ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀው። ኢየሱስ ሁሉንም ነገር እንዲሸጥ እና እንዲከተለው ነገረው፡

21 ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። (ማቴዎሰ 19)

በዚያን ቀን ሃብታሙ ወጣት ገዢ በሕይወቱ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ውሳኔ ወሰነ፡ 

22 ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። (ማቴዎስ 19)

ወደ ጌታ ኢየሱስ ጀርባውን አዙሮ ሄደ። የኢየሱስ ደቀመዝሙር ለመሆን ሁሉንም ነገር ለመተው ፈቃደኛ አልነበረም። ከኢየሱስ ይልቅ ሀብቱን መረጠ።

ጌታን ለመከተል ራሳቸውን ለኢየሱስ አሳልፈው ለሚሰጡ ሁሉ ጌታ እንደሚከተለው ቃል ገብቷል፡

29 ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉመቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። (ማቴዎስ 19)

 

እያንዳንዱ አማኝ ሊወስነው የሚገባ አንድ ትልቅ ውሳኔ አለ። ሁሉንም አሳልፈን በመስጠት ጌታ ኢየሱስን እንከተላለን? መስቀላችንን አንስተን ያለማፈር የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንሆናለን? በዓላማው ለመመላለስ ወደማናውቀው እንሄዳለን?

 

ይህንን ከባድ ጥያቄ ለሚቀበል ሁሉ ትልቅ ጥርጣሬ አለ። በመሠረቱ ንብረቶቻችን ይዘን እና በተለመደው የሕይወታችን ዘይቤ ውስጥ ስንኖር ደህንነት ይሰማናል።               ጌታ ይህንን ሁሉ ለእርሱ አሳልፈን እንድንሰጥ ቢጠይቀንስ? ራሳችንን እና ድክመቶቻችንን አውቀን በተቃውሞ ውስጥ መጽናት እንደምንችል እናስባለን። የአገልግሎት ፈተና እና የክርስትናን ሕይወት መሸከም ለእኛ በጣም ይበዛብን ይሆን? ብቁ አለመሆናችንን እየተሰማን ነገር ግን እናደርገው ዘንድ ጌታ የሚጠራን ጊዜ አለ። እንደ ሀብታሙ ወጣት ገዥ ሁሉ እኛም ሁሉንም ነገር ለመስጠት፣መስቀላችንን አንስተን ኢየሱስን እንከተል ዘንድ በእግዚአብሔር ጥሪ ፊት ቆመናል። ውሳኔያችን ምን ይሆን? በዛ ጥሪ እንዴት መጽናት እንችላለን? የዚህ መልስ ከእምነት ጋር የተያያዘ ነው፡

እምነት በዕብራውያን 11 ውስጥ እንደሚከተለው ተብራርቶ ተቀምጧል፡

11:1 እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። (ዕብራውያን 11)

እምነት በአዕምሮ እውቀት ማየት ወይም መረዳት የማንችላቸውን ነገሮች ማረጋገጫ ነው። በእግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ መተማመን ነው።

ዕብራውያን 11 የእምነት ወንዶችና ሴቶች ምሳሌዎችን ይሰጠናል። በቁጥር 7 ላይ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ቁርጠኛ ውሳኔ ካደረገው እና እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ብቻ መርከብን ለመስራት ስለተነሳው ኖኅ እናነባለን፡

7 ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። (ዕብራውያን 11)

አብርሃም ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ የእግዚአብሔርን መሪነት በመከተል አገሩን ለቆ ወጣ፡

8 አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። (ዕብራውያን 11)

ሙሴ ሕዝቡን በምድረ በዳ ወደተስፋይቱ ምድር ለመምራት ከግብፅ የሚያገኛቸውን ጥቅሞች ትቶ ወጥቷል።

24 ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤

25-26 ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። (ዕብራውያን 11)

 

በርካታ ቅዱሳን መከራ እና ስቃይ ያላቸውን ሁሉ ሲነጥቋቸው በጽናት እንዲቆሙ ያደረገቻው ያው ተመሳሳይ እምነት ነው። እነዚህ ቅዱሳን በእምነት የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። (ዕብራውያን 1132-34) በሕይወት ውስጥ ታላላቅ መሰናክሎችን ተቋቁመው እግዚአብሔርን እና ቃሉን በመታመን አስደናቂ ድል አግኝተዋል:

35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤

36 ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤

37 በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤

38 ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።

39-40 እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና። (ዕብራውያን 11)

ድልን የሰጣቸው በእግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ ያላቸው እምነት ነበር በዕብራውያን 11 ውስጥ የነበሩ ወንዶችና ሴቶች አስፈላጊ ውሳኔዎችን ወስነው ነበር ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍም ለአምላካቸው ለጌታ በታማኝነት እና በመታዘዝ ለመጓዝ ቆርጠው ነበር ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደሚኖር ጠንቅቀው በማወቅም ያንን ውሳኔ አሳለፉ እነርሱ በእግዚአብሔር እና የሰጣቸውን የተስፋ ቃል በመታመን ወደማያውቁት የሕይወት ልምምድ መጡ ከራሳቸው የሚበልጡትን ጠላቶች አሸነፉ የጨለማ ኃይላትን ድል ነስተው በአሸናፊነት እና በታማኝነት ሕይወት በመታዘዝ ወደ እረፍቱ ገቡ

ሐዋርያው ዮሐንስ ከእግዚአብሔር የተወለዱት ዓለምን እንደሚያሸንፉ ይናገራል ያ ድል እንዴት ሊሆን እንደሚችል አስተውሉ፡

4 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።

5 ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?(1 ዮሐንስ  5)

ድልን የሚሰጠን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ነው በኢየሱስ እና በቃሉ እናምናለን በመንፈሱ ባለው ኃይል እንተማመናለን በእርሱ እና በእርሱ መሪነት ስለምናምን በድፍረት እንወጣለን ለእኛ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ የሚቻል መሆኑን እናውቃለን

እምነት ውሳኔዎቻችንን እና እግዚአብሔርን በቁርጠኝነት ለመከተል የሚያስፈልገን ጥንካሬ ነው በእርግጥ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በእያንዳንዱ ውሳኔ በእግዚአብሔር ማመን አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ያሳስበን ነበር ለሮሜ ሰዎች የተናገረውን ተመልከቱ፡

23 የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። (ሮሜ 14)

 

በልባችን ውስጥ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር ይሰጠናል እርሱ በእኛ ውስጥ ሲሠራ፣ለጌታ እና ለዓላማው በቁርጠኝነት ለመሰጠት እንነሳሳለን እያንዳንዱ ቀን የራሱን ውሳኔዎች ያመጣል በእምነት እና በመታዘዝ እንድንመላለስ ወይም የእግዚአብሔርን ቃል እና የመንፈሱን እምነት መቃወምን እንድንመርጥ ተጠርተናል ትክክለኛ ውሳኔዎችን እንድናደርግ እና ነገሮች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ በእነዚያ ውሳኔዎች እንድንጸና የሚያስችለን እምነታችን ነው በኢየሱስ እናምናለን በተስፋዎቹም እንታመናለን አንዳንድ ጊዜ በፍርሃት እንወጣለን ነገር ግን ፍርሃት የሚሸነፈው እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ እና ምንም ቢከሰትም እንደሚጠብቀን ስናምን እና በእርሱ ስንደገፍ ነው የምንወስናቸው ውሳኔዎች እና የምንወስዳቸው ቁርጠኝነቶች በእግዚአብሔር ላይ ባለን እምነት፣ፈቃድ እና መቻል መጠንከር እና መደገፍ አለባቸው እስከ መጨረሻው ለመከተል ጥንካሬ የሚሰጠን ይህ ነውና

 

 

ለግንዛቤ፡

ውሳኔዎቼ ሁልጊዜ ህይወቴን ቀላል ያደርጉት ይሆን? መከራን የሚያመጡ ውሳኔዎችን ለምን እንወስናለን? ዕብራውያን 11ን እና በዚያ የተገለጹትን የእምነት ሰዎች ውሳኔዎችን እንመልከት፡

እምነት ምንድ ነው?

እምነት እንዴት ቁርጠኝነተችን ያጠነክራል፤እንዲሁም ውሳኔዎቻችንን እንዴት ይደግፋል?

በምትወስኑት ውሳኔ እና በምታደርጉት መሰጠት ውስጥ እምነትን እስከምን ያህል ድረስ ትተገብሩታላችሁ?

 

ለጸሎት፡

የምትወስኑት ውሳኔ ሕይወታችሁን ምንም ያህል ችግር ውስጥ የሚከታችሁ ቢሆንም እንኳን ትክክለኛውን ውሳኔ ለመወሰን እግዚአብሔር ጸጋ እንዲሰጣችሁ ጸልዩ

እግዚአብሔር በእርሱ እና በቃሉ ላይ ያላችሁን እምነት እንዲያበረታው ጸልዩ። በመታዘዝ በድፍረት መውጣት እንዲያስችላችሁ ጸልዩ።

እግዚአብሔር በሰጠህ አገልግሎት እና ተግባር ውስጥ ራስህን ተጨንቀህ  አግኝተዋልን? በእሱ እና በተስፋዎቹ ላይ እምነትህ እና መተማመንህ እንዲጨምር እግዚአብሔርን ጠይቅ። ለሕይወትህ ባለው መንገድ እንዲመራህ እና በዓላማው ውስጥ ሰላም እንዲሰጥህ ጸልይ።


ምዕራፍ 15 - ጸጋ የመውደቅ ነጻነት

 

በዚህ ጥናት ሂደት ውስጥ ጌታ እግዚአብሔር የመምረጥ ኃላፊነት እንደሰጠን አይተናል። የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በሕይወታችን ውስጥ ውጤቶችን ያስከትላሉ። ትክክለኛውን ምርጫ ሁሉም ሰው አያደርግም። ኢየሱስ በማቴዎስ 2514-30 ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ እሱ በማይኖርበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ እንዲሰሩ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው በምሳሌ ይናገራል።

ጌታው ለእያንዳንዱ ሶስት አገልጋዮቹ እንዳቅሙ ገንዘብ ሰጣቸው። ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው ለሁለተኛው ደግሞ ሁለት ሰጠ እንዲሁም የመጨረሻው አገልጋይ አንድ መክሊት ብቻ ተቀበለ። አምስት እና ሁለት መክሊት የተቀበሉ አገልጋዮች የተቀበሉትን ገንዘብ በስራ ላይ በማዋል እያንዳንዳቸው ለጌታቸው እጥፍ አተረፉ። ጌታው የመጨረሻውን አገልጋይ በገንዘቡ ስለሰራው ስራ ምላሽ እንዲሰጠው ሲጠይቀው፤እንዲህ በማለት መለሰለት፡

24 አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤

25 ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።

(ማቴዎስ  25)

አንድ መክሊት የተቀበለው ሎሌ ጌታውን እንደሚፈራ እና መክሊቱን በምድር ውስጥ እንደቀበረው ነገረው። እስቲ ይህንን ለአፍታ አስቡት። ይህ ግለሰብ ጌታውን ላለማስከፋት ይፈራ ነበር። የተቀበለውን ገንዘብ በሥራ ላይ የማዋል ውሳኔ አስፈላጊ እንደሆነ ያውቅ ነበር። ጌታውም የሰጠው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ይጠብቃል። ይህ አገልጋይ የተሳሳተ ውሳኔ ካደረገ እንደሚወድቅ እና ጌታው የሰጠውን ገንዘብ ሊያጣ እንደሚችል ያውቅ ነበር። ሃሳቡ ገንዘቡን ለማጥፋት ባለመፈለግ በስራ ላይ ሳያውለው እና ሳያተርፍበት ጌታው ከጉዞው ወደ ቤቱ ሲመለስ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ማድረግ ነው።

የውድቀት ፍርሃት ለእኛ በጣም እውነተኛ ጉዳይ ነው። ብዙ አማኞች በዚህ ፍርሃት ሽባ ሆነዋል። በመፍራት ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረግ እንደማንችል ሁሉ እንዲሁም በቁርጠኝነት ወደፊት መቀጠል አንችልም። ብዙ ጊዜ ብቁ እንደሆንን ስለማይሰማን ውሳኔ ከማድረግ ወደ ኋላ እንላለን። በሕይወታችን ላይ በእግዚአብሔር ጥሪ እና ያንን ጥሪ ለመፈፀም በሚያስችለን በእሱ ችሎታ ላይ እምነት አይኖረንም።

አንዳንድ ቁርጠኛ የሆነ ውሳኔ ለመወሰን የምንታገልበት ምክንያት ካለፉት ውድቀቶቻችን ጋር የተቆራኘ ነው። በአርባ ዓመቱ የእስራኤልን ልጆች ከባርነት ነጻ ለማውጣት የሞከረውን ሙሴን እንደ ምሳሌ እንመልከት። በሐዋርያት ሥራ 724-25 ገለጻ መሠረት እስራኤላውያን እነርሱን ለማዳን ዝግጁ መሆኑን እንዲገነዘቡ ስለፈለገ በዕብራይስጡ ባሪያ ላይ ግፍ ሲፈጽም የነበረን አንድ ግብፃዊን ገደለ። ዕብራውያን ባሪያዎች ግን አዳኛቸው እንዲሆን የሙሴን ግብዣ ውድቅ አደረጉ። ሙሴ ግብፃዊውን እንዴት እንደገደለ ዜናው ይፋ ሲወጣ፣ሙሴ ሕይወቱን ለማትረፍ ሃገሩን ጥሎ ለመሸሽ ተገደደ።

ከአርባ ዓመታት በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ከሚቃጠለው ቁጥቋጦ ሙሴን አነጋግሮ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ሲጠራው ሙሴ ሌላ ሰው እንዲልክ እግዚአብሔርን ተማጸነ። ለእንዲህ ዓይነቱ ተግባር ብቁ እንዳልሆነ ስለተሰማው ሁሉንም ዓይነት ሰበብ ሰጠ። ቀደም ሲል ውድቀት ስላጋጠመው ሙሴ ለእግዚአብሔር ጥሪ ራሱን ለመስጠት ትግል እያደረገ ሊሆን ይችላልን? ያንን ውድቀት እንደገና መጋፈጥ አልፈለገም። በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጥሪ በመታዘዝ የሚመጣውን አደጋን ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም።

በሉቃስ 15 ውስጥ ስለ አባካኙ ልጅ የኢየሱስን ምሳሌ እናነባለን። ይህ ልጅ ውርሱን ሁሉ ሰብስቦ ከቤት ለመውጣት ወሰነ። ሩቅ በሆነ ሃገር ውስጥ ግድየለሽነት የተሞላበት የአኗኗር ዘይቤ በመኖር ገንዘቡን ሁሉ አባክኖ ጨረሰ። በዚያም ያለውን ሁሉ ጨረሰ። ከዚያም ልጁ እጣ ፈንታው ሞት ብቻ መሆኑን ሲያውቅ ወደ አባቱ ለመመለስ ወሰነ። ወደ ቤቱ ሲደርስ አባቱ በሞቀ አቀባበል ተቀበለው። አባቱ ሊቀበለው ሲወጣ አባካኙ ልጅ የተናገረውን ያዳምጡ፡

21 ልጁም፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው። (ሉቃስ 15)

ይህ ልጅ በግድየለሽነት እና በኃጢአት የተሞላውን ህይወቱን በማወቁ ጥልቅ የሆነ የማይገባው አይነት ስሜት ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ። በአባቱና በአምላኩ ላይ ኃጢአት ሠርቷልና። ከአሁን በኋላ ልጅ ለመሆን ብቁ ሆኖ አልተሰማውም። የቀድሞ ኃጢአታችን እና ውድቀቶቻችን ለእግዚአብሔር እና ለአገልግሎቱ ጥልቅ የሆነ ቁርጠኝነት እንዳናደርግ ያደርጉናል። እንደ እዚህ ልጅ ሁሉ እኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመሆን ብቁ እንዳልሆንን ይሰማናል። እርሱ እንዴት እኛን በጭራሽ ሊያምነን ወይም ይቅር ሊለን እንደሚችል አልገባንም።

 

ያለመቻላችን ፍርአት፣ያለፈው ውድቀቶቻችን እና የጌታን ይቅርታ አለመረዳት ለጌታ እና ለህይወታችን ካለው ዓላማ ጋር ቁርጠኛ የሆነ ውሳኔ እንዳናደርግ ያደርገናል። በእነዚህ ስሜቶች ስንጨናነቅ መታዘዝን መምረጥ ከባድ ነው።

ጸጋ የሚሰራው እዚህ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚገባንን የማይሰጠን ቸር አምላክ ነው። ይህንን በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ላስረዳ።

ሐዋርያው ጴጥሮስ ከጌታ ጋር ባለው ግንኙነት የሚኩራራ በራሱ የሚተማመን ሰው ነበር። ኢየሱስ ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ሲነግረው፣ጴጥሮስ ከማንም በላይ ተገርሞ ነበር። ሌሎቹ ደቀመዛሙርት ሁሉ ቢክዱት እንኳን በእርግጠኝነት እርሱ እንደማይክደው ለኢየሱስ ነገረው። ኢየሱስ የተናገረው በተፈጸመ ጊዜ ግን ጴጥሮስ እጅግ አዘነ። ሉቃስ 22:62 “መራራ ልቅሶእንዳለቀሰ ይነግረናል።

እዚህ ጋር መመልከት ያለብን ጉዳይ ጴጥሮስ ኢየሱስን ከካደ በኋላ ሕይወቱ ላይ ምን እንደሆነ ነው። የሐዋርያት ሥራ 2 በበዓለ ሃምሳ ዕለት የተከናወነውን ነገር ገልጧል። ጴጥሮስ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ፊት እንዲቆም የእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሳው። በዚያ ቀን በሕይወቱ ውስጥ በጣም ኃይለኛ ከሆኑት መልዕክቶች መካከል አንዱን ሰበከ። በውጤቱም 3,000 ሰዎች ሕይወታቸውን ለጌታ ኢየሱስ በመስጠት ወደ ቤተክርስቲያኗ ተጨመሩ። ጴጥሮስ በመቀጠል ታማኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ቁልፍ ሰው ሆነ። ጴጥሮስ ጌታውን ቢክድም ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ ይቅርታን፣መንጻትን እና አዲስ ጅምርን ሰጠው።

በጴጥሮስ ህይወት ላይ የተፈጸመው እውነት እንዲሁ በሕይወቱ በአንድ ወቅት   ለክርስቶስ እና በዘመኑ በነበረችው ቤተክርስቲያን ላይ ጠላት ሆኖ ለተነሳው ሐዋርያው ጳውሎስ ደግሞ ይህ እውነት ነው። እሱ እንደሚለው ኑፋቄን የሚሰብኩ የዓለም ክርስቲያኖችን ለማስወገድ ዘመቻ ጀመረ።  ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ ጌታ ኢየሱስን ሲገናኝ የዚህ ሰው ሕይወት ተለወጠ። ያለፉት ውድቀቶች እና ኃጢአቶች ሁሉ ይቅር የተባሉ ሲሆን ጳውሎስ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታላቁ ሚስዮናዊ ሆኖ ቀጠለ። ጳውሎስ ያለፈውን ጊዜ አልረሳም፣ነገር ግን በይቅርታ በተቀበለው የእግዚአብሔር ጸጋ በታላላቅ መሰናክሎች ውስጥ እንኳን ለመፅናት አስችሎታል። ሐዋርያው ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ እንዲህ ይላል፡

9 እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፤

10 ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።  (1 ቆሮንቶስ 15)

ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ከንቱ እንዳልሆነ እንዴት እንደነገራቸው አስተውሉ። በዚያ ጸጋ ምክንያት እርሱ ከማንኛውም ሐዋርያ የበለጠ ጠንክሮ ሊሠራ ወስኖ ነበር። ጳውሎስ በእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት በጣም ከመደሰቱ የተነሳ ራሱን ለአምላኩ ሙሉ በሙሉ አሳልፎ ለመስጠት ወሰነ።                   ትዳር ሳይዝ፣ስለ ኢየሱስ በመስበክ እና በማስተማር ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይዘዋወር ነበር። እሱ ከማንኛውም ሐዋርያ የበለጠ መከራን በጽናት ተቋቁመዋል፣ነገር ግን እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። የእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ላይ ለማገልገል ኃይለኛ ተነሳሽነት ነበረው።

ሉቃስ 7 አንዲትኃጢአተኛ ሴትኢየሱስ ከፈሪሳውያን ጋር ማዕድ ለመቅረብ ወደ ተቀመጠበት ቤት እንዴት እንደመጣች ይነግረናል። እሷም ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ ወደ ኢየሱስ ቀርባ ተንበርክካ በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች። ኢየሱስን ወደ ቤቱ የጠራው ፈሪሳዊ ተበሳጭቶ ለራሱ እንዲህ አለ፡

39 የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። (ሉቃስ 7)

ኢየሱስ የፈሪሳዊውን ልብ ሀሳብ ስላወቀ ሁለት ዕዳ ስለነበረበት ሰው ምሳሌ ተናገረ። የመጀመሪያው 500 ዲናር እና ሁለተኛው ደግሞ 50 ዲናር ዕዳ ነበረበት። ገንዘብ አበዳሪው ግን ሁለቱንም ዕዳዎች ለመሰረዝ ወሰነ። ኢየሱስ ወደ ቤቱ የጋበዘውን ፈሪሳዊውን ስምዖንን የትኛው አበዳሪ የበለጠ አበዳሪን እንደሚወድ ጠየቀው። ከፍተኛ ዕዳ ያለው ሰው አበዳሪውን በጣም ይወደው ይሆናል ብሎ ለኢየሱስ መለሰለት። ኢየሱስ የምሳሌውን ትርጉም ለስምዖን በመንገር ይቀጥላል።

44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።

45 አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም።

46 አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች።

47 ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል። (ሉቃስ 7)

 

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገርብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።የሚለው ሃረግ ነው። ኢየሱስ ይህች ሴት ኃጢአተኛ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ ትኖር እንደነበረች አልካደም። እግዚአብሔርን አሳዝናለች እንዲሁም ብዙ ሰዎችን ጎድታለች። እዚያ በስምዖን ቤት ውስጥ ግን አስደናቂ የሆነውን የኢየሱስን ጸጋ ተለማመደች። ኃጢአቷ ሁሉ ይቅር ተባለላት። የእሷ ያለፈ ታሪክ ከእንግዲህ ወዲህ በእሷ እና በአምላኳ መካከል ግድግዳ ሆኖ አይቆምም። በዚያን ቀን ኢየሱስእምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት።”(ሉቃስ 748-50) እስከምናውቀው ድረስ በኢየሱስ ፍቅር ውስጥ ኖራለች።

የሰራውን ሥራ ለመደበቅ የሴቲቱን ባል የገደለው ዳዊት፣ሐዋርያት ሥራ 13 እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነ ሰው እንደሆነ ይናገራል:

22 እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ። (ሐዋ 13)

በሚሞትበት ጊዜ  የነበረውን የዳዊትን ሕይወት መልዕክት እንመልከት፡ 

26 የእሴይም ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ።

27 በእስራኤልም ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ፤ ሰባት ዓመት በኬብሮን ነገሠ፥ ሠላሳ ሦስትም ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ።

28 ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ። (1ኛ ዜና  29)

 

ዳዊት፣ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ (ቁጥር 28) ። ዳዊት ኃጢአት የሌለበት አልነበረም፣ዳሩ ግን ከእግዚአብሔር አስደናቂ ጸጋ የተነሳ በክብር ሞተ። እርሱ ታላቁ የእስራኤል ንጉስ በመባል ይታወቃል፡

እነዚህ ምሳሌዎች ስለዚህ ጥናት ርዕሰ ጉዳይ ምን ያስተምሩናል? ትክክለኛ ውሳኔዎችን እና ቁርጠኝነትን ከማድረግ የሚያግዱን በህይወት ውስጥ ብዙ መሰናክሎች እንዳሉ እንማራለን። ፍርሃታችን፣ያለፉ ውድቀቶቻችን እና ይቅርታን ለመቀበል አለመቻላችን ትክክለኛውን ነገር እንዳናደርግ እና ጌታን ከመታዘዝ እንድንወጣ ያደርገናል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እንድንወድቅ እና እንደገና በእግራችን እንድንቆም ነፃነትን ይሰጠናል። የእግዚአብሔር ጸጋ የምንወድቅበትን ነፃነት ይሰጠናል። በህይወት ውስጥ መጥፎ ውሳኔዎችን ላደረጉ ሰዎች ወርዶ ምህረትን እና ንፅህናን ይሰጣቸዋል። አዲስ ለመጀመር እድሉን ይሰጣቸዋል። ጴጥሮስ ኢየሱስን ከካደ በኋላ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ፊት ለመቆም እድል የሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ኃጢአተኛዋን ሴት በፊቱ ተንበርክካ በእንባዋ እግሩን እንድታጥበው እና ይቅርታን የሰጣት  የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ጳውሎስ ላሳደደው ክርስቶስ ሕይወቱን እንዲሰጥ ድፍረት የሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ ነበር።

የጌታ እግዚአብሔር ቸርነት ሳያስፈልገን ማንኛችንም በሕይወት ውስጥ ጸንተን አናልፍም። ሁላችንም በህይወት ውስጥ መጥፎ ውሳኔዎችን አድርገናል። ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ወድቀናል። የእግዚአብሔርን ኃይል በተጠቀሙ እና መክሊታቸውን በተደበቁ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት የእግዚአብሔርን ጸጋ ሙሉ በሙሉ ይቅር ለማለት ብቻ ሳይሆን ለማስቻል ካላቸው ግንዛቤ ጋር የተቆራኘ ነው።

 

ከእግዚአብሔር በኃይል የተጠቀሙት ይቅር የተባሉ እና በዚያ ይቅርታ ውስጥ የገቡት ናቸው። ለውድቀቶቻቸው የእርሱን ማንጻት ተቀብለዋል። ብቁ እንዳልሆኑ ቢሰማቸውም የእርሱን ጥሪ ታዘዋል። የእርሱን ጸጋ ለመቀበል እና ለስሙ ክብር በመታዘዝ ለመውጣት ወስነዋል።

ፍርሃት አለዎት? ውድቀትን ይፈራሉ? ያለፈው ጊዜዎ ኃጢያት እግዚአብሔር ይቅር ለማለት እጅግ የበዛ እንደሆነ ይሰማዎታል? እሱ ሌላን ሰው ሊጠቀም እንደሚችል ይሰማዎታል፣ነገር ግን እርስዎ እንዲሁ ብቁ አይደለሁም ብለው ያስባሉን? እነዚህ ስሜቶች እግዚአብሔር የጠራቸውን ውሳኔዎች እንዳያደርጉ ይከለክልዎታልን? ምናልባት የጸጋን ተፈጥሮ መረዳት ያስፈልግዎት ይሆናል። ጸጋ እግዚአብሔር ለማይገባው ሰው የሚሰጠው ሞገስ ነው። የእግዚአብሔር የሚሰጠን የሚገባን ባይሆንም ነገር ግን የእርሱን ይቅር ባይነት እና የማስቻል ልምድን እንዲያመልጠን አንፈልግም። ጸጋ ለራሳቸው ለሚጠቀሙ ሁሉ በይቅርታ እና ምህረት የመውደቅ ነፃነት ይሰጠናል።

 

 

ለግንዛቤ፡

ዛሬ ማድረግ ያለብዎትን ውሳኔ ከማድረግ የሚያግድዎት ነገር ምንድን ነው?

እግዚአብሔር ታደርጋቸው ዘንድ የሚጠይቅህን ውሳኔዎች እና ቁርጠኝነቶች እንዳታደርግ ያሉብህ ፍርሃቶች ምንድ ናቸው?

ያለፉት ውድቀቶችህ ዛሬ ትክክለኛውን ውሳኔ ከማድረግ ሊያግዱሀ ይገባልን?

ጸጋ ምንድ ነው? የእግዚአብሔርን ጸጋ በሕይወት ተለማምደህ ታውቃልን? የእግዚአብሔር እውቀት እንዴት በእርሱ ዓላማ በድፍረት እንድትወጣ ያስችልሃል?

 

ለጸሎት፡

እርሱ ዛሬ እንድትወስናቸው የነገርህን ውሳኔዎች ከመወሰን የሚያግዱህን መሰናክሎች እንዲያሳይህ ጸልይ

በፍርሃቶች ላይ እግዚአብሔር ድል እንዲሰጥገህ ጸልይ። እርሱ የጠየቀህን ታደርግ ዘንድ የሚያስፈልግህን ሁሉ ሊሰጥፍ ፈቃደኛ ስለሆነ እግዚአብሔርን አመስግን።

እርሱ የምህረት ዓምላክ ስለሆነ ያለፈውን ውድቀቶችህን ሁሉ ይቅር ሊል ፈቃደኛ ስለሆነ እግዚአብሔርን አመስግን። የእርሱ ክብር መጠቀሚያ ለመሆን ፍጹም መሆን ስለሌለብህ እግዚአብሔርን አመስግን።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በአንድ ወቅት ሲያሳድደው የነበረውን በሕይወቱ እንዲያገለግለው በረዳው የእግዚአብሔር ጸጋ ተደንቋል። በሕይወትህ ስላለው የእግዚአብሔር ጸጋ ታመሰግን ዘንድ ጸልይ።

 


ምዕራፍ 16 - የተስፋ ቃል ኪዳኖች አምላክ

 

እግዚአብሔር ራሱ ለማድረግ የማይፈልገውን እንድናደርግ አይጠይቀንም።                የውሳኔ አሰጣጥ የእግዚአብሔር ባሕርይ አካል ነውእሱ ይመርጣል፣ይፈጽማል እንዲሁም የተስፋ ቃልን ይሰጣል። እስቲ ይህን የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ ገፅታ ለመመልከት ጥቂት ጊዜ እንውሰድ።

በኖህ ዘመን ምድር በጣም ተበላሽታ ነበር። የሰው ልጅ ልቡን ከእግዚአብሔር መልሶ፣ሰዎች በፊታቸው ደስ ያሰኛቸውን ሁሉ ያደርጉ ነበር። ይህም እግዚአብሔርን አስቆጥቶ ሰውን ለማጥፋት ወሰነ። ከሁሉም የምድር ቤተሰቦች ግን የኖህን ቤተሰቦች ለማዳን መረጠ። ዘፍጥረት 6 እግዚአብሔር ከዚህ ቤተሰብ ጋር ስላደረገው ቃልኪዳን ይናገራል፡

17 እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።

18 ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አቆማለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።

19 ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለት እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁን። (ዘፍጥረት 6)

በዚያ ቀን እግዚአብሔር ኖኅንና ቤተሰቡን መርጦ ከሚመጣው ፍርድ ጠበቃቸው። በዚህ ቤተሰብ አማካኝነት እንደገና ምድርን ሞላ።

ከዚያም በዘፍጥረት 15፣እግዚአብሔር ከሌላ ቤተሰብ ጋር ስምምነት ለማድረግ መረጠ

1 ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።

2 አብራምም፦ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ።

3 አብራምም፦ ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል አለ።

4 እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።

6 አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። (ዘፍጥረት 15)

 

እግዚአብሔር የአብርሃምን ቤተሰብ በቁጥር ማብዛት እና ታላቅ ህዝብ በማድረግ መባረክን መርጧል። ዘፍጥረት 17 እግዚአብሔር ለአብርሃም ቤተሰብ ስለጠው የተስፋ ቃል ተጨማሪ ዝርዝር ያስቀምጣል፡

4 ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።

5 ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፤ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።

6 እጅግም አበዛሃለሁ፥ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።

7 ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።

8 በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ። (ዘፍጥረት 17)

 

እግዚአብሔር የአብርሃምን ቤተሰብ ታላቅ ህዝብ እንዲያደርግ ቃል ገብቷል። የአብርሃም ዘሮች አምላክ ለመሆን እና የራሳቸው የሆነ ምድር እንዲሰጣቸው የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል። እግዚአብሔር ሌሎች አሕዛብን አውጥቶ መሬታቸውን ለአብርሃም ልጆች ይሰጣቸዋል፡

ይህ ጌታ ለአብርሃም ቤተሰብ ያለው ቁርጠኝነት በተደጋጋሚ ተፈትኗል፣ዳሩ ግን እግዚአብሔር ለቃሉ ታማኝ ነው። እግዚአብሔር የአብርሃምን ዘር የመረጠው ከሌሎች የምድር ህዝቦች የተሻሉ በመሆናቸው አይደለም። በእነርሱ ላይ እንዲቆጣ ብዙ ምክንያት ነበረው። እግዚአብሔር ግን ለሰጠው የተስፋ ቃል ታማኝ ስለሆነ የተናገረውን ሁሉ ለማድረግ ራሱን ሰጠ። ሙሴ በዘዳግም 9 ላይ ለሕዝቡ ይህንን በማስታወስ እንዲህ ይላል፡

4 አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ካወጣቸው በኋላ፦ ስለ ጽድቄ እወርሳት ዘንድ ወደዚች ምድር እግዚአብሔር አገባኝ ስትል በልብህ አትናገር፤ እነዚህን አሕዛብ ስለ ኃጢአታቸው እግዚአብሔር ከፊትህ ያወጣቸዋል።

5 ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው። (ዘዳግም  9)

 

2ኛ ሳሙኤል 7 ጌታ እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲህ በማለት የተስፋ ቃልን ሰጠው፡

16 ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል። (2 ሳሙኤል 7)

ጌታ የዳዊትን ቤተሰብ እንዴት እንደመረጠ እና ለእነሱም ጽኑ ቃልኪዳን እንደገባ እንደገና አስተውሉ። እግዚአብሔር ለዳዊት መንግሥቱ እንደሚጠነክር እና ዙፋኑም ለዘላለም እንደሚጸና የተስፋ ቃልን ሰጠው። የዚህ ፍጻሜ ደግሞ በዳዊት ዘር ለዘላለም የሚገዛው ጌታ ኢየሱስ ነው።

ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እንዴት ሰብስቦ ከእነርሱ ጋር እንጀራ እንደቆረሰ እናነባለን። እንጀራውን ሲቆርስ እና ወይኑን ሲካፈል ኢየሱስ ለተሰበሰቡት እንዲህ አላቸው፡

20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። (ሉቃስ 22)

የቃል ኪዳኑን ማጣቀሻ ልብ ይበሉ። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ከእነሱ እና ከእነሱ በኋላ ለሚከተሉት ሁሉ ቃልኪዳን እየገባ መሆኑን ነግሯቸዋል። የዚያ ቃል ኪዳን ባህሪ ምን ነበር? ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮማውያን የአዲሱ ቃል ኪዳን ክፍል የኃጢአት ይቅርታ እንደሚሆን ነግሯቸዋል፡

27 ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው። (ሮሜ 11)

የዕብራውያን ጸሃፊ የሚከተለውን ያክላል፡

 

10 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።

11 እያንዳንዱም ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም፥ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።

12 ዓመፃቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም። (ዕብራውያን  8)

 

ጌታ እግዚአብሔር ለሚቀበሉት ሁሉ ራሱን ለመስጠት ምርጫው አድርጓል። አምላካቸው ለመሆን ቃል ገብቷል። ለእሱ እና ለዓላማው ጥልቅ የሆነ መሻትን በመስጠት ልባቸውን እንደሚያድስ ቃል ገብቷል። ኃጢአታችንን ይቅር ለማለት ከልቡ ወስኗል። ይህ ለእኛ ያለው ቁርጠኝነት ነው።

ዘማሪው ዳዊት በእግዚአብሔር ተስፋዎች እና ቃል ኪዳን ላይ ከፍተኛ እምነት ነበረው።

8 እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስልኛል አቤቱ፥ ምሕረትህ ለዘላለም ነው፤ አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል። (መዝሙር  138)

በጣም በሚፈተን ሁኔታ ውስጥ እንኳን ጌታ እንደማይተወው ታመነ።

በነብዩ ኢሳይያስ በኩል ጌታ እግዚአብሔር ራሱ የሚከተለውን ይናገራል፡

15 በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።

16 እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ። (ኢሳይያስ 49)

እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ቁርጠኝነት ከማንኛዋም እናት ቁርጠኝነት ይበልጣል። እርሱ መቼም አይረሳንም። በእውነቱ ኢሳይያስ 4916 በእጆቹ መዳፍ ላይ እንደተቀረጸን ይነግረናል። እኛ ሁልጊዜ በፊቱ እና በሃሳቡ ውስጥ አለን። እርሱ ስለእኛ እያንዳንዱን ዝርዝር ያውቃል እንዲሁም የሕይወታችንን እያንዳንዱን ክፍል ይቆጣጠራል።

 

ስለ ኃይለኛው የእግዚአብሔር ተዋጊ ኢያሱ ሲናገር፤ጌታ እንዲህ ይላል፡ 

5 በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። (ኢያሱ 1)

እግዚአብሔር የምርጫዎች እና የቁርጠኛ ውሳኔ አምላክ ነው። እኛ ዛሬ እርሱን እናውቀዋለን ምክንያቱም ለእኛ ራሱን ለመግለጥ ስለመረጠ እና ልባችንን እስኪያሸንፍ ድረስ ስለተከተለን ነው። ዛሬ የምንኖረው እግዚአብሔር ሕይወትን ሊሰጠን ስለመረጠ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ቁርጠኝነት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ በጭራሽ አናውቅም። ስንት ጊዜ ሕይወታችንን በደህንነት ተጠብቋል? ስንት ጊዜ ከጉዳት ጠብቆናል? መንገዳችንን ስንት ጊዜ ቀይሮታል?

ታላቁ ፈጣሪ ለምን በዚህ መንገድ ይንከባከበኛል? ለምን ራሱን ለእኔ አሳልፎ ይሰጣል? እኔን ለማዳን እና በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላኝ ለምን ወሰነ? ለምን ይባርከኛል ለምንስ  ይጠብቀኛል? ለምን በእኔ ይጠቀማል? ለእነዚህ ጥያቄዎች በጭራሽ መልሶች ላይኖርን ይችላል፣ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምርጫ ሁልጊዜ አመስጋኞች መሆን አለብን። እርሱ ለሕዝቡ ራሱን አሳልፎ የሰጠ እና ለሕይወታቸው ለሰጣቸው የተስፋ ቃሎች እውነተኛ እንደሚሆን ቃል የሚገባ አምላክ በመሆኑ ሁልጊዜ መደሰት አለብን።

እኛን የመረጠን እና ራሱን ሙሉ በሙሉ ለእኛ የሚሰጠን አምላክ፣የእርሱን ምሪት እንድንከተል ይጠይቀናል። እርሱን እንመርጠው ዘንድ ይጠራናል። እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀውን ያሳየናል። እርሱን መምረጥ እንችል ዘንድ እርሱ አስቀድሞ መርጦናል። እኛ በምላሹ ራሳችንን ለእርሱ እንድንሰጥ እርሱ ራሱን ለእኛ ይሰጠናል።

ቁርጠኝነት እና ውሳኔዎች የእግዚአብሔር ባሕርይ አካል ናቸው እንዲሁም የክርስትና ሕይወታችንም አካል ይሆናሉ። እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ ለመሆን ከፈለግን አንዳንድ ከባድ ውሳኔዎች ማድረግ ይኖርብናል። ከእነዚህ ውሳኔዎች ውስጥ የመጀመሪያው እኛ ከምናገለግለው አምላክ ጋር የሚዛመድ ነው። ኢያሱ እንዲህ በማለት ይናገራል፡

15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። (ኢያሱ 24)

 

እኛ ማድረግ ያለብን ሁለተኛው ውሳኔ በማቴዎስ 16 ውስጥ ካለው ከኢየሱስ ቃላት ጋር ይዛመዳል፡

24 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። (ማቴዎስ 16)

ከፊታችን ያለው ጥያቄ ይህ ነው: ራሳችንን ክደን ጌታ ኢየሱስን ለመከተል መስቀላችንን እንሸከማለን? ጳውሎስ ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ።በማለት ይናገራል (ፊልጵስዩስ 3:7-8 ተመልከት)

የተስፋን ቃል የሰጠው አምላክ ከእርሱ ጋር ወደዚህ ቃል ኪዳን ይገቡ ዘንድ እርሱ እንደገባላቸው ሁሉ እነርሱም ቁርጠኛ ውሳኔ እንዲወስኑ ይጠብቃል።                       እርሱ ስለመረጣቸው እነርሱም ይመርጡታል (ዮሐ 15 16) እርሱን ይወዱታል ምክንያቱም እርሱ አስቀድሞ ወዷቸዋልና (1 ዮሐንስ 4:19)። ይቅር ስላላቸው ሌሎችን ይቅር ይላሉ (ሉቃስ 11:14) እርሱ ስለ እነሱ ስለ ሞተ ለራሳቸው ይሞታሉ (ሮሜ 12:1)

ክርስትና የቁርጠኝነት እና የምርጫ ሕይወት ነው። በመጀመሪያ ለእኛ የተሰጠ የእግዚአብሔር ምርጫ እና መሰጠት ነው። ነገር ግን ይህ እኛ ለእርሱ የምንሰጠው ምላሽ መሆን አለበት። እግዚአብሔር በአምሳሉ ፈጠረን፤ስለዚህ የአምሳሉ ክፍል ደግሞ የመምረጥ ችሎታ ነው። ከሁሉም ውሳኔዎች በጣም አስፈላጊው ለእርሱ ካለን ቁርጠኝነት ጋር ይዛመዳል።

 

ለግንዛቤ፡

እግዚአብሔር የቁርጠኝነት እና የውሳኔ አምላክ መሆኑን የሚያሳይ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ምን ማስረጃ አለ?

እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያደረገላቸውን ቤተሰቦች እና ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ ጥቀስ? እግዚአብሔር እነዚያን ቃል ኪዳኖች ለምን አደረገ?

ኢየሱስ በእርሱ ከሚያምኑት ጋር የሚያደርገው የቃልኪዳን ባህሪ ምንድ ነው? በዚህ ቃል ኪዳን ሥር የሰጠን የተስፋ ቃል ምንድ ነው?

እንደ እግዚአብሔር አምሳል በመፈጠራችን ምን አይነት ውሳኔዎች እና ቁርጠኝነቶችን ማድረግ አለብን?

በእግዚአብሔር ምርጫ ደስተኞች መሆን ይገባናል ወይስ የራሳችንን ምርጫ መምረጥ አለብን? እርሱ ለእኛ የገባውን የተስፋ ቃል ላለመያዝ መወሰን እንችላለን? ውጤቱ ምንድ ነው?

 

ለጸሎት፡

በልጁ በኢየሱስ በኩል ልጆቹ ሊያደርገን ስለፈለገን እግዚአብሔርን ስለ ውሳኔው እና የተስፋ ቃሉ አመስግነው

የማይገባህ እንኳን ብትሆንም እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልህ እና ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን ስላደረገ በግልህ ጌታን አመስግን

እርሱ ለአንተ ራሱን አሳልፎ ስለሰጠ አንተም ለእርሱ ፍጹም ራስህን አሳልፈህ መስጠት ትችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጥህ ጸልይ


 

ምዕራፍ 17 - የቅዱሳን ውሳኔዎች

 

ጌታ ኢየሱስን ለመከተል የሚደረግ ውሳኔ ቀለል ባለ መንገድ የሚወሰድ አይደለም፣ምክንያቱም እንዲህ ያለውን ቃልኪዳን ለሚፈጽሙ ሁሉ የሚከፍል ዋጋ አለና። በሉቃስ 14 ላይ የሰፈረውን የኢየሱስን ቃል ተመልከቱ:

 

26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

27 ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

28 ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቈጥር ማን ነው?

29 ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ።

30 ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ።

31 ወይም ሌላውን ንጉሥ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ፥ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉሥ ማን ነው?

32 ባይሆንስ ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል።

33 እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። (ሉቃስ 14)

 

ኢየሱስን ለመከተል የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ ነው። እርሱን መከተል ከፈለግን ዋጋውን መቁጠር እንዳለብን ኢየሱስ ይነግረናል። የእርሱ ደቀመዝሙር ለመሆን ቤተሰቦቻችንን እና የራሳችንን ህይወት አሳልፈን መስጠት አለብን። መስቀላችንን ለመሸከም ፈቃደኞች መሆን አለብን እንዲሁም ለራሳችን ፈቃድ እና ምኞት ለመሞት ዝግጁ መሆን አለብን። በሁሉም ነገራችን እርሱ የመጀመሪያ መሆን አለበት። የእርሱ ዓላማ ከራሳችን በፊት መምጣት አለበት። እርሱን ለማክበር ያለንን ሁሉ በፈቃደኝነት አሳልፈን መስጠት አለብን። በሕይወታችን ውስጥ ከእሱ እና ከሱ ፈቃድ የበለጠ ምንም አስፈላጊ ነገር ሊኖር አይችልም።

አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?በማለት ንጉስ ዳዊት ይጠይቃል። በሌላ አገላለጽ በእግዚአብሔር ፊት ማን ይቆማል በህልውናውስ ውስጥ ማን  ይኖራል? ማለት ነው። በመዝሙር 15 ላይ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ እንመልከት፡

1 አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?

2 በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።

3 በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።

4 ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም። (መዝሙር  15)

 

በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም እና በቅድስናው ውስጥ ለመኖር የሚችል በአምላኩ ፊት በቅንነት ለመኖር ቁርጠኛ ውሳኔ የወሰነ ሰው ብቻ ነው። በቁጥር 4 መሠረት እርሱለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም ነው። በሌላ አገላለጽ፣ታማኝነትን ከማጣት ይልቅ በፈቃደኝነት ጉዳትን ወይም ሞት እንኳን ቢሆን ይቀበላል ማለት ነው። ይህ ጌታ  በህልውናው ውስጥ ሊያኖረው የሚያስደስተው ዓይነት ሰው ነው።

ሁላችንም የተጠራነው ከጌታ ጋር መሄድን ወይም አለመሄድን እንድንመርጥ ነው። የመረጥነው ምርጫ በሕይወታችን ላይ ዘላቂ ተጽዕኖ ይኖረዋል። የልባችንን ቅድሚያዎች የሚወስን ሕይወትን የሚቀይር ውሳኔ ይሆናል። በክርስትና ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር ህዝብ ምርጫ እንዲመርጡ ተጠርተዋል።

ማርቲን ሉተር በምርጫው ምክንያት የሚመጣበትን መዘዞች ጠንቅቆ ቢያውቅም በመጽሐፎቹ በጻፈው ላይ ማስተካከያ ያደርግ ዘንድ ለመጠየቅ በተሰበሰቡት የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጉባኤ ፊት ቆሞ ሉተር እንዲህ ብሎ ነበር፡

 

በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ወይም ግልፅ በሆነ ምክንያት ካልተረዳሁ በቀር (በሊቀ ጳጳሱም ሆነ በምክር ቤቶቹ ብቻ እምነት የለኝም፣ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ የሚሳሳቱ እና የሚቃረኑ መሆናቸው በደንብ ስለሚታወቅ)፣በጠቀስኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የታሰርኩ ነኝ እንዲሁም ህሊናዬ ለእግዚአብሔር ቃል ምርኮኛ ነው። ከሕሊና ውጪ መሄድ ጤናማም ትክክልም ስላልሆነ ምንም ነገር ላስተካክል ልተውምም አልችልም። እግዚአብሔር ይርዳኝ። አሜን (https://en.wikipedia.org/wiki/Diet of_Worms)

በውሳኔው ምክንያት ሉተር ሊደበቅ ተገደደ። የቅዱስ ሮማን ኢምፓየር ጉባኤ (The Diet of Worms) ማርቲን ሉተርን በተመለከተ የሚከተለውን አዋጅ አውጥቶ ነበር፡

በዚህ ምክንያት ማርቲን ሉተር የተባለውን ሰው ለመቀበል፣ለመከላከል፣ለመደገፍ ወይም ለማገዝ በቃልም ሆነ በድርጊት መነሳት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለማንም የተከለከለ ነው። በተቃራኒው እኛ እንደመናፍቅነቱ መጠን እንደተያዘ እንዲቀጣ እንፈልጋለን በግል ወደ እኛ እንዲቀርብ ወይም የያዙት እስኪያሳውቁን ድረስ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲጠበቅ እንፈልጋለን፣ከዚያ በኋላ ማርቲን ሉተር በተባለው ላይ ተገቢውን የፍርድ ሂደት እንዲጀመር እናዛለን። ሉተርን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚረዱ ሁሉ ለመልካም ሥራቸው በልግስና ይሸለማሉ። (https://en.wikipedia.org/wiki/Diet_of_Worms)

ማርቲን ሉተር በእግዚአብሔር ቃል ባመነበት እውነት ላይ ጸንቶ ለመቆም በወሰነው ውሳኔ ምክንያት የሚፈለግ ሰው ሆነ። ለጌታ ታማኝ ለመሆን የመረጠው ምርጫ ዋጋ ነበረው፣ዳሩ ግንተጎድቶምለእውነት ታማኝ ለመሆን ፈቃደኛ ነበር። (https://en.wikipedia.org/wiki/Diet_of_Worms)

1956 አምስት ሚስዮናውያን የኢኳዶር የሁዋራኒ ሕንዳውያንን ለመጎብኘት ሄደው ነበር። አደገኛ መሆኑን ቢያውቁም ለጥቂት ወራቶች ከእነሱ ጋር ግንኙነት ሲገነቡ ቆይተው ጥልቅ የሆነ ሕብረት ለማድረግ ጊዜው እንደሆነ ተሰማቸው። እ...በጥር 1956 አስር የሁዋራኒ ተዋጊዎችን ያገኗቸው ሚስዮናውያኑ እነርሱን ወዳጅ ለማድረግ ቢጥሩም ጥቃት ሰንዝረው ገደሏቸው። እነዚህን ሁዋራኒ ሕንዳውያንን ለማነጋገር በዚያ ቀን ያደረጉት ውሳኔ ገዳይ ነበር።

እነዚህ ሚስዮናውያን ወደዚህ ጠላት ወደነበረው የህንድ ጎሳ ለመድረስ እንዲሞክሩ ያደረጋቸው ምንድን ነው? በእነዚህ ጦረኞች ከተገደሉት መካከል ጂም ኤሊዮት የሚባል ሰው ይገኝበታል። የሚከተለውን ጥቅስ እንመልከት፡

 

... ጥቅምት 28 ቀን 1949 የጽሁፉ መግቢያ ላይ፣ለኢየሱስ የተሰጠ ሥራ ከህይወቱ የበለጠ አስፈላጊ የሆነበት እምነቱን ይገልጻል (ሉቃስ 924ን ተመልከቱ "ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል።")  እንዲሁም ሊያጣ የማይችለውን ለማግኘት የማይችለውን የሚሰጥ ሞኝ አይደለም።" በማለት ጽፏል። (https://en.wikipedia.org/wiki/Jim_Elliot)

 

እነዚህ ሚስዮናውያን የሚስከፍለውን ዋጋ ቆጥረው ዓለምን በክርስቶስ ለመድረስ ሲሉ ሁሉንም ነገር ለማስቀመጥ ፈቃደኞች ነበሩ። የእነርሱ ምርጫ የእግዚአብሔር ዓላማ ከህይወታቸው የላቀ መሆኑን በመረዳት ላይ የተመሠረተ ነበር። በሂደቱ ውስጥ ህይወታቸውን ቢያጡ እንኳን ይታዘዙ ነበር።

.ዲ ግሪርየዊሊያም ኬሪ 11 ውሳኔዎችበሚል ርዕስ በወጣው ጽሑፍ በህንድ ሚስዮናዊ የነበረው የዊሊያም ኬሪ ውሳኔዎችን ገልጧል፡

1.     ለሰዎች ነፍስ ማለቂያ የሌለው ዋጋ መስጠት

2.     የሰዎችን አዕምሮ ከሚይዙ ወጥመዶች ጋር ራሳችንን ማስተዋወቅ

3.     ሕንድ በወንጌል ላይ ያላትን ጥላቻ ከሚያጠናክር ከማንኛውም ነገር መራቅ

4.     ለሕዝቡ መልካም ለማድረግ የሚያስችሉ ሁሉንም ዕድሎችን መመልከት

5.     እንደ ትልቅ የመለወጫ መንገድ "የተሰቀለውን ክርስቶስን" መስበክ

6.     ህንዶችን ሁልጊዜ እኩያችን አድርገን ማክበር እና እና መያዝ

7.     "ብዙዎች የሚሰበሰቡባቸውን" መጠበቅ እና መገንባት

8.     ሕንዳውያንን በክርስቶስ ወንጌል የሚደርሱት ሕንዳውያን ስለሆኑ ከሚሲዮናዊ ግዴታ አንጻር ግፊት በማሳደር መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን ማሳደግ

9.     በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ዘንድ ያለማቋረጥ መሥራት

10.በግል ኃይማኖት እድገት ውስጥ ፈጣን መሆን

11.ራሳችን ስለምንለብሰው ልብስ እንኳን ሳናስብ ለጉዳዩ ያለመጠባበቂያ ራሳችንን መስጠት (https://jdgreear.com/blog/william-careys-11-resolutions/)

 

ዊሊያም ኬሪ በሕይወቱ ለእግዚአብሔር ጥሪ ለመታዘዝ በእነዚህ መመዘኛዎች እንዲኖር ወስኖ ሕይወቱን እስከዚህ ድረስ አሳልፎ ሰጥቷል።

ጆን ዌስሊ (1703-1791) የተባለው እንግሊዛዊ የስነ መለኮት ምሁር እና የወንጌል ሰባኪ በማስታወሻው ላይ የሚከተለውን ጽፏል፡

የራሴን ባህሪ በተመለከተ፤አሁን ተለውጬ የቀድሞ ውሳኔዎቼን ጽፌአለሁ።

1.     መነጋገር ከሚገባኝ ሁሉ ጋር ፍጹም ግልፅነትን ለመጠቀም እና ላለመቆጠብ።

2.     ቀጣይነት ካለው ከባድነት በኋላ ወደ ሥራ ለመግባት፤በምንም ዓይነት አንተኛ የስነምግባር ባህሪ፤ሳቅ ለትንሽም ጊዜ ቢሆን እራሴን ለማስነፍ ፈቃደኛ አለመሆን

3.     የእግዚአብሔርን ክብር የማይገልጽ ምንም አይነት ቃል አለመናገር፤በተለይ፤ዓለማዊ ነገሮችን ከመናገር መቆጠብ። ሌሎችም ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ያ ለአንተ ምንድ ነው? እና

4.     እግዚአብሔርን የማያከብር ደስታን አለመካፈል፤ ባለኝ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን እንዲሁም እግዚአብሔርን እንዳላመስገን ከሚደርጉኝን ነገሮች ሁሉ ማራቅ 

(https://www.ccel.org/ccel/wesley/journal.vi.ii.xi.html)

ምንም እንኳን እነዚህ ውሳኔዎች ለሁሉም የማይሆኑ ቢሆኑም፣ጆን ዌስሊ በማንኛውም መንገድ ጌታውን የሚያስደስት ሕይወት ለመኖር የገባው ቃል ነበር። ሕይወቱን ለመስጠት እና ከጌታው አገልግሎት የሚያግደውን ማንኛውንም ነገር ለመተው ፈቃደኛ ነበር።

1703-1758 የኖረው ታላቁ አሜሪካዊ የኃይማኖት ምሁር እና ሰባኪ ጆናታን ኤድዋርድስ ረጅም የውሳኔዎች ዝርዝር ነበረው። በታህሳስ 2006 “የጆናታን ኤድዋርድስ ውሳኔዎችበሚል ርዕስ የወጣውን የግል ውሳኔዎች ይዘረዝራል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ለማካተት በጣም ብዙ ቢሆኑም ጥቂቶቹን ብቻ ላካፍላችሁ፡

በነፍስም ሆነ በስጋ ቢሆን፣ይነስም ይብዛ፣ማንኛውንም ነገር ለማድረግ በጭራሽ አልወስንም፣ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብር በሕይወቴ ለመጠበቅ እኖራለሁ፤ይህን ማስቀረት አልሻም።

ምንም ጊዜ ላለማባከን ነገር ግን በምችለው መጠን ፍሬአማ በሆነ መንገድ ለማደግ ወስኛለሁ

የህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት ቢሆንም ለማድረግ የምፈራውን መቼም ላለማድረግ ወስኛሁ.

ለሞት ስቃረብ የተመኘሁትን እንዳደረኩ ሆኜ ለመኖር ወስኛለሁ

የመንግሥተ ሰማይን ደስታ፣እና የገሃነም ሥቃይን ቀድሞውኑ እንዳየሁ ኖሮ ማድረግ ያለብኝን ማድረግ እንደምትችል ሁሉ በቻልኩበት መጠን ለማድረግ ወስኛለሁ።

እራሴን በተመሳሳይ እውቀት ማደጌን በግልጽ አውቅ እና አገኝ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት፤ያለማቋረጥ እና በተደጋጋሚ ለማጥናት ወስኛለሁ

ከአሁን ጀምሮ  እኔ የራሴ እንዳልሆንኩ፣ዳሩ ግን ሙሉ በሙሉ እና በአጠቃላይ የእግዚአብሔር እንደሆንኩ ወስኛለሁ።

(https://www.desiringgod.org/articles/the-resolutions-of-jonathan-edwards)

ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በሕይወቱ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና ቁርጠኝነቱን ሲገልጽላቸው የተናገሩትን ተመልከቱ፡  

20 ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።

21 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።( ፊልጵስዩስ 1)

ጳውሎስ በድርጊቱ እና በቃላቱ የማያፍርበትን እንደዚህ ዓይነት ሕይወት ለመኖር በልቡ ወሰነ። በተናገረውም ሆነ ባደረገው ሁሉ ክርስቶስ እንዲከበር ወሰነ። ክርስቶስን በማወቅ ይኖርና ይሞት ነበር።

ስለ ክርስቶስ ብዙ መስዋዕትነት ለመክፈል እና ራሳቸውን ለመስጠት ስለመረጡ በታሪክ ውስጥ ተመዝግበው ስለሚገኙ ብዙ ቅዱሳን ቁርጠኝነት መናገር መቀጠል እንችላለን። እኛ ግን ልብ ልንለው የሚገባን ነገር እነዚህ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ለእግዚአብሔር በግል ቁርጠኛ በመሆናቸውና ሰውነታቸውን እና አዕምሯቸውን ለዚያ ቁርጠኛ ውሳኔ ለእግዚአብሔር ክብር ታማኝ እንዲሆኑ መምረጣቸው ነው።

 

ብዙውን ጊዜ ያለ እኛ ውሳኔ ወይም ቁርጠኝነት እንደሚገለጥ በማሰብ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ለመኖር እንሞክራለን። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን እና እራሱን ለእኛ አሳልፎ ለመስጠት ስለመረጠ ደስተኞች ነን ዳሩ ግን እኛ መልካም ምላሽ አንሰጥም። የመምረጥ ነፃነት የሰጠን አምላክ ውሳኔያችንን ይጠብቃል። እርሱ አስቀድሞ እንደመረጠን ሁሉ እኛም እርሱን በመምረጥ ምላሽ እንሰጣለን? ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ምትክ ስጋችንን፣ነፍሳችንን እና መንፈሳችንን ለእርሱ በማቅረብ እርሱ ለእኛ ስለከፈለው መስዋዕትነት እውቅና እንሰጣለን?

ምርጫ ለማንኛውም ግንኙነት አስፈላጊ ነው። አንድን ሰው ለመውደድ ትመርጥ ይሆናል ነገር ግን በምላሹ እርስዎን ለመውደድ እንደመረጡ ማወቁ ምንኛ አስደሳች ነው። ለክርስቶስ እና ለዓላማው ያለዎት ቁርጠኝነት ምንድ ነው? እንደ ጥንቶቹ ቅዱሳን ሁሉ ሰውነትዎን፣አዕምሮዎን፣ሃብቶችዎን እና ጊዜያችሁን ለእሱ እና ለአላማው ለመስጠት ቁርጥኛ ውሳኔ ያደርጋሉ?

 

ለግንዛቤ:

ከክርስቶስ እና ለህይወታችን ካለው ዓላማ ጋር ጥልቅ ቁርጠኝነት ሳናደርግ በክርስትና ሕይወታችን እናድጋለን ብለን መጠበቅ እንችላለን?

ተግሣጽ እና ቁርጠኛ ውሳኔዎች ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ጉዞ ላይ ምን ሚና ይጫወታሉ?

ከክርስቶስ ጋር ያላችሁን ሕብረት እንዴት ትገልጹታላችሁ? ለእርሱ እና ለአገልግሎቱ ምን አይነት ቁርጠኛ ውሳኔዎችን አድርጋችኋል?

በአንድ በኩል ብቻ ባደላ ግንኙነት ሕብረት ለማድረግ ይቻላልን? እግዚአብሔር እንደመረጠን በማወቅ፤በምላሹ እርሱን መምረጥ ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

 

ለጸሎት

ከእርሱ ጋር በሚኖርህ ጉዞ ዓላማ ያለህ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ጸልይ

ለግል ሕይወትህ እና አገልግሎትህ እርሱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ እንዲያሳይህ ጌታን ጠይቅ። ለእርሱ ያለህ ቁርጠኝነት ምን መሆን እንዳለበት ለመመልከት ጥቂት ጊዜ ውሰዱ። በዚያ ዓላማ ውስጥ ለመራመድ ከልብ የመነጨ ስነስርዓት እንዲሰጥህ ጠይቅ።


 

ላይት ቱ ማይ ፓዝ የመጽሐፍ ስርጭት

 

ላይት ቱ ማይ ፓዝ (LTMP) በእስያ፤በላቲን አሜሪካ እና በአፍሪካ የሚገኙ ድሃ ክርስቲያን አገልጋዮችን የሚደርስ የመጽሐፍ ስርጭት አገልግሎት ነው። በታዳጊ አገሮች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ክርስቲያን አገልጋዮች የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጠና ለማግኘት ወይም ለአገልግሎቶቻቸው እና በግል ለመታነጽ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቁሳቁሶችን ለመግዛት አስፈላጊ የሆኑ ሃብቶች የሏቸውም።

ኤፍ.ዋይኒ ማክ ሌኦድ የአክሽን ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪስ አባል ሲሆን በዓለም ዙሪያ ላሉ ድሃ ክርስቲያን አገልጋዮች ይሰራጩ ዘንድ ዓላማን በማንገብ እነዚህን መጽሐፍቶች ሲጽፍ ቆይቷል።

እስከዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ መጽሐፍት ከስድሳ በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ለስብከት፤ለማስተማር፤ለወንጌል ስርጭት አገልግሎት እና ለአከባቢው አማኞች ማበረታቻ ጥቅም ላይ ውሏል። አሁን መጽሐፍቶቹ ወደ በርካታ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ዓላማው በተቻለ መጥን ለሁሉም አማኞች ተደራሽ ማድረግ ነው።

(LTMP) አገልግሎት በእምነት ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ነው፤በዓለም ዙሪያ ያሉ አማኞችን ለማበረታታት እና ለማነጽ መጽሐፎቹ ይሰራጩ ዘንድ ለእነዚህ አስፈላጊ ሃብቶች ጌታን እንታመናለን ጌታ እነዚህን መጽሐፍት ለመተርጎም እና የበለጠ ለማሰራጨት በሮችን ይከፍት ዘንድ ትጸልያላችሁን? ስለ ላይት ቱ ማይ ፓዝ የመጽሐፍ ስርጭት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ www.lighttomypath.ca